Events

Spread the love

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላት የማጠቃለያ ፕሮግራም በደማቅ ሁኔታ ተከበር

ነሀሴ 25/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን

የክፍለ ከተማው ባህል ኪነ-ጥብና ቱሪዝም ፅ/ቤት በሀገራችን በሰሜኑ ክፍል የሚከበረውን የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላትን ባህላዊ ቱፊቱን በጠበቀ ሁኔታ በድምቀት አክብሯል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ባህል ኪነ-ጥብና ቱሪዝም ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አለሙ ኢምሮ የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓላት መከበር ዓላማ የማህበረሰብን የአንድነት ግንባታ ማበልፀግና እሴቶቻችን ለቀጣይ ትውልድ በማሻገር የሀገርን ባህላዊ፣ ቱፊታዊ እና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማስቀጠል፣ ማህበረሰቡ ትክክለኛ እሴቱን እንዲረዳ ለማድረግና በህዝቦች መካከል ወንድማማችና እህትማማችነትን ለማጠናከርና ለማጎልበት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ እና ሶለል በዓል አመጣጥ ባህላዊና እምነታዊ ጉዳዮች ያሉ ሲሆን ከቀደምት ልደተ ክርስቶስ ጀምሮ የክረምቱን መውጣትና የበጋውን መምጣት አያይዞ የሚከበር ሲሆን ሴቶች በቡድን ሆነው ወገባቸው ላይ የአሸንዳ፣ ሻደይ፣ አሽንድዬ ተክል አስረው አደባባይ ላይ በነፃነት እየሚጨፍሩ የሚያከብሩት በዓል ነው፡፡

በዓሉም በክፍለ ከተማ ደረጃ በተለያዩ ኩነቶች የተከበረ ሲሆን በሴት ልጃ ገረዶች ልዩ ልዩ ውዝዋዜ እና የባህል አለባበስ ደምቆ ተከብሯል።