ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ፅ/ቤት
በ2025 ወሳኝ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለነዋሪዎቿ እና ለጎብኚዎቿ ምቹ የሆነች ዘላቂ እና ችግሮችን መቋቋም የምትችል አዲስ አበባን ማየት፡፡ እንዲሁም፡-በከተማ አስተዳደሩ ያሉ ተቋማት ምርታማነታቸውንና አገልግሎቶቻቸውን ማሻሻል የሚያስችላቸው አቅም ተገንብቶ ማየትበከተማ አስተዳደሩ የአገልግሎት አሰጣጥና ምርታማነትን የሚያሻሻል ተቋማዊ አቅም ተገንብቶ ማየት።የላቀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም አኗኗራቸው የተለወጠ ዜጎች።በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን የመጠቀም ባህሉ የጎለበት ዜጋ ማፍራት፡፡በቴክኖሎጂ የበለጸገ ብቁና አምራች ዜጋ ማየት
ለወረዳና ለክ/ከተማ ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጠ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በ3 የስልጠና አርስት ላይ ማለትም 1.webmail 2. acronis True lmage 3. A.A complaint management portal / የካ ክፍለ ከተማ የአይሲቲ ባለሙያዎች እና ለወረዳ የአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰቷል፡፡
ሕዳር 27/2016 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት
ልምድ ልውውጥ
በቀን 6/03/2016 የካ ክፍለከተማ ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት የወረዳ ቡድን መሪዎችን እና የክፍለ ከተማ ኢኖቬሽን ባለሞያዎችንና ቡድን መሪዎች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተደረገ ልምድ ልውውጥ
የካ ክፍለከተማ ኢኖቪሽን ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት ከ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ጋር የተደረገ የስራ ልምድ ልውውጥ
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽህፈት ቤት በ6 ወር የስራ አፈፃፀም በከተማ ደረጃ ተመዝኖ ከ11ዱ ክፍለ ከተማ 2ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነ!!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በዛሬው ዕለት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀሙን ከከተማና ከክፍለ ከተማ ዘርፍ አመራሮች ጋር የገመገመ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማትና ክፍለ ከተሞች እውቅናና ሽልማት በቢሮ ኃላፊዎች እጅ አበርክቷል።
በዚህም የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ጽህፈት ቤት በክፍለ ከተማው ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግና በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻሉ እውቅና ተሰጥቶታል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ማስረሻ ተገኝተው እውቅናውን የተቀበሉ ሲሆን ለውጤቱ መገኘት የክፍለ ከተማው አስተባባሪዎች፣ በየደራጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።
ጽህፈት ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችን ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ያነሱት አቶ ቴዎድሮስ እውቅናው ይበልጥ ጽህፈት ቤቱን የአገልግሎት እርካታ እስኪረጋገጥ እንዲተጋና የተቋም ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያነሳሳው መሆኑን አክለዋል።