የካ ወረዳ 08 አስተዳደር ጽ/ቤት በየካ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ 12 ወረዳዎች መካከል በህዝብ ፍሰትም ሆነ በገበያ ማዕከልነት በቀዳሚነት የሚጠቀስ ወረዳ ነዉ፡፡ወረዳዉ በቀደምት ስሙ 11 ቀበሌ የሚባል ሲሆን ከ2000 ዓ/ም በኋላ ነዉ ወረዳ 08 የሚለዉን መጠሪያ ያገኘዉ፡፡Read More
ወረዳ 08 አስተዳደር ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማዉ በስተ ፀሃይ መዉጫ/ምስረቅ በኩል/ ሚካኤል ታቦት ማደሪያ አካባቢ በ1.5 ኪ/ሜ እርቀት ላይ ይገኛል፡፡አስተዳደሩ በንግድ እና በኢኮኖሚ መዳረሻነቱ ከመርካቶ በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ የሚገኝ የክፍለ ከተማዉም ሆነ ለከተማዉ አስተዳደሩ የጀርባ አጥንት የሆነ ወረዳ ነዉ ፡፡ሾላ ገበያ ደግሞ የወረዳዉ ሌላዉ መታወቂያዉ ሆኖ ይጠራል፡፡
ወረዳ አስተዳደሩ በስተ ሰሜን የካ ክፍለ ከተማ፣ በስተ ደቡብ ቦሌ ወረዳ 04፣በስተ ምስራቅ ቦሌ ክፍለ ከተማ እንድሁም በስተ ምዕራብ የካ ወረዳ 07 ያዋስኑታል፡፡
ወረዳ አስተዳደሩ ለህብረተሰቡ የአገልግሎት አሰጣጥ አድማሱን ለማስፋት እና ለማዘመን በሳምንት 6 ቀን እንድሁም ወሳኝ ኩነት የመሰሉ ጽ/ቤቶች ደግሞ በሳምን 8 ቀን እሁድን ጨምሮ ማለት ነዉ ለተገልጋይ ክፍት ሆነዉ አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
ከዚህ ባሻገር ተገልጋዩን ማህበረሰብ እና አገልጋዩን የመንግስት አመራር እና ባለሙያ ፊት ለፊት አገናኝቶ አግልግሎት ለመስጠት በሳምንት ሁለት ቀን ማለትም እረቡ እና አርብ የባለ ጉዳይ ቀን ተብሎ ተሰይሞ አስተዳደሩ ህዝብ የጣለትን ሃላፊነት ለመወጣት እየሰራ ይገኛል፡፡
ወረዳዉ በከተማዉ አሉ ከሚባሉ ደረጃቸዉን የጠበቁ የወጣቶች የስፖርት ማዘዉተሪያ ሜዳዎች መካከል አንዱ ሜዳ ያለዉ ሲሆን በበፌደራል፤ በከተማ እንድሁም በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ ዉድድሮች ይደረግበታል፡፡ ከዚህ ባሻገር የግል እና የዉጭ ድያስፖራ አካላትም ለልምምድ እና ለዉድድር ይጠቀሙበታል የወረዳ 08 11 ቀቤ እግርኳስ ሜዳ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ Facebook ፡- yeka wereda sement
Facebook Page ፡- Yeka woreda 08 communication
Telegram ፡-የካ 08 ኮሙኒኬሽን/Yeka 08 Communication
Youtube :-የካ ወረዳ 08 ኮሙኒኬሽን/Yeka woreda 08 Communication
Twitter :- yeka 08 communication
ስልክ ቁጥር፡-011 18 38 79 00
አድራሻ ፡-ከ 22 ወደ ሾላ ወደሚወስደው መንገድ ካስ ሜዳው ፊት ለፊት ወረዳ 08 አስተዳደር ግቢ ውስጥ