Map

Spread the love
Map’s of Yeka sub city

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ከሚገኙ አስርአንድ (11) ክፍለ ከተሞች እንዱ የሆነው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 56. 71 እስኩየር ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን በኢትዮጵያ ስታትስቲክ ኤጀንሲ ትንበያ መሠረት በ2014 ዓ.ም 363’100 (ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺ አንድ መቶ) ህዝብ ይኖራል ተብሎ ይገመታል የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ2015 በጀት በ60/90 ቀናት የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የከተማ ግብርና ስራዎች፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማዘመንና ማሻሻል፣ በመልካም አስተዳደር ፣የፀጥታ ስራውን በተቀናጀ መልኩ መስራት፣ የኑሮ ውድነቱን ማረጋጋት፣ ህገ-ወጥ ስራዎችን መከላከል፣ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ፣ በክረምትና በበጋ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን መስራት ችሏል የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ የእሁድ ገቢያዎችን ከመፍጠርና ከማስፋፋት፣ የህብረት ስራ ማህበራት አቅርቦትና ስርጭትን የምርቶችን ተደራሽነት ከማረጋገጥ አንፃር ሸማቹን ማህበረሰብ በቀጥታ ማገናኘት የሚችል የእሁድ ገበያ 18 የነበረው ወደ 20 ማሳደግ በሸማች ህ/ስራ ማህበራት አምራቾችን ጨምሮ በተለያዩ ግብይቶች እና የገበያ ትስስር 9,539,494.72 ( ዘጠኝ ሚሊየን አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ አራት መቶ ዘጠና አራት )ብር ማድረስ ተችሏል በህብረት ስራ ማህበራት በኩል የድጎማና የግብርና ምርቶች ስርጭትን አስመልክቶ በበጀት ዓመቱ 14,463 ኩንታል የግብርና ምርት፣ 54,756 ኩንታል ስኳር ፣ 901,723 ሊትር ዘይት፣ 4,629 የድጎማ ስንዴ ዱቄት ማሰራጨት ተችሏል በከተማ ግባርና በኩል የክፍለ ከተማችን ነዋሪ ባለዉ አነስተኛ ቦታ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የከተማ ግብርና ስራ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የነዋሪዉን የቤተሰብ የምግብ ፍጆታ እንዲሸፍን ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል