woreda-09

Spread the love
  1. በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አሰስተዳደር አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አሰስተዳደር በክ/ከተማው ስር ከሚገኙ 12 ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በወረዳ ደረጃ የተቋቋመው በ2000 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡ በመሆኑም ወረዳውን በሰሜን አቅጣጫ የካ ክ/ከተማ ወረዳ10 አስተዳደር& በምስራቅ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር & በስተደቡብ ከቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 6 እና ወረዳ 7 አስተዳደር& በስተምራብ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አስተዳደር ጋር የሚዋሰን ሲሆን አጠቃላይ የወረዳ አስተዳደሩ ስፋት 504.02 ሄክታር ይሆናል ፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ውስጥ 16 የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዋቅረው አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ አስተዳደሩ በ24 የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተዋቅሮ በእነዚህ መስሪያ ቤቶች 497 የመንግስት ሰራተኞች በሰው ሀይል አስተዳደር ተቀጥረው በየዘርፉ በየስራ መደቡ ተገልጋዩ ህብረተሰብ ሰፊ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ህብረተሰቡን ለማርካት እየሰሩ ይገኛል፡ ይህንንም ግልጋሎት ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ለማድረግ የተለያዩ ስልቶችን ይጠቀማል፡፡