የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር
በየካ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ሞዴል ወረዳ ነዉ ። ወረዳው የከተማዋ በምዕራብ አቅጣጫ የሚገኝ ሲሆን በምስራቅ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ይዋሰናል፡፡ወደ ምዕራብና እና ሰሜን አቅጣጫ የአራዳና ክፍለ ከተማ እንዲሁም በደቡብ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ያዋስኑታል፡፡ በመጨረሻዉ የህዝብ ቆጠራ በድምሩ 40,000 (አርባ ሺህ )ነዋሪዎች ይኖሩበታል፡፡ ወረዳዉ 5 ቀበሌዎች 10 ቀጠናዎች እና በ 34 መንደሮች የተከፈለ ነዉ፡፡ ወረዳዉ የህዝቡን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊ ችግሮችን በመፍታት የሚጥር በለዉጥ ላይ ያለ የተለያዩ ሪፎርሞችን በማድረግ በከተማችን ከአዲስ አበባ ግንባር ቀደም ሞዴል ወረዳ ነዉ፡፡የወረዳዉን ሰራተኛ እና የወረዳዉን ነዋሪ በማሳተፍ መጠነ ሰፊ ስራ በመስራት ትልቅ እድገት አሳይቶል፡፡