የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ
አዋጅ ቁጥር _________/2013
ነሐሴ 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
አዋጅ ቁጥር 00/2013 ዓ.ምRead More
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 00/2013
የከተማው አስተዳደር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስትና በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 (እንደተሻሻለ) የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በተሟላ መልኩ መወጣት የሚያስችለው የአደረጃጀት ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የከተማው አስተዳደር ለነዋሪው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በእኩልነት፣ በግልጽነትና በፍትሀዊነት መርህ መሰረት ለመስጠት እንዲችል የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት በተገቢው ማደራጀት በማስፈለጉ፤
በሀገራችን ብሎም በከተማችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ዘላቂና ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ (1) (ሀ) መሰረት ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
- አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት፤ ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር——– /2013 ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
- ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-
- “ከተማ” ማለት የአዲስ አበባ ከተማ ነው፤
- “የከተማው አስተዳደር” ማለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው፤
- “ከንቲባ” ማለት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 (እንደተሻሻለ) አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ (3) የተመለከተውና በቻርተር አዋጁ አንቀፅ 21 የተመለከቱት ስልጣንና ተግባር ያሉት የከተማውን አስተዳደር የሚመራ ዋና ስራ አስፈፃሚ ነው፤
- “ቻርተር” ማለት የተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 (እንደተሻሻለ) ነው፤
- “ካቢኔ” ማለት በከንቲባው አቅራቢነት በከተማው ምክር ቤት የሚሾሙ አባላት ያሉት አስፈጻሚ አካል ነው፤
- “የከተማ ስራ አስኪያጅ” ማለት በቻርተሩ አንቀፅ 24 የተመለከቱት ስልጣንና ተግባር ያሉት ነው፤
- “ክፍለ ከተማ” ማለት በቻርተሩ አንቀፅ 2 ንዑስ አንቀፅ (5) የተመለከተው የከተማው ሁለተኛ ደረጃ የአስተዳደር እርከን ነው፤
- “ወረዳ” ማለት የክፍለ ከተማ አካል የሆነ የከተማው ሶስተኛ ደረጃ የአስተዳደር እርከን ነው፤
- “የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅና የክፍለ ከተማ ቋሚ ኮሚቴ” ማለት እንደቅደም ተከተላቸው በቻርተሩ አንቀጽ 34 ፣ 36 እና 37 የተመለከቱት አካላት ናቸው፤
- “የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የወረዳ ቋሚ ኮሚቴ፣ የወረዳ ስራ አስኪያጅ” ማለት በቻርተሩ አንቀፅ 38 ንዑስ አንቀፅ (2) የተመለከቱት አካላት ናቸው፤
- “ቋሚ ኮሚቴ” ማለት በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ በዋና ስራ አስፈጻሚ አቅራቢነት በክፍለ ከተማ ወይም በወረዳ ምክር ቤት የሚሾሙ አባላት ያሉት የከተማ አስተዳደሩን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ህጎችና እቅዶችን የሚያስፈጽም አካል ነው፤
- ሌሎች ትርጉሞች ካቢኔ በሚያወጣው የአሰራርና አደረጃጀት ደንብ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡
- የጾታ አገላለጽ
በዚህ አዋጅ ውስጥ በወንድ ፆታ የተደነገገው የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡
ክፍል ሁለት
ስለ አስፈፃሚ አካላት
ዘርፍ አንድ
ስለአደረጃጀት
- አደረጃጀት
በቻርተሩ የተደነገገው አደረጃጀት እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማውን ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ሕጎች የሚያስፈጽሙ አስፈጻሚ አካላት፡-
- ከንቲባ፤
- ምክትል ከንቲባ፤
- ካቢኔ፤
- የከተማ ስራ አስኪያጅ፤
- የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ፤
- የክፍለ ከተማ ቋሚ ኮሚቴ፤
- የወረዳ ዋና ስራ አስፈጻሚ፤
- የወረዳ ቋሚ ኮሚቴ፡፡
ዘርፍ ሁለት
ስለከንቲባ፣ ስለምክትል ከንቲባ፣ ስለካቢኔ፣ ስለከተማ ሥራ አስኪያጅ
- ስለከንቲባ
በቻርተሩ አንቀጽ 21 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከንቲባው፡-
ሀ. ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለእርሱ የሆኑ አስፈፃሚ አካላትን በበላይነት ይመራል፤ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
ለ. ለስራው ቅልጥፍና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከስልጣኑ በከፊል ለምክትል ከንቲባ፣ በቀጥታ ለራሱ ተጠሪ ለሆነ ኃላፊ ወይም አስፈፃሚ አካል በውክልና ሊሰጥ ይችላል፤
ሐ. በአስፈፃሚ አካላት ወይም በኃላፊዎቻቸው የተሰጡ ውሳኔዎች፣ የወጡ መመሪያዎችና የተሰጡ ትእዛዞች ህግን የሚፃረሩ መሆናቸውን ሲያረጋግጥ ይሽራል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እንዲስተካከሉ መመሪያ ይሰጣል፡፡
- ስለምክትል ከንቲባ
የምክትል ከንቲባ ተጠሪነት፣ ስልጣንና ተግባር በቻርተሩ አንቀፅ 22 የተመለከተው ይሆናል፡፡
- ስለካቢኔ
የካቢኔው ሥልጣንና ተግባራት በቻርተሩ አንቀፅ 23 የተመለከተው ይሆናል፡፡
- ስለካቢኔ አባላት
- የካቢኔው አባላት የሚከተሉት ናቸው፡-
ሀ. ከንቲባ፣
ለ. ምክትል ከንቲባ፣
ሐ. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ከተራ ቁጥር 3 እስከ 20 የተቋቋሙትን አስፈፃሚ አካላት የሚመሩ
ኃላፊዎች፣
መ. እንደ አስፈላጊነቱ በከንቲባ የሚሰየሙ ሌሎች አባላት ይኖሩታል፡፡
- የካቢኔ አባል በካቢኔው ስብሰባ ላይ ሊገኝ በማይችልበት ጊዜ ምክትሉ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ምክትሎች ሲኖሩ በሹመት ቅድሚያ ያለው ወይም በግልጽ ተለይቶ ውክልና የተሰጠው በካቢኔው ስብሰባ ላይ በምትክ አባልነት በመገኘት ይመክራል፤ ድምፅ ይሰጣል፡፡
- ስለካቢኔ የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት
የካቢኔው የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ መሰረት ይወሰናል፡፡
- ስለከተማ ስራ አስኪያጅ
በቻርተሩ ስለ ከተማ ስራ አስኪያጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማ ስራ አስኪያጅ፡-
ሀ. ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለእርሱ የሆኑ አስፈፃሚ አካላትን በበላይነት ይመራል፤ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
ለ. ለስራው ቅልጥፍና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከስልጣኑ በከፊል ለምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ በቀጥታ ለራሱ ተጠሪ ለሆነ ኃላፊ ወይም አስፈፃሚ አካል በውክልና ሊሰጥ ይችላል፤
ስለአስፈፃሚ አካላት መቋቋምና ተጠሪነት
የሚከተሉት አስፈፃሚ አካላት በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁመዋል፤
- ጽህፈት ቤት፤
- ጽህፈት ቤት፤
- ደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፤
- ጽህፈት ቤት፤
- ደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን፤
- ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፤
ሀ.የደንብ ማስከበር ኤጀንሲ
ለ.የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
1.አግባብ ባለው ህግ ፖሊስ ኮሚሽኑ ተጠሪነት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲዛወር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኮሚሽኑን በበላይነት ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤
2.በዚህ አንቀጽ ንዑስ (1) የተደነገገው እስከሚፈፀም የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበርና በመቀናጀት ይሰራል፡፡
- ተጠሪ የሆነ ተቋም፤
የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት፤
- ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፤
- ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ፤
- ቢሮ ተጠሪ የሆኑ ተቋማት፤፤
- ቢሮ ተጠሪ የሆነ ተቋም፤
የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ፤
የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር
1. የእያንዳንዱ አስፈፃሚ አካል ኃላፊ፣ እንደአስፈላጊነቱ ምክትል ኃላፊ ወይም ኃላፊዎች፣ ሌሎች አግባብ ያላቸው የስራ ክፍሎችና ለስራው የሚያስፈልጉ ሰራተኞች የሚኖረው ሆኖ ይደራጃል፤
2. አንድ አስፈፃሚ አካል ከሌላ አስፈፃሚ አካል ጋር እንደ አስፈላጊነቱ ደጋፊ ስራ ሂደት አገልግሎቶችን በጋራ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ዝርዝሩ የከተማው ካቢኔው በሚጸድቀው መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በከንቲባው በሚወጣ መመርያ ይወሰናል፤
3. የየክፍለ ከተማው ጽህፈት ቤት ወይም የሌላ አስፈጻሚ የስራ ክፍል፡-
ሀ) በቻርተር አዋጁና በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሰረት ተጠሪነታቸው ለክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ነው፤
ለ) ከከተማው ቢሮ ወይም ሌላ አስፈፃሚ አካል በእቅድ ዝግጅት፣ ክዋኔ ክትትልና ግምገማ በትስስር ይሰራል፤
ሐ) እንደየአግባቡ የሰራተኛ የውስጥ ዝውውር የደረጃ ዕድገት፣ አመዳደብ በሌሎች ቴክኒካዊና ሙያዊ ጉዳዮች በየክፍለ ከተማው በተዋረድ በስራው መስክ ከተደራጀው ጽህፈት ቤት ወይም ሌላ የስራ ክፍል ጋር ቀጥተኛና መደበኛ ግንኙነት በማድረግ ይሰራል፡፡
1. እያንዳንዱ የካቢኔ አባል ተጠሪነቱ ለከንቲባው ሆኖ፡-
ሀ) የሚመራውን አስፈፃሚ አካል ስለሚመለከቱ ስራዎች፣ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና ህጎች አፈጻጸም ተጠሪነቱ ለካቢኔው ይሆናል፤
ለ) ኃላፊ ለሆነበት አስፈፃሚ አካል የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በስራ ላይ ያውላል፤
ሐ) ኃላፊ ለሆነበት አስፈፃሚ አካል በተፈቀደው በጀትና የስራ ፕሮግራም መሰረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል፤
መ) ኃላፊ የሆነበትን አስፈፃሚ አካል ይመራል፤ ይወክላል፡፡
2. የእያንዳንዱ ሌላ አስፈፃሚ አካል ኃላፊ፡-
ሀ) የሚመራውን አስፈጻሚ አካል ስለሚመለከቱ ስራዎች፣ ፕሮግራሞችና ህጎች አፈጻጸም ተጠሪነቱ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12 ለተመለከተው አስፈጻሚ አካል ወይም የስልጣን አካል ይሆናል፤
ለ) ኃላፊ ለሆኑበት አስፈጻሚ አካል የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በስራ ላይ ያውላል፤
ሐ) ኃላፊ ለሆነበት አስፈፃሚ አካል በተፈቀደው በጀትና የስራ ፕሮግራም መሰረት ገንዘብ ወጭ ያደርጋል፤
መ) ኃላፊ የሆነበትን አስፈጻሚ አካል ይመራል፤ ይወክላል፡፡
ክፍል አራት
የአስፈፃሚ አካላት ሥልጣንና ተግባር
- የወል ሥልጣንና ተግባር
እያንዳንዱ አስፈጻሚ አካል፡-
- እቅድን በሚመለከት፡-
ሀ) በሚደርሰው መመሪያ መሰረት ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር እቅዶችን ያዘጋጃል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
ለ) የሚመለከቱትን ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ስራ ላይ ያውላል፤
ሐ) ለዕቅዱ አተገባበር አስፈላጊ የሆኑትን ተግባራት በወቅቱ ይፈፀማል፤ ያስፈጽማል፤
መ) የስታትስቲክስ መረጃዎች ያሰባስባል፤ ያቀነባብራል፡፡
- በስራው መስክ ፖሊሲ ወይም የህግ ረቂቅ ያመነጫል፤ በጀት ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም በስራ ላይ ያውላል፤ ይቆጣጠራል፤ ያስተዳድራል፤
- በስራው መስክ፤-
ሀ) መስርያ ቤቱን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ ደንቦችና መመርያዎች ተግባራዊ
መሆናቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
ሐ) ጥናት ያጠናል፤ ተገቢውን ስልጠና ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
መ) በህግ መሰረት ውሎችንና ስምምነቶችን ያደርጋል፤
ሠ) በህግ መሰረት መመርያዎችን ያወጣል፤ በስራ ላይ ያውላል፤
ረ) ከሌሎች ተቋማት ጋር ሥራዎችን በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ትስስርና ትብብር ያደርጋል፡፡
- ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጡን በቀጣይነት ያዘምናል፤ ተቋማዊ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ያከናውናል፣ የለውጥና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ይፈጽማል፣ ያስፈጽማል፣ ዉጤታማነታቸውን ያረጋግጣል፤
- ስለስራው ክንዋኔ በወቅቱ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፤
- የመስሪያ ቤቱን ድርጅታዊ መዋቅር አግባብ ላለው አካል አቅርቦ ያፀድቃል፤
- የሚያዘጋጃቸው ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የሴቶችንና የወጣቶችን ጉዳይ እንዲያካትቱ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤
- የአካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ የማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እና በደማቸው ውስጥ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያለባቸው ሰዎች በኃላፊነቱ ክልል የእኩል እድል ተጠቃሚና ሙሉ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት አስፈላጊ የሆኑ ሰራተኞችን ይቀጥራል፤ ያዘዋውራል፤ይመድባል፤ ያሰናብታል፤ ያስተዳድራል፤
- ተጠሪ የተደረጉለትን አስፈፃሚ አካላት አፈፃፀም በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤አደረጃጀቶቻቸውን፣ የስራ ፕሮግራሞቻቸውን እና በጀቶቻቸውን መርምሮ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ለሚሰጠው አገልግሎት በህግ ሲፈቀድለት የአገልግሎት ክፍያ ይሰበስባል፤
- እንደየስራ ባህሪያቸው የህብረተሰብ ተሳትፎን በማጎልበት ተጠቃሚ ያደርጋል፤ ከአስተዳደሩ አካላትና ከሌሎች አስፈፃሚ አካላት ጋር አግባብነት ባላቸው ጉዳዮች ላይ በቅንጅትና በትብብር ሥራዎችን ማከናወን ይኖርበታል፤
- የዘላቂ ልማት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ስራዎችን ለማበረታታት ሲፈቀድ ፈንድ ሊያቋቁም ይችላል፤
- በከንቲባው ወይም አግባብ ባለው ተጠሪ ኃላፊ የሚሰጡትን ሌሎች ተያያዥ ተግባራትን ያከናውናል፤
- በዚህ አዋጅ የተመለከቱትንና ሌሎች በህግ የተሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፤
- ለስራው ቅልጥፍና አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከስልጣንና ተግባሩ በከፊል ለሌላ አስፈፃሚ አካል በውክልና ሊሰጥ ይችላል፡፡
- 16. ከንቲባ ጽህፈት ቤት
ጽህፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
1.ለካቢኔ ስብሰባ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን አስፈላጊነት አይቶ ውሳኔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ውሳኔዎቹ
ተግባራዊ መደረጋቸውን ይከታተላል፣ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
2.የካቢኔ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔዎች፣ ውሳኔዎችና ሌሎች ተያያዠ ሰነዶች በሚገባ ተመዝግበው
እንዲጠበቁ ያደርጋል፤
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የደንብ ማስከበር ኤጀንሲን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- በዚህ አዋጅ አንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ (3) (ለ) የተደነገገው እንደተጠበ ሆኖ
ከከንቲባው በሚሰጠው አመራር መሰረት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸንን የዕለት ተዕለት ተግባር ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ያስተባብራል ስለ አፈጻጸሙ ለከንቲባው ሪፖረት ያቀርባል፡፡
- የብሔራዊ የፀጥታና የሰላም ፖሊሲን መሠረት በማድረግ የከተማውን የአስተዳደርና ፀጥታ ጉዳይ ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ከተማ አቀፍ ፖሊሲ ይቀርፃል፤ እስትራቴጂ ይነድፋል፤ ህግ ያመነጫል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
- በፀጥታ ጉዳዮች የከተማው አስተዳደር ዋና የፀጥታ አማካሪ ሆኖ ይሰራል፤ ለፀጥታና ሰላም አስጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ተገቢ የሆነ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም እንደ አግባብነቱ በቢሮው ወይም ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት የእርምት እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የግጭት መንስዔዎችን በጥናት ይለያል፣ ግጭት እንዳይከሰት ይከላከላል፤ ሲከሰትም ባህላዊና ዘመናዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ይፈታል፤
- በከተማው ልዩ ልዩ ሀይማኖትና ቤተ-እምነት ተከታዮች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብነት ካላቸዉ የፌደራልም ሆነ የከተማው አስተዳደር አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
- በግጭት መከላከል፣ አያያዝም ሆነ አፈታት፣ በነዋሪው ደህንነት፣ ሰላም እና ፀጥታ አጠባበቅ ጉዳዮች ዙሪያ አግባብነት ካላቸው የፌደራል፣ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር እና ሌሎች አካላት ጋር የሥራ ግንኙነቶችን ያደርጋል፤ እንደአግባብነቱ ችግሮችን በተናጠል ወይም በጋራ ይፈታል፤
- ህግና ስርዓት መከበሩንና የህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት መጠበቁን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
- ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና በስውር የህዝቡንና የመንግስትን ጥቅም ጉዳት ላይ ለመጣል የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን፣ ቡድኖችንና ድርጅቶችን በመከታተል ነዋሪውንና ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ከጸጥታ አስተዳደር ጋር የተያያዙ ቅሬታ እና አቤቱታዎችን ይቀበላል፤ ይመረምራል፤ እንዳግባብነቱ እራሱ ወይም በተጠሪ ተቋማት ወይም በሌሎች በሚመለከታቸው አካላት ቅሬታዎቹንና አቤቱታዎቹን መልስ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- በፌደራል መንግስት የተመዘገቡ እና ፈቃድና እድሳት የተሰጣቸውን የሀይማኖት ተቋማት እና የብዙሀን ማህበራት ይመዘግባል፤ መረጃ ያደራጃል፤ ህገ-መንግስቱንና ሌሎች ህጎችን አክብረው ስለመስራታቸው ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ ይሰራል፤
- የህግ አስከባሪ አካላት በሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አያያዝና አጠባበቅ፤ በህገመንግስታዊ እና በወቅታዊ ጉዳዩች ዙሪያ አቅማቸውን በመገንባት የህዝብ አገልጋይነት ሚናቸውን እንዲወጡ ያደርጋል፤
- የሌሎች ህጎች ድንጋጌዎችና አሰራሮች እንደተጠበቁ ሆነው የጦር መሳሪያ ፈቃድ በሚመለከት የድጋፍ ደብዳቤ ይሰጣል፤ መረጃ ያደራጃል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
- በከተማው የጦር መሣሪያ አጠቃቀምና አያያዝ በተመለከተ የምዝገባ አፈጻጸምን ይከታተላል፤
- የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ወንጀል፣ የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ የማስተባበር ስራዎችን ይሰራል፤ ተፈጽሞ ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣
- የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት በህብረተሰብ ተሳትፎ ላይ እና በመስፈርቱ መሰረት ስለመከናወኑ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
- የፀጥታ አስተዳደር እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- የፀጥታ ሁኔታ መረጃ ይሰበስባል፣ ያደራጃል፣ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፣ ውጤቱን ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ተግባር ላይ እንዲውል ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤
- የመንግስትና የግል ተቋማትን እና ነዋሪውን በአካባቢያቸው የፀጥታ፣ ሰላም እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚሳተፉበትን ስልት ይቀይሳል፤ ተቋማዊ አደረጃጀት ይፈጥራል፤ ያስተባብራል፤
- በከተማው ክልል ውስጥ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ከሌሎች ባለደርሻ አካላት ጋር በመተባበር የጉዳቱ መጠን እንዳይባባስ አስፈላጊውን ሁሉ ያደርጋል፤ በአደጋው ክልል ውስጥ የሚገኙ ማህበረሰብ አካላት የህይወትና የንብረት ደህንነት እንዲጠበቅ ያደርጋል፤
- የሰላማዊ ሰልፍ፣ በአደባባይ ላይ ለሚከናወኑ የተለያዩ ፕሮግራሞች እና ስብሰባዎች ከንቲባውን ያማክራል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም የአካባቢ ቅጥር ጥበቃ የሚመሩበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ መስፈርት ያወጣል፣ በዚሁ መሠረት ስለመፈጸሙ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የሰላም እና የፀጥታ ምክር ቤት አደረጃጀትና አሰራር አጥንቶ ለከንቲባው ያቀርባል፤ ሲወሰንም ተግባራዊ ያደርጋል፤
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- በሕግ ጉዳዮች የከተማው አስተዳደር ዋና አማካሪና ተወካይ ሆኖ ይሠራል፤
- የከተማውን የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራምን ያቅዳል፤ ያስተባብራል፤ በእቅዱ መሰረት መከናወኑን ያረጋግጣል፤ ይከታተላል፤ ክፍተቶችን እየለየ ድጋፍ ያደርጋል፤
- የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብር ይተገብራል፤ አስፈፃሚ አካላት በዋና ዕቅዳቸው ማካተታቸውን ያረጋግጣል፤ ይደግፋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል፤
- ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ፕሮግራም ይቀርፃል፤ ዕቅድ ይነድፋል፤በሚመለከተው አካል ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ይመራል፤ ያስተባብራል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤
- የከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአስተዳደሩና የነዋሪው መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የከተማው አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚያደርጉትን ውል እንደአስፈላጊነቱ ይመረምራል፤ ሕጋዊነታቸውን ያረጋግጣል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ተገቢው የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል ወይም ይወስዳል፤
- የከተማው አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤትንና እንደአግባቡ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በመወከል በማንኛውም የዳኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ወይም በግልግል ጉባኤ በመቅረብ ክስ ይመሰርታል፣ መልስ ይሰጣል፣ የጣልቃ ገብ፣ የመቃወም እና የይግባኝ አቤቱታ ያቀርባል፤
- የከተማ አስተዳደሩን የህዝብ መብትና ጥቅም ለማስከበር አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በማንኛውም የዳኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ወይም በግልግል ጉባኤ በመቅረብ በስሙ ክስ ይመሠረታል፤ መልስ ይሰጣል፤ የጣልቃ ገብ አቤቱታ ያቀርባል፤ ይግባኝ ይጠይቃል፤
- የተሰጠው ውሣኔ የህዝብንና የመንግስትን ጥቅም የሚጐዳ ሆኖ ካገኘው የመቃወም አቤቱታ ያቀርባል፤ ይከራከራል፤
- የአስተዳደሩ ተቋማት ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ የክርክር ጉዳዮችን ወክሎ ይከራከራል፤ ያስወስናል፤ ያስፈጽማል፤
- በከተማው አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በእርሳቸው ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጪ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሣኔ ይሰጣል፣ በውሣኔ መሠረት መፈፀሙን ይከታተላል፤
- በካቢኔው በሚፀድቅ ወይም በፀደቀ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት የራሳቸው የሕግ አገልግሎት እንዲኖራቸው የተፈቀደላቸው አካላትን የህግ አገልግሎቶች በሚመለከት ወቅታዊ ሪፖርት እንዲቀርብለት ያደርጋል፤ የጉዳይ አያያዛቸውን ወይም ስራቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ይቆጣጠራል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
- በሌሎች ሕጐች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በፍርድ ቤት የተያዙ ወይም ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት የማያዋጡ ወይም ለአላስፈላጊ ወጪ የሚዳርጉ ጉዳዮችን በአማራጭ ክርክር መፍቻ ዘዴዎች እንዲፈቱ ያደርጋል፤
- በከተማው ውስጥ ለሚኖሩ አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች ነፃ የህግ ምክር ድጋፍ ይሰጣል፤ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- በዐቃቢያን ሕግ የሚሰጡ ውሣኔዎች በሕግ መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ ጉድለቶችን በጥናት አስደግፎ ይለያል፤ በግኝቱ መሠረትም እንዲታረሙ ያደርጋል፤ አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የሕግ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤ የከተማው አስተዳደር ያወጣቸው ሕጎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ይጠብቃል፤ የሕግ ወይም የውል ረቂቅ ያዘጋጃል፤
- ነዋሪው በሕገ መንግስቱና በቻርተሩ የተሰጡትን መብቶችና ነጻነቶች እንዲያውቅና እንዲጠቀም ተገቢውን የሕግ ስልጠና ይሰጣል፤
- ለከተማው አስፈጻሚ አካላትና የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሰራተኞች የንቃተ ሕግ ስልጠና ይሰጣል፤
- ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ከሚመለከተው አካል ወይም በህግ በውክልና የሚሰጡትን የወንጀል ጉዳዮች ይከራከራል፤ ያስወስናል፤ ያስፈጽማል፤
- በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የደንብ መተላለፍ ጉዳዮችን በከተማው ፖሊስ ተጣርቶ ሲቀርብለት ወይም እንዲቀርብለት በማድረግ ክስ ይመሰርታል፣ ይከራከራል፤ የተጀመረ ምርመራ በሕግ መሠረት እንዲቆም ያዛል፤ ክስ ያነሣል ወይም የምርመራ መዝገቡ በሕጉ መሠረት ይዘጋል፤ ሌሎች ሕጋዊ ተግባራትን ያከናውናል፤
- በከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የሚጣሉ የደንብ መተላላፍ ቅጣቶችን ያስፈፅማል፤ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
- በካቢኔ የጸደቀ ደንብ በአዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ያሳትማል፤ የከተማው ሕጎችን መሰብሰብ ማደራጀት መተንተንና ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፤ ይፈጽማል፤
- የከተማው አስተዳደር የሚሰጣቸው አስተዳደራዊ ውሣኔዎች ከሕግ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ ምክር ይሰጣል፤
- በቻርተር አዋጁ በተሰጠው ስልጣን መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶችና ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ስልጣን ስር በሚወድቁ የወንጀልና የደንብ መተላፍ ጉዳዮችን፣ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን በሚመለከት ወንጀል ምርመራ በከተማው ፖሊስ ኮሚሽን ተጣርቶ ሲቀርብለት ወይም እንዲቀርብለት በማድረግ በህግ መሠረት ቀርቦ ተገቢውን ውሳኔ እንዲያገኙ ክስ ያቀርባል፣ ይከራከራል፣
- የተጀመረ ምርመራ በህግ መሠረት እንዲቆም ያዛል፣ ክስ ያነሳል ወይም የወንጀል ምርመራ በህግ መሠረት ይዘጋል፣ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፤
- የቢሮውን ዓቃብያነ-ሕግ ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ መሰረት ይቀጥራል፣ይሾማል፣ያስተዳድራል ፡፡
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የአዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲትዩትን በበላይነት ያስተባብራል፣ ይመራል፤
- የተቋም አቅም ግንባታ ስራን የሚያሳልጡ ዘመናዊ አሰራሮችንና ተሞክሮዎችን በመለየት በከተማ አስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል፣ አስፈላጊዉን የቴክኒክና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
- በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የልማት ድርጅቶች የሰዉ ሀብት ልማት በቀጣይነት የሚለማበትና ጥቅም ላይ የሚዉልበትን ስርዓት ይዘረጋል፤
- የተቋማት አደረጃጀት ጥናት ላይ አስፈላጊዉን ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤ አግባብነት ይመረምራል፣ ያጸድቃል፤
- የከተማ አስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባራት ጥናት ያካሂዳል፤ ለካቢኔዉ ያቀርባል፣ ሲጸድቅም ተገቢዉን ይፈጽማል፤
- በአስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተገቢዉ ስታንዳርድ መኖሩን ይለያል፤ እንዲያዘጁ ያደርጋል፤ ያጸድቃል፤ ተግባራዊ መደረጉን ያረጋግጣል፤
- በአስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ አፈጻፀም ይከታተላል፣ የተገልጋዩን እርካታ ምዘና ስርዓት ይዘረጋል፣ አፈጻፀሙን ይከታተላል፣ ከፍተትን መሰረት ያደረገ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
- የመንግስት ሰራተኞች ቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለዉ መንገድ መዘርጋቱንና ተግባራዊ መደረጉን እና ዉጤታማነቱን ያረጋግጣል፤
- ያልተማከለ የአስተዳደር ስርዓት ለማጠናከር የሚያስችል የማስፈጸም አቅም ግንባታ ይዘረጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤
- የመንግስት ሰራተኛውን ወቅታዊ አፈፃፀም ምዘና የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል፤
- መንግስት ሰራተኛዉ በብቃትና በአፈጻፀም ላይ የተመሰረተ የምደባ፣ የደረጃና የእርከን ጭማሪ፣ የጥቅማጥቅምና የማበረታቻ ስርዓት ይዘረጋል፣ እንዲተገበር ያደርጋል፤ ዉጤታማነቱን ይገመግማል፣ አስፈላጊዉን የማሻሻያ እርምጃ ይወስዳል፤
- የአስተዳደሩ ሰራተኞች የስነምግባር መከታተያ ስርዓት እንዲዘረጋ ይደረጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- ለመንግስት ሰራተኛዉ የሚያስፈልጉ የስራ መደቦች፣ የትምህርት የስልጠናና የስራ ልምድ አጠቃላይ መመዘኛዎች ያወጣል፤
- የአስተዳደሩን የመንግስት ሰራተኞች አቀጣጠር፣ አመዳደብ፣ የደረጃ እድገት፣ ዝዉዉር፣ አበልና ጥቅማ ጥቅም፣ ስልጠናና ዲሲፕሊን በህግ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
- በህግ መሰረት የከተማ አስተዳደሩን የመንግስት ሰራተኞችን ከጡረታ ዕድሜ ክልል በላይ በአገልግሎት ላይ ለማቆየት በሚቀርብ ጥያቄ ላይ ዉሳኔ ይሰጣል፤
- የከተማ አስተዳደሩን የሰዉ ሀብት መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ያደራጃል፤
- ብቃትና የህዝብ አገልጋይነት አስተሳሰብ ያለዉ አመራርና ፈጻሚ እንዲገነባ ይሰራል፣ የብቃት ማረጋገጫ ስርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ይደግፋል፤ ያረጋግጣል፤
- ቢሮው በሚዘረጋቸው አዳዲስ አሰራሮች፤ አደረጃጀቶችና ማኑዋሎች ዙሪያ አጫጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ እንዲሰጥ ያደርጋል፣
- ሁሉም ተቋማት ዉጤታማ አፈጻፀም እንዲኖራቸዉ የሚያደርጋቸዉን አዳዲስ አሰራሮችን በራሳቸዉ ሴክተር ባህርይ በማፈላለግ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ያበረታታል፤ ይደግፋል፤ ይከታተላል፤
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል:-
- የመንግስት ሕንጻና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣንን እና የመንግስት የግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲን ያስተባብራል፤ በበላይነት ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤
- በከተማው አስተዳደር አካላት ተዘጋጅቶ የሚቀርብለትን የበጀት ጥያቄ እና የክፍለ ከተሞችን የበጀት ድልድል መርምሮ የተጠቃለለ ዓመታዊ በጀት በማዘጋጀት ያቀርባል፤ ሲፀድቅም በህግ መሰረት ያስተዳድራል፤
- የፊሲካል ፖሊሲ ያጠናል፤ እንዲጠና ያደርጋል፤ ውጤቱንም ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
- ባልተማከለ የበጀት አስተዳደር ሥርዓት መሠረት የክፍለ ከተሞችን የበጀት ድልድል ቀመር አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ ለክፍለ ከተሞች የሚሰጠውን የበጀት ድጎማ በትክክል ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤
- በገቢዎች ቢሮ የሚሰበሰበውን፣ በብድርና በእርዳታ የሚገኝ ገቢ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ገቢዎችን ያስተዳድራል፤ በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤
- የግብር እና የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ የታሪፍ ማሻሻያ እንዲሁም አዳዲስ የገቢ ምንጭ ጥናት በማዘጋጀት እና/ወይም እንዲዘጋጅ በማድረግ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
- አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ከሀገር ውስጥ ምንጮች በከተማ አስተዳደሩ ስም ይበደራል፤
- የቴክኒክ፣ የማቴሪያልና የገንዘብ ድጋፍ ከዕርዳታ ሰጪ አገሮች፤ (ከተሞች) እና ድርጅቶች ያፈላልጋል፤ ያስተባብራል ውል ይፈርማል አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የከተማውን የሂሳብ አያያዝ ሥርዓት፤ የክፍያና የውስጥ ኦዲት ሥርዓት ይዘረጋል፤ የአፈጻጸሙን ውጤታማነት ይከታተላል፤ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል፤
- ለመንግስት መስሪያ ቤቶች የሂሳብና ገቢ ደረሰኞች፣ ቅጻቅፆች፣ መዛግብቶች ያሳትማል፤ እንዲታተም ያደርጋል፤
- ለካፒታል ፕሮጀክቶች የተመደበው በጀት በአግባቡ መፈጸሙን ይከታተላል፤ ይገመግማል፤
- ከከተማው አጠቃላይ ሃብት ጋር የተጣጣመ የመካከለኛ ዘመን የወጪ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ያቀርባል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚያቀርቧቸው ፕሮጀክቶችን ተቀብሎ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ያበለጽጋል፤ ያፀድቃል፤ ውል ይፈራረማል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የከተማው አስተዳደር ዓመታዊ ሒሳብ አጠቃልሎ ይይዛል፤ በዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ያስመረምራል፤ በግኝቱ ላይ ተመስርቶ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱን ያረጋግጣል፤
- የከተማው የግዥና የንብረት አስተዳደር ስርዓት ይዘረጋል፤ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፤
- የውስጥ ኦዲት በሴክተር መሥሪያ ቤቶች፣ በክፍለ ከተሞችና በወረዳዎች እንዲቋቋሙ ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
- የውስጥ ኦዲት መመሪያዎች፣ ማኑዋሎችና የሙያ ሥነ-ምግባር ደንብ በማዘጋጀት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ የኦዲት ሪፖርቶችን ተቀብሎ ይገመግማል፤ የተገኙ ድክመቶች እንዲታረሙ ያደርጋል፤
- የከተማ አስተዳደሩ የልማት ድርጅቶችን የኮርፖሬት አስተዳደርና የፋይናንስ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የልማት ድርጅቶቹን መነሻ ካፒታል እንዲፀድቅ ያደርጋል፤ እንዲቀንስ፤ እንዲጨምር ለሚመለከተው አካል የውሳኔ ሀሳብ በማቅረብ እንዲወሰን ያደርጋል፤
- እያንዳንዱ የልማት ድርጅት የተፈቀደ ካፒታል መጠን የሚከፈልበትን አሰራር ይዘረጋል፤ የመጠባበቂያ ሂሳቦች እንዲያዙ ያደርጋል፤
- ከተጣራው ትርፍ ውስጥ በየዓመቱ ለከተማ አስተዳደሩ ፈሰስ ሊደረግ የሚገባውን መጠን አግባብ ባለው ህግ ይወስናል፤
- የውጭ ኦዲተሮችን ይሰይማል፤ የልማት ድርጅቱን የሂሳብ ሪፖርትና የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ያፀድቃል፤
- በእያንዳንዱ የልማት ድርጅት ገንዘብ ወጪ የሚደረግበትንና ሽያጭም ሆነ ግዢ በመመሪያ ይወስናል፤
- የከተማ አስተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ባለቤትነት ለማዛወር የሚያስፈልጉ ሰነዶችን ያዘጋጃል፤ ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመቀናጀት የዝውውር ሂደቱን ያሳልጣል፤
- የከተማ አስተዳደሩን አክሲዮኖች፣ የሚተላለፉና የማይተላለፉ የገንዘብ ሰነዶች እና ሌሎች ተመሳሳይ ተቀማጭ የገንዘብ ሀብቶችን ይይዛል፤ ይጠብቃል፤
- የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የከተማ መዋቅራዊ ፕላን እና ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላኖች መሰረት በማድረግና ፍትሃዊና ኢኮኖሚያዊ የመሬት ልማትና አቅርቦት እንዲሁም የከተማ ማደስ ጥናት ስራዎችን ያከናውናል፤ እንዲከናወን ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የልማት ቅደም ተከተል በማውጣት የመልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጥናት፣ መርሀ ግብሮች፣ ጥቅል ዓላማዎች፣ ግቦች፣ የኢንቨስትመንት ዕቅዶች፣ በጀት፣ የዓላማ ማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎችና የጊዜ ሠሌዳ ያዘጋጃል፤ ሲጸደቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ለመልሶ ማልማትና ለመሬት ዝግጅት ተፈላጊውን መሰረተ ልማት እንዲጠና ለሚመለከታቸው ያሳውቃል፤ መጠናቱን ያረጋግጣል፤ ከገንቢዎች በሚገኝ ግብዓት የግንባታ ቅንጅት እቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድም ያስገነባል፤
- የመሬት አቅርቦትና ፍላጎት ሚዛኑን ጠብቆ መሄድ እንዲችል የተለያዩ ጥናቶችን በማከናወን የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ለልማት የተመረጡ አካባቢዎች በአካባቢ ልማት ፕላኑ መሰረት የተቀናጀ የከተማ ንድፍ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በሚመለከተው አካል ሲጸደድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች የሚውል መሬት ወሰን ያስከብራል፤ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤
- በከተማው ውስጥ የተጎዱና ያረጁ አካባቢዎችን ለማደስ እንዲቻል የካሳ ክፍያ ስርዓት ጥናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያከናውናል፤ በየጊዜውም እንዲሻሻል ያደርጋል፤ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ ሁኔታ ስታንዳርዱን ጠብቆ መልሶ ማልማት የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፤
- ለግንባታ ተረፈ ምርት መድፊያነት አገልግሎት የሚሰጡ ቦታዎችን ከልሎ ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፈቃድና ቁጥጥር ቢሮ ያሳውቃል፤ ያስተዳድራል፤ በተሰጠው ፈቃድ መሰረት በተገቢው የተደፋ መሆኑን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ለልማት ተነሺዎች የምትክ ቤት ፍላጎትን ያጠናል፤ የምትክ ቤት መቀበያ ሰርተፊኬት ይሰጣል፤ ለሚመለከተው ያሳውቃል፤ ሲፈቀድም ለተነሽዎች ምትክ ቤት ድልድል በማድረግ እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤ ያረጋግጣል፤
- ለልዩ ልዩ የልማት ስራዎች የለማ መሬት፣ በይዞታነት ለማንም አካል ያልተላለፉ የተዘጋጁና ያልተዘጋጁ ቦታዎችን፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት፣ ባንክ የተደረጉ ክፍት መሬቶችን ወይም ይዞታዎችን ይመዘግባል፤ በዲጂታል እና በፕላን ፎርማት ተገቢውን መረጃ ይይዛል፤ የቦታውንም አገልግሎት ደረጃ እና አስፈላጊ መግለጫዎችን የያዘ የመለያ ሰሌዳ ይተክላል፤ ለህገወጥነት እንዳይጋለጡ ይከላከላል፤
- በከተማው አስተዳደር ወሰን ክልል ውስጥ ያለውን የመሬት ሃብት ኦዲት ያደርጋል፤ በኦዲት ግኝቱ መሠረት ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የይዞታ እና የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገቦ ለመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ እስኪተላለፍ ጥበቃ ያደርጋል፤ የቦታ ይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
- በካርታ በተደገፈ መልኩ የከተማ ቦታ ደረጃ፣ የሊዝ መነሻ ዋጋ እና አማካይ የሊዝ ዋጋ ጥናት ያካሂዳል፤ ወቅታዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በከተማ ክልል ወስጥ ለልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች የለማ መሬትን በመመዝገብ ወጥ የሽንሻኖ ቁጥር ይሰጣል፤ በጨረታ እና በምደባ የሚተላለፉ ቦታዎችን ይለያል፤ ቦታው ለተጠቃሚ እስከሚተላለፍ ድረስም የመከላከልና የመጠበቁን ሥራ ያከናውናል፤
- መሠረተ ልማት ተሟልቶላቸው የተዘጋጁ የከተማ ቦታዎች ለአልሚዎች የሚተላለፉበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ ለአልሚዎች የሚተላለፉ ቦታዎችን አግባብነት ይመረምራል፤ አግባብ ባለው ህግ መሬት ያስተላልፋል፤ ቦታውን በመስክ ያስረክባል፤ በሊዝ ህግና ዉል መሠረት ክፍያ ይሰበስባል፤
- አግባብ ባለው ህግና የሊዝ ውል መሠረት ግንባታ መከናወኑን ያረጋግጣል፤ በሕግና በውል በተወሰነው ጊዜና ሁኔታ መሬቱ መልማቱን ያረጋግጣል፤ መሬቱ ካለማ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- ለጊዜያዊ መጠቀሚያነት አገልገሎት የሚሰጡ ቦታዎችን በጊዜያዊነት በሊዝ ያስተላልፋል፤ የውል ጊዜያቸው ወይም አገልግሎታቸው ሲያበቃም በመረከብ እና ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤
- ለልማት ይዞታቸውን የሚለቁ ባለይዞታዎች ከመልቀቃቸው በፊት አግባብ ባለው ህግ መሰረት የይዞታ ማስለቀቅ ሂደቱን ይተገብራል፤ የተነሽዎችን ዝርዝር እና መረጃ ለአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ያስተላልፋል፤
- የልማት ተነሺዎች ከመነሳታቸው ቀደም ብሎ አግባብ ባለው ሕግ የምትክ ቦታ፣ ቤት፣ ተመጣጣኝ ካሳ እና ሌሎች ክፍያዎች ማግኘት የሚችሉበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ ለልማት በሚለቀቀው መሬት ላይ ላለው ንብረት በህግ መሠረት ካሳ ይተምናል፤ እንዲተመን ያደርጋል፤ የካሳ ክፍያ ይፈጽማል፤ ምትክ ቦታ ያዘጋጃል፤ምትክ ቦታ ያስተላልፋል አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- ለመሠረተ ልማት አውታር፤ ለመናፈሻ፣ ለአረንጓዴ ልማት እና ለሕዝብ መሰብሰቢያ ፕላዛዎች በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ቦታ ያዘጋጃል፤ ያስተላልፋል፤ የይዞታ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
- ለልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች ሊያገለግሉ የሚችሉ የማዕድን ማውጫ ቦታዎች በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ከልሎ ይይዛል፤ ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሚሰጥ የማዕድን ማዉጫ ፈቃድ መሠረት በጊዜያዊነት መሬቱን በሊዝ ያስተላልፋል፤ የቦታዎቹ ጠቀሜታ ሲያበቃም ተከታትሎ በመረከብ ለዳግም ልማት ያዘጋጃል፤
- የመሬት ይዞታ እና የቤት አጠቃቀም ዓይነትና የባለይዞታዎች መረጃዎች ይይዛል፤ ይጠብቃል፤ አግባብ ባለው ህግ ለህጋዊ ባለይዞታዎች የቦታ አገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎች መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሠረት የቦታ ኪራይና የቤት ግብር ተመን አስልቶ ለሚመለከተው አካል በወቅቱ ያስተላልፋል፤
- ከካሳ ጉዳይ በስተቀር ለግብር ሰብሳቢ ተቋማት፣ ለፍርድ ቤቶችና ለሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግምት አገልግሎት ይሰጣል፤
- በህግ የሚቀመጠውን የአሰራር ስርአት ተከትሎ እና በከተማ አስተዳደሩ ለሚፈቀድላቸው፣ ለሰነድ አልባ ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይሰጣል፤ ማህደራቸውን ያደራጃል፤
- መደበኛ የይዞታ አገልግሎቶችን ያከናውናል፤ አፈጻጸሙንም ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፤ከፖሊስና ከህግ ውጪ የሆኑ የይዞታ አስተዳደር አፈፃፀም ሲከሰት የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፡፡
- በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ መብት ላልተፈጠረላቸው ባለይዞታዎች በሚወጡ ህጎችና አሰራሮችን መሰረት ባደረገ ሁኔታ የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ መረጃም ያደራጃል ለሚመለከተው ሪፖርት ያቀርባል፡፡
- 22. የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፡-
- አገራዊ የቤቶች ልማትና አስተዳደርን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ዝርዝር የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም ስታንዳርድ በከተማዋ ተፈጻሚ ያደርጋል፤
- የሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የስትራቴጂያዊና ዓመታዊ የፊሲካልና የፋይናንሻል ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ያዳብራል፤ በሚመለከተው አካል አጸድቆ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በቤት ልማት ፖሊሲውና ስታንዳርድ መሰረት የሚከናወኑ የቤት ልማት ስራዎች በጥራትና በጊዜው የሚጠናቀቁበት የቁጥጥርና ክትትል ስርዓት ይዘረጋል፤ ይተገብራል፤
- አዳዲስ የቤት ልማት ቴክኖሎጂዎችን እና የአሰራር ዘዴዎች አማራጮች ያጠናል፤ ሲፈቀደም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የጋራ መኖሪያ ቤቶችንና ንግድ ቤቶችን ለማስተላለፍ፣ ለማከራየትና ለማስተዳደር እንዲሁም ሌሎች የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበራት፣ የግል ቤት አልሚዎች እና ሪል ስቴቶችን ለመምራት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ፣ ስልትና ስታንዳርድ ያዘጋጃል፣ ይተገብራል፤ የመኖሪያ ቤት አይነቶችን መደብና ደረጃ ያወጣል፤
- የጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት እንዲመሠረቱና በህግ አግባብ ተልዕኳቸውን እንዲወጡ ያበረታታል፤ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራ አደረጃጃት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በማጥናት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
- በአነስተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎች በተለይም ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና የልማት ተነሺዎች በቤት ልማት ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- የቤት ልማቱ ስራ ከድህነት ቅነሳ እና ከስራ እድል ፈጠራ ጋር የተቀናጀ እንዲሆን ያደርጋል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
- የቤት ፍላጎትና አቅርቦት መለየት የሚያስችል ዝርዝር ጥናት ያከናውናል፤ የቤት አቅርቦት ክፍተቶችን መሙላት የሚያስችል የመፍትሔ ኃሳቦችን ያመነጫል፤ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ ሲወሰን ይተገብራል፤
- የቤት ፍላጎት፣ አቅርቦት እና አጠቃላይ የቤት መረጃ በዝርዝር ይይዛል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት ነዋሪ ከአቅሙ ጋር የተመጣጠነ መኖሪያ ቤት እንዲሠራ፣ የከተማዉ አስተዳደርና የግል ባለሃብቶች በአጋርነት የቤት ልማት ማካሄድ የሚችሉበት አጠቃላይ አቅጣጫ ለመቀየስ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካሂዳል፣ ሥርዓት ይዘረጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- በበጎ አድራጊ ወይም በሌላ የከተማውን ህብረተሰብ የቤት ችግር ለመቅረፍ የሚሰሩ የቤት ልማቶች በከተማው አጠቃላይ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ፕሮግራም ጋር የተጣጣሙና የተቀናጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
- ለቤቶች ግንባታ የሚያስፈልገውን ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤
- የሚገነቡ ቤቶችን ስፔስፊኬሽን እና የስራ ዝርዝር ያዘጋጃል፤ የታይፖሎጂ ዲዛይንና ዝርዝር ዲዛይን እንዲሰራ ያደርጋል፤ የተዘጋጁ ዲዛይኖችን ከግንባታ ሳይቶች ጋር የማጣጣም ስራ ይሰራል ወይም እንዲሰራ ያደርጋል፤
- አግባብ ባለዉ ህግ መሠረት የፕላን ስምምነትና የግንባታ ፈቃድ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ በማቅረብ ያስፈጽማል፤ ይረከባል፤
- ለጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ የሚያስፈልገውን የለማ መሬት ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ያቀርባል፤ ሲፈቀድ ይረከባል፤
- ለቤቶቹ ልማት የሚያስፈልገውን ገንዘብ በከተማ አስተዳደሩ ዋስትና ከአበዳሪ ባንክ ወይም ከሌላ ህጋዊ የፋይናንስ ተቋም ይበደራል፤ በቤት ልማት ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለመሆን የተመዘገቡና በባንክ የሚቆጥቡ ነዋሪዎችን ቁጠባ ለመጠቀም የብድር ወለድ ምጣኔውን በተመለከተ ከባንኩ ጋር ድርድር ያደርጋል፤
- ከአበዳሪው ባንክ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ወቅታዊና መሠረታዊ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፤ ከባንክ የተገኘው ብድር፣ ቤቶቹ ሲተላለፉ የተገኘው ገቢ፣ የተመለሰው የብድር መጠን እና ወለድ በተመለከተ ለሚመለከተው አካል ያሳዉቃል፤
- ግንባታውን የሚያከናውኑ አማካሪዎችንና ስራ ተቋራጮችን አግባብ ባለው ህግ መሠረት ይመዘግባል፤ ይመለምላል፤ የቤቶች ልማትን ማካሄድ የሚያስችሉ ውሎችን ያዘጋጃል፤ ይዋዋላል፤ ውሉንም ያስተዳድራል፤
- የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በተገባው ውል መሠረት፣ የጥራት ደረጃ፣ በተወሰነው ዋጋና የጊዜ ገደብ መሠረት መሠራቱን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤ ግንባታቸው ሲጠናቀቅ ርክክብ ይፈጽማል፤ በውሉ መሰረት ባልተፈጸሙ፣ በሚታዩ ጉድለቶችና ጥፋቶች ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- ለግንባታና ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚያስፈልገውን መሠረተ-ልማት እንዲሟላ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ያቀርባል፤ መሟላቱን ያረጋግጣል፤
- ግንባታው ሲጠናቀቅ ለሚመለከተዉ አካል የመጠቀሚያ ፈቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀርባል፤ ፈቃዱን ይረከባል፤
- ግንባታቸው ተጠናቆ የመጠቀሚያ ፈቃድ ያገኙ የመኖሪያ ቤቶችን በማስተላለፊያ ዋጋቸው ለተጠቃሚዎች በዕጣ ወይም በምደባ ያስተላላፋል፤ የቤቶቹን አስፈላጊ ሰነዶች በሙሉ ቤቱ ለደረሳቸው ባለመብቶች በወቅቱ ያስረክባል፤
- በሚገነቡ የጋራ ህንጻዎች ለንግድ አገልግሎት የሚውሉትን ቤቶች በጨረታ ይሸጣል፤
- የከተማ አስተዳደሩ ንብረት የሆኑ የመኖሪያ፣ ንግድና ሌሎች ቤቶችን ያስተዳድራል፤ ቤቶችን በህግ መሠረት ያከራያል፤ የተለያዩ አማራጭ የኪራይ ተመን ያጠናል፤ ሲጸድቅ ይተገብራል፤ ወርሃዊ የቤት ኪራይ መሰብሰቡን ይከታተላል፤
- በከተማው አስተዳደር ባለቤትነት ስር ያሉ ቤቶችን ያስተዳድራል፤ ለቤቶቹ ጥገናና እድሳት ያደርጋል፤
- አጠቃላይ በከተማው ውስጥ ያሉ ቤቶችን መረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይይዛል፤
- የከተማው አስተዳደር ባለቤትነት ስር ያሉ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ከያዙት አካላት ያስለቅቃል፤
- በከተማ አስተዳደር ባለቤትነት ስር ያሉ ቤቶች በልማት ምክንያት በሚፈርሱበት ወቅት አስፈላጊውን መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይለያል፣ ያጣራል፣ አግባብነት ላለው አካል ያስተላልፋል፤ አግባብ ባለው የአስተዳደሩ አካል ምትክ ቤት እንዲሰጥ ሲወሰን ሂደቱን በማጣራትና በማረጋገጥ በህጉ መሠረት እንዲስተናገዱ ያደርጋል፤
- ኢ-መደበኛ የሆኑ ቤቶችን መረጃ ይሰበስባል፤ በመደበኛው የቤቶች ልማት ፕሮግራም ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ በማጥናት የውሳኔ ሃሳብ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
- በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት ምትክ ቤት ለሚሰጣቸው ነዋሪዎች አግባብ ባለው የከተማ አስተዳደሩ ውሳኔ መሠረት ጉዳዩን አጣርቶ እንዲስተናገዱ ያደርጋል፤
- የግል መኖሪያ ቤት ያላቸው ነዋሪዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመለየት ከጋራ መኖሪያ ቤት እጣ ውጪ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ ቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲና አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣንን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- የትራንስፖርትና ትራፊክ አመራርና አስተዳደር ሥራ በበላይነት ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤ ለአገልግሎቱ ሥልጠት የሚያግዝ ስልት ይቀይሳል፤ ይተገብራል፤
- የትራንስፖርት ማስተር ፕላን ያዘጋጃል፤ የትራንስፖርት አቅርቦት ፍላጎት ያጠናል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የከተማዋን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ይገነባል፤ ያስፋፋል፤ ይጠግናል፤ ከሌሎች የከተማው መስረተ ልማት አውታሮች ጋር የተናበቡ መሆናቸውን ይከታተላል፤
- የተቀናጀ የህዝብ፣ ደረቅና ፍሳሽ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር የሚያግዙ የከተማ ትራንስፖርት ደንብ፣ መመሪያ፣ ደረጃዎች፣ መመዘኛዎች እና የአሰራር ሥርዓቶች ያዘጋጃል፤ ሲጸድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
- የአየር ብክለት የሚቀንሱና ለአየር ንብረት ምቹ የሚሆኑ የትራንስፖርት ዓይነቶችን መጠቀምን ለማበረታታት የሚያስችሉ መመሪያ በማውጣትና ተግባራዊነቱን በመከታተል ከተማዋን ከብክለት ይከላከላል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
- የከተማውን የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ማለትም ለህዝብና ለጭነት ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ መናኽሪያዎችን፣ ፌርማታዎችን፣ መጋዘኖችና ዴፖዎችን ይገነባል፤ ያስተዳድራል፤
- የከተማውን የትራንስፖርት አቅርቦትና ፍላጎት በመለየት፤ የህዝብና ደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ስምሪት ስርዓት ይዘረጋል፤ አዳዲስ የትራንስፖርት መስመሮችን ይከፍታል፤ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
- የከተማውን የተማከለ የብዙሃን፣ የጭነትና ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች የኦፕሬሽን ሥርዓታቸውን በበላይነት ይቆጣጠራል፤ ይመራል፤ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያግዳል፤ የሥምሪት ድልድል ያዘጋጃል፤ ታሪፍ አጥንቶ ለሚመለከተዉ አካል ያቀርባል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ለሕብረተሰቡ ተደራሽ የሆነ የትራንስፖርት መረጃ አገልግሎት ያደራጃል፤ ያሰራጫል፤ የከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት በቅንጅት እንዲሰሩ ዕቅድ ያወጣል፤
- በትራንስፖርት አገልግሎቱ ውስጥ የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍ የሚያበረታታ ሥርዓት ይዘረጋል፤ የትራንስፖርት ማህበራትን ያደራጃል፤ ያሉትም እንዲጠናከሩ ያደርጋል፡፡
- የከተማውን የብዙሃንና የጭነት ትራንስፖርት መመዘኛ መስፈርቶች፣ ማንዋሎችና ደረጃዎች ያወጣል፤ ለተፈፃሚነቱ ይሰራል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በብዙሃንና በጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ የሚሰሩ ኦፕሬተሮች፣ ማኅበራት፣ ድርጅቶችና ግለሰቦችን ያደራጃል፤ እንዲጠናከሩ ያደርጋል፤ ለከተማው ትራንስፖርት ቅልጥፍናና ደህንነት መሥራታቸውንም ያረጋግጣል፡፡
- የትራንስፖርት ደንቦች መከበራቸውን ቁጥጥር ያደርጋል፤ ህግና ደንብ የሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤
- የህዝብን ደህንነት የሚጎዱ ተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ አግባብ ባለው ህግ መሰረት በመከታተል ያግዳል፡፡
- የትራንስፖርትና ትራፊክ አመራርና አስተዳደር ሥራ በበላይነት ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤ ለአገልግሎቱ ሥልጠት የሚያግዝ ስልት ይቀይሳል፤ ይተገብራል፤
- የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፡-
- ከየተቋማቱ የሚቀርበውን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የሚገነቡ የመንግስት ህንጻዎች የስትራቴጂያዊና ዓመታዊ የፊሲካልና የፋይናንሻል ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ ያዳብራል፤ በሚመለከተው አካል አጸድቆ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የሚገነቡ ህንጻዎች የታይፖሎጂ ዲዛይንና ዝርዝር ዲዛይን እንዲሁም ስፔስፊኬሽን እና የስራ ዝርዝር ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ የተዘጋጁ ዲዛይኖችን ከግንባታ ሳይቶች ጋር የማጣጣም ስራ ይሰራል ወይም እንዲሰራ ያደርጋል፤
- የግንባታ ፕሮጀክት አዋጭነት ጥናት ያካሄዳል፣ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የፕላን ስምምነትና የግንባታ ፈቃድ ከሚመለከተው አካል ያወጣል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የስራ ተቋራጭ፣ የዲዛይንና የግንባታ ሱፐርቭዥን አማካሪ ጨረታ ሰነድ ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ አግባብ ባለው ህግ መሠረት ጨረታውን ያወጣል፤ አሸናፊውን ይለያል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የመንግስት ህንጻ ግንባታ በተገባው ውል መሠረት፣ የጥራት ደረጃ፣ የጊዜና የዋጋ ገደብ ተጠብቆ መሠራቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል የቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል፤ በበላይነትም ይቆጣጠራል፤
- የከተማ አስተዳደሩን ወክሎ የህንጻና ተመሳሳይ የግንባታ ስራዎችን አግባብ ባለው ህግ መሰረት ውል ይፈጽማል፤ ኮንትራት ያስተዳድራል፤ ግንባታው ሲጠናቀቅም በውሉ መሰረት መከናወኑን አረጋግጦ ይረከባል፤ ህንጻው ወይም ግንባታው ለተከናወነለት ተቋም በሰነድ ያስረክባል፤
- ለግንባታና ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚያስፈልገውን መሠረተ-ልማት እንዲሟላ ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ያቀርባል፤ መሟላቱንም ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤
- ግንባታው ሲጠናቀቅ ቢሮው ለሚመለከተው አካል የመጠቀሚያ ፈቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀርባል፤ ፈቃዱን ይረከባል፤
- በውሉ መሰረት ባልተፈጸሙ፣ በሚታዩ ጉድለቶችና ጥፋቶች ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
- የክህሎት፣ ካይዘን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ማሰልጠኛ ኮሌጆችንና ማዕከላትን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
- የከተማዋን የክህሎት፣ ኢኖቬሽን፣ቴክኖሎጂ እና የካይዘን እንቅስቃሴዎችን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- የተቋሙን ተልዕኮ ሊሳኩ የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን ያካሄዳል፤ እንዲካሄዱ ያደርጋል፤ ያስተዋውቃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አሠልጣኞች እና ቴክኒሺያኖችን የክህሎት ክፍተት በመለየት በክህሎትና በቴክኖሎጂ ብቃት ለማሳደግ አጫጭር ስልጠና የሚያገኙበትን ሥልት ይቀይሳል፤ ተግባራዊ ያድርጋል፤
- መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞችና የግል አመልካቾች የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የሚያገኙበትን አሰራር ይዘረጋል፤
- በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ መሰማራት የሚፈልጉትን የግል ባለሀብቶች ይደግፋል፤ መንግስታዊ ከሆኑ እና ካልሆኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ጠንካራ ግንኙነት ይፈጥራል፤
- የኢንተርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ምርታማነት ተወዳዳሪነት የሚያጎልብትበት አገር በቀል ቴክኖሎጂዎች እንዲሰራ ያደርጋል፤ የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን ይደግፋል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፡፡
- የሀገሪቱን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስትራቴጂና መርሃ ግብር ለማስፈፀም የሚያስችል የአሰራር ሥርዓቶችን ይዘረጋል፤ ተግባራዊነታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በአገር አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጁ የሙያ ደረጃዎች በከተማው ውስጥ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- ማሰልጠኛ ተቋማት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተሟላ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ድጋፍ እንዲሰጡ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይቆጣጠራል፤ ይከታተላል፤
- .በቴክኖሎጂ ምርምር በእሴት ሰንሰለት ትንተና እና በተለያዩ የአመራርና የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ ዙሪያ ከከፍተኛ ት/ት ተቋማትና ከዘርፍ ኢንስቲቲዮቶች ጋር ትስስር እንዲፈጠር ያደርጋል፤በጋራ ይሰራል፡፡
- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት ያላቸውና ሌሎች ትኩረት የሚሹ ዜጎች ትኩረት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ በዚህ ረገድ የሚቀየሱ አገር አቀፍ ሥርዓቶች በከተማው ውስጥ ተግባራዊ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤
- የማሰልጠኛ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች የሚመደቡበትን የአሰራር ስርዓት አግባብ ባለው ህግ መሠረት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የቴክኒክና ሙያ ምሩቃን በሙያቸው ተደራጅተው ወደ ሥራ በሚገቡበት ጊዜ ያላቸውን የሙያ ክፍተት በመለየት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በየደረጃው ሙያዊ እገዛ እንዲደረግላቸው አስፈላጊውን የሥራ ትብብር ያደርጋል፤
- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናን አስመልክቶ ለሕብረተሰቡ የተለያዩ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረኮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል፤ ያስተባብራል፤ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች እንዲሰጡ ያደርጋል፡፡
- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማሰልጠኛ ተቋማት ከአገር ውስጥና ከውጪ ከሚገኙ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር አግባብ ባለው መንገድ መሰረት ግኑኝነት በመፍጠር ልምድ እንዲለዋወጡ፣ እንዲተጋገዙ ያደርጋል፡፡
- የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተደራሽነትና ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ያደረጋል፤ይከታተላል፤ይደግፋል፡፡
- በመንግስትና በግል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለሚሰማሩ ወይም ፕሮግራም ለሚያስፋፉ በስታንዳርዱ መሰረት ያላቸውን ዝግጅት ሱፐርቪዥን በማካሄድ ይገመግማል፤ ጉድለቶቻቸውን እንዲያርሙ አቅማቸውን ይገነባል፤ ዕውቅና ለሚሰጠው አካል መረጃ ይሰጣል፤ይቀበላል፤ብቃታቸውን ለማሳደግ ይሰራል፡፡
- በከተማ ደረጃ የቴክኖሎጂ ምርምርና ሽግግር፣ የኢንኩቤሽን፣ የክህሎት፣ የብየዳ፣ የሥራ ፈጠራ ማዕከላትን ያደራጃል፤ ይመራል፤ ያስተባብራል፤ በመካከላቸው የምርምርና የፈጠራ ክህሎት ውድድር በማዘጋጀት ዘርፉን ያበረታታል፡፡
- የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የኮምፒውተር መረቦችና አፕሊኬሽኖች እንዲቀናጁና እንዲናበቡ ያደርጋል፤ ያረጋግጣል፤
- የአስፈፃሚ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለማዘመን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል፤ ቀጣይነቱን ያረጋግጣል፤
- የከተማ አስተዳደሩን ተቋማት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ክፍተትን ይለያል፤ አስፈላጊ መስፈርቶችን በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ይዘረጋል፤ እንዲዘረጋም ያደርጋል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በከተማዋ የተዘረጉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና አስተማማኝነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን የሚያስችሉ ደረጃዎችን ይወስናል፣ ተግባራዊ መደረጋቸውን ይቆጣጠራል፤
- የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም በከተማ አስተዳደሩ የሚሰጡ አገልግሎቶች ከተማ አቀፍ የመረጃ ቋት ያደራጃል፤ ያስተዳድራል፤ ቀጣይነቱን ያረጋግጣል፤
- ደረጃ አውጥቶ ወይም በወጣው ደረጃ መሰረት ሃርድዌርና ሶፍትዌር ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ለከተማው አስተዳደር ተቋማት ያቀርባል፣ ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤ በዚህ መልኩ ለሚያዘጋጃቸው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስም ይሰጣል፤ ስለአጠቃቀሙ ተቋማቱን ያማክራል፤
- ለኢኖቬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ለፈጠራ ሥራዎች ዕድገት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት ሽልማትና ማበረታቻ የሚሰጥበትን ሥርዓት ይዘረጋል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፤
- በከተማ አስተዳደሩ ባሉ ተቋማት የካይዘን ፍልስፍናን በማስተግበር አሰራራቸዉን አዘምነዉ ቀልጣፋና ዉጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ እና ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ የሚያስችል የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፣ ይከታተላል፤ ቀጣይነት ያለዉ መሻሻል መኖሩን ያረጋግጣል፤
- በግል አምራች ድርጅቶች የካይዘን ፍልስፍናን እንዲተገብሩ ተገቢ የሚሆኑ ተቋማትን በትብብር ይለያል፣ የግንዛቤና ሙያዊ ስልጠናዎችን ይሰጣል፣ የሙያ ድጋፍ ያደርጋል፤
- በቴክኖሎጂ ምርምር፤ በእሴት ሰንሰለት ትንተና እና በተለያዩ የአመራርና የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ ዙሪያ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትስስር እንዲፈጠር ያደርጋል፤በጋራ ይሰራል፡፡
- የንግድ ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- የንግድና ገበያ ልማት ተወዳዳሪነትን በቀጣይነት የሚያረጋግጡ ከተማ አቀፍ ፖሊሲዎችን ይቀርፃል፤ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የከተማው የምርት ውጤቶች እንዲታወቁ ያደርጋል፤ አውደ-ርዕይ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ይሳተፋል፤ ፈቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤
- የአገር ውስጥ ባለሃብቶች በከተማው ውስጥ በንግድና ገበያ ልማት ስራ ላይ በሰፊው እንዲሰማሩ ያበረታታል፤ የቴክኒክና የምክር አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ በንግድ ስራ ለሚሰማሩና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለሚያቋቁሙ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች የንግድ ፍቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤
- በከተማው ውስጥ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እንዲቋቋም ያበረታታል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤
- የከተማውን የንግድ መዝገብ ያቋቁማል፤ የንግድ ስም ምዝገባ ያከናውናል፤ ያስተዳድራል፤ የንግድ ማህበራትን በህግ መሠረት በመመዝገብ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ያግዳል፤ ይሰርዛል፤
- የዋስትና መያዣ በሕግ መሠረት በንግድ መዝገብ ይመዘግባል፤ ይሰርዛል፤ ለሃራጅ ሽያጭ አፈጻጸም የሚረዱ ስራዎችን በሕግ መሰረት ያከናውናል፤
- የገበያ ማዕከላት ያለማል፤ ደረጃ ያወጣል፤ ደረጃቸውን የጠበቁ የገበያ ማዕከላት መገንባታቸውን ይቆጣጠራል፤ የሚስፋፉበትንና የሚያድጉበትን ስልት ይቀይሳል፤
- በከተማው ውስጥ የመሠረታዊ ንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ስርጭት የገበያ ህግና ስርዓትን መከተሉን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ለገበያ የሚቀርቡ ምርቶችና አገልግሎቶች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ጊዜ ያለፈባቸው ምርቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲወገዱ ያደርጋል፤
- የፍጆታ ምርቶችን የአገልግሎት ዘመንና የተዘጋጁባቸውን ንጥረ-ነገሮች ይዘት ሸማቹ ማወቅ በሚችልበት ሁኔታ መሆኑን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በገበያው ውስጥ በቂ አቅርቦት መኖሩንና ግዥና ሽያጩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ያረጋግጣል፤ ለነጻ ገበያ ውድድር እንቅፋት የሆኑ ድርጊቶችና ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ስራዎች እንዳይፈጸሙ በመከላከልና በማስወገድ የከተማውን ነዋሪዎች ጥቅም ያስጠብቃል፤
- የገበያ ዋጋ መረጃ የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና የማቀነባበር ተግባራትን ያከናውናል፤ እንዳስፈላጊነቱ በጥቅም ላይ ያውላል፤
- የልኬት መሳሪያዎችንና መስፈሪያዎችን ትክክለኛነት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤ ትክክለኛ ሆነው ያልተገኙ የልኬት መሳሪያዎችንና መስፈሪያዎችን እንዲወገዱ ያደርጋል፤
- ለገበያ አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ቦታዎችን ይቆጣጠራል፤ ያስተዳድራል፤ የአገልግሎት አስጣጡን በተመለከተ መመሪያ ያወጣል፤
- ኢ-መደበኛ ንግድ ወደ መደበኛ ስርዓት የሚገባበትን አሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
- ሕገ-ወጥ ንግድን ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡
- የኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የኢንተርኘራይዞችንና የኢንደስትሪ ልማት ለማፋጠን የሚረዱ ተቋማዊ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ፕሮጀክቶችን፣ የድጋፍ ማዕቀፎች፣ መመሪያዎችንና እቅዶችን ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በከተማው ውስጥ የሚገኙትን ነዋሪዎች አምራች ዜጋ ለማድረግ የሚያስችሉ አዳዲስ የስራ ዕድል አማራጮችን ይለያል፣ ያጠናል፣ ያስጠናል፣ ፕሮጀክት ፕሮፋይል ያዘጋጃል፣ የአዋጭነት ጥናቶችን ያጠናል፣ ያስተዋውቃል፣ ወደ ስራ እንዲገቡ ያበረታታል፤
- የኢንተርኘራይዞች የኢንደስትሪዎች የሥራ ፈላጊዎችንና የስራ ገበያ መረጃ ይመዘግባል፤ መረጃ ይሰበስባል፣ ይተነትናል፣ ያደራጃል፣ይተነትናል ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
- ለሥራ ፈላጊዎች ለኢንተርፕራይዞችና ኢንደስትሪዎች በሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ፣ አሰራርና የድጋፍ ማዕቀፎች ላይ ግንዛቤ ይፈጥራል፤ አፈፃፀሙን እየተከታተለ ድጋፍ ያደርጋል፤
- የኢንተርኘራይዞችና ኢንደስትሪዎች የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ያቋቁማል፣ ያስተባብራል፣ ይቆጣጠራል፤
- ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎችን በንግድ ህጉ እና አግባብ ባለው ሌላ ህግ መሰረት ያደራጃል፤ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
- ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ በአግባቡ ማካሄድ የሚያስችላቸው የብድር፣ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤ የመስሪያና መሸጫ ቦታ ይሰጣል፤ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፣ ከታለመለት ዓላማ ዉጭ ጥቅም ላይ ዉሎ ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ያስወስዳል፤
- በኢንተርኘራይዝና ኢንደስትሪ ልማት ለተሰማሩ አንቀሳቃሾችና አምራቾች የሙያ ማበልፀጊያ ስልጠናዎች እና አውደ ርዕዮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤
- የኢንተርኘራይዞችና ኢንደስትሪዎችን የገበያ ችግር ለመቅረፍ ከተለያዩ አካላት ጋር የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው ያደርጋል፤ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ በውጭ ሀገር በሚካሄዱ ኤግዚቢሽንና ባዛሮች እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ለተወዳዳሪነታቸው እንቅፋት የሆኑ ጉዳዩችን በጥናት በመለየት መፍትሔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ለይቶ ያጠናል፣ ይቀምራል፣ ያስተገብራል፣ ውጤታማነቱን ይከታተላል፤
- የኢንተርፕራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች እርስ በእርስ በግብዓት አቅርቦት፣ በምርትና በቴክኖሎጂ ትስስር እንዲፈጥሩ ያደርጋል፤ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር የገበያ ትስስር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- ኢንተርኘራይዞችና ኢንደስትሪዎች ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ከጥናትና ምርምር ተቋማት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ይሰራል፣
- ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የመረጃ፣ የቴክኖሎጂ መረጣ፣ የድርድር፣ የግንባታ፣ የኮሚሺኒንግ ድጋፍ ይሰጣል፤ ውጤቱንም ይገመግማል፤
- ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የመረጃና የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፤
- የኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም የደረጃ እና የጥራት ሰርቲፊኬሽን እንዲያገኙ ድጋፍ ያደርጋል፤
- ኢንተርኘራይዞችንና አምራች ኢንደስትሪዎች ከጥቃቅን ወደ አነስተኛ፤ ከአነስተኛ ወደ መካከለኛና ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ እንዲሸጋገሩ ያደርጋል፤
- ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ተወዳዳሪ ለማድረግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የማበረታቻ፣ የዕውቅና እና ሽልማት ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች በዘርፍ ማህበራት ያደራጃል፤ ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል፤
- የኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት በቀጣይነት ሊያሣድጉ የሚችሉ የአቅም ግንባታ እና ችግር ፈቺ የጥናት ስራዎችን ያከናውናል፤ እንዲሁም የሰራተኞች የስራ ላይ ደህንነት፤ የአካባቢ ጥበቃና የኢንዱስትሪ ሰላም የሚያስጠብቁ ተግባራትን ያከናውናል፣
- ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች አስፈላጊ የሆነ የሰለጠነ የሰዉ ኃይል እና የግብዓት አቅርቦት አስተማማኝ በሆነ መልኩ ለማሟላት የሚያስችል ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
- ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ነባር የመስሪያ ቦታ የሆኑ ህንጻዎች፣ ሼዶች፣ ተለጣፊ ሱቆች እና ኮንቴነሮች እንዲሁም በመንግስት፣ በግልና በተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የተገነቡ መደብሮችን ያስተዳድራል፤ ይከታተላል፤
- ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ማምረቻ፣ ማሳያ እና መሸጫ ሼድና ህንጻ በኢንደስትሪ መንደሮች፣ በክላስተር ማዕከላትና በገበያ ማዕከላት ማስገንባት እንዲችል ከሚመለከተው አካል የለማ መሬት ይረከባል፤ ካርታ የሌላቸው ነባር ይዞታዎች ካርታ እንዲሰራላቸው ያመቻቻል፤ የተገነቡትን ያስተላልፋል፤ ያስተዳድራል፤
- ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ማምረቻ፣ ማሳያ እና መሸጫ ሼድና ህንጻ በኢንደስትሪ መንደሮች፣ በክላስተር ማዕከላት፣ በገበያ ማዕከላት እና በኢንፖሪየም ማዕከላት በማደራጀት እንዲገነቡ ያደርጋል፤ እድሳትና ጥገና እንዲደረግላቸው ያደርጋል፤ የመሠረተ ልማት አውታሮችም እንዲሟሉላቸው ይደግፋል፤ ይከታተላል፤
- ነባር እና አዲስ የመስሪያ ቦታ ማዕከላት ስታንዳርድ እና ዝርዝር የአፈጻጻም መመሪያ ያወጣል፣ ይተገብራል፣ ይቆጣጠራል፤ በወጣው መመሪያ መሰረት ለኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች በኪራይ ያስተላልፋል፤ ኪራይ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤
- መስራት እየቻሉ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት ሥራ ሳይኖራቸው በከፋ ድህነት ላይ የሚኖሩ የከተማ ነዋሪዎችን መረጃ ይመዘግባል፤ ይለያል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፤ ሲፈቀድለትም በማህበረሰብ አቀፍ ልማት ስራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- ከማህበረሰብ አቀፍ ልማት ስራዎች የተጠቃሚነት ጊዜያቸው ሲያበቃ የማስመረቅ ስራ ይሰራል፤ በዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሥራ ቦታ ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል፤ የወል የሥራ ክርክሮች እና የኅብረት ስምምነት ድርድር ልዩነቶች በመግባባት እልባት እንዲያገኙ ያደርጋል፤ የህብረት ስምምነቶችንና ማሻሻያቸውን ይመዘግባል፤
- በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሥራ ቦታ ሰላም እንዲሰፍን የትምህርትና የሥልጠና አገልግሎት ይሰጣል፣ የሙያ ምክር አገልግሎት ስለሚስፋፋበት፣ ክፍት የሥራ መደቦች ስለሚመዘገቡበትና ሥራና ሠራተኛ ስለሚገናኙበት ዘዴ ይቀይሳል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤
- አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር በከተማው ውስጥ በሥራ ላይ ስለተሰማራውና ሥራ አጥ ስለሆነው የሰው ኃይል፣ ስለሙያ መደብ፣ የከተማውን የስራ ሰምሪት እንዲሁም የሙያ አመዳደብ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤ መረጃዎችን ይይዛል፤ የስራ ገበያ መረጃዎች ስርዓት ይዘረጋል፣ ይሰበስባል፣ ያጠናክራል፤ ያሰራጫል፤
- በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ህግ በተደነገገው መሰረት በከተማው ውስጥ የሚደራጁ የአሰሪና ሰራተኛ የሙያ ማህበራትን ይመዘግባል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤ ሲፈርሱ ምዝገባውን ይሰርዛል፤
- አሰሪዎች የስራ ሁኔታን፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነትንና የስራ አካባቢን ለመጠበቅ የወጡ የስራ ሁኔታ ደረጃዎችና የመከላከያ ዘዴዎች በሥራ ላይ ማዋላቸውን ይቆጣጠራል፤
- ሥራና ሠራተኛ ለሚያገናኙ ኤጀንሲዎች የብቃት ማረጋገጫ በህግ መሰረት ይሰጣል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ መሥራታቸውን ያረጋግጣል፤ ይሰርዛል፤
- በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ህግ መሰረት የከተማው አስተዳደር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ እና አማካሪ ቦርድ አባሎችን ይሾማል፤ ያሰናብታል፤ ተግባርና ኃላፊነታቸውን ይከታተላል፤
- የከተማ ነዋሪ ስለውጭ አገር ሥራ ስምሪት እና ህገ ወጥ ዝውውር ተጨባጭ ሁኔታ፤ ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንዲያገኝ የመገናኛ ብዙኃንንና ሌሎች አማራጭ ዘዴዎችን በመጠቀም ቀጣይነት ያለው ከተማ አቀፍ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥራዎችን ያከናውናል፤
- ለስራ ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ፍላጎት ላላቸው ዜጎች ስለተቀባይ አገር ሁኔታ በሚሰማሩበት የስራ መስክ ሊኒራቸወው ስሚገባ ክህሎት፣ስለመብታቸውና ኃላፊነታቸው እና ስለመሳሰሉት ጉዳዩች የቅድመ-ስምሪትና የቅድመ ጉዞ ግንዛቤ ማሰደጊያ ስልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ እና ከግል ድርጅቶች ጋር ትስስር በመፍጠር ኢንተርኘራይዞችና አምራች ኢንደስትሪዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፣ተፈጻሚነቱን ያረጋግጣል፤
- የጤና ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- በከተማው አስተዳደር ባለቤትነት ስር ያሉ ጤና ተቋማትን እና የህክምና ማሰልጠኛ ተቋማትን በሕግ መሠረት ያስተዳድራል፤ ይመራል፤
- የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲና ደረጃ በማገናዘብ የከተማውን የጤና አገልግሎት ደረጃ ያወጣል፤ ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል፤ በጤና ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስፋፊያ ትምህርት ለነዋሪው አመቺ በሆነ ዘዴ ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- አጠቃላይ የሆነ የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥርና ቅኝት ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፤ ይከላከላል፤ መረጃዎችን ያሰባስባል፤ ወረርሽኝ ሲነሳ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይከላከላል፤
- የእናቶችና ህፃናት ጤና ክብካቤ አገልግሎት ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፤
- ከፌደራል መንግሥት እና ከዕርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ለተለያዩ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚሰጡ መድኃኒቶችንና የሕክምና መሳሪያዎችን ያሰራጫል፤ ስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የባህል ህክምና ከዘመናዊ ህክምና ጎን ተጠናክሮ የሚሄድበትን ስልት ይቀይሳል፤
- የጤና አገልግሎት ፕሮግራሞችን ከሚያካሂዱ መንግሥታዊ ያልሆኑ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር ሕጋዊ ስምምነቶችና ውሎች ይፈጽማል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
- የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመግታት የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ይሰራል፤ በደማቸው ቫይረሱ ያለባቸው ወገኖች ድጋፍና ክብካቤ ያደርጋል፤
- በከተማው ውስጥ የሚከናወኑ የኤች አይ ቪ/ኤድስና ሌሎች በሽታዎች ቁጥጥር መረጃ ያጠናቅራል፤ በአግባቡ በመተንተን ለሚመለከታቸው ያቀርባል፤
- በከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ዓመታዊ የስራ ዕቅድ ውስጥ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዕቅድ መካተቱን ይከታተላል፤
- የኤች አይ ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚንቀሳቀሱ አካላትን ያስተባብራል፤ የሥራ ቅንጅት እንዲኖር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- የጤና አጠባበቅ የምክርና የመረጃ አገልግሎት ያደራጃል፤ ይሰጣል፤
- መንግስታዊ ጤና ተቋማት የሚሰጡትን የሕክምና መረጃዎች ያረጋግጣል፤ ይከታተላል፤ እንደ አስፈላጊነቱም እርምጃ ይወስዳል፤
- በምገባ ኤጀንሲ የምገባ አገልግሎት የሚያገኙ የጤና እክል ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የጤንነት ሁኔታ ይከታተላል፤ ተገቢውን ድጋፍ ይሰጣል፤
- ደረጃውን የጠበቀ የቅድመ ሆስፒታል አምቡላንስ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል፤ በበላይነት ይመራል ያስተዳድራል።
- የትምህርት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የትምህርት ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንዲቻል ትምህርት ቤቶችን ያስፋፋል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እንዲጠገኑ እና መሰረተ ልማታቸው በአግባቡ እንዲሟላ ያደርጋል፤
- የሀገሪቱን የትምህርት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ደረጃ በመጠበቅ የከተማውን አስተዳደር ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤ መደበኛ ያልሆኑ፣ ቅድመ መደበኛ እና መጀመርያ ደረጃ ሥርዓተ ትምህርት ያዘጋጃል፤ መጻህፍት ያሳትማል፤ የትምህርት ግብዓት መሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
- በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚወጣውን መስፈርት መሠረት በማድረግ በከተማው ውስጥ የሚገኙትን ትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- የመምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን የአቅም ግንባታ ስራ ያከናውናል፤
- በከተማው ውስጥ አገር አቀፍ ፈተናዎችን ያስፈፅማል፤ በከተማው ውስጥ በሚገኙ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተዘጋጅተው የሚሠጡ ፈተናዎችንና የምስክር ወረቀቶችን ህጋዊነት ያረጋግጣል፤
- ከተማ አቀፍ የሆኑ ፈተናዎችን ያዘጋጃል፣ ያስፈፅማል፤
- በመገናኛ ዘዴዎች የተደገፉ የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲሰጡ ያደርጋል፤ መደበኛና ኢ-መደበኛ የትምህርት ፕሮግራሞች የሚስፋፉበትን ሁኔታ ይቀይሳል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ለሴቶች፣ ለህፃናት፣ ለጎልማሶችና ልዩ የትምህርት ፍላጎት ላላቸው ዜጎች ለሚሰጡ የትምህርት አገልግሎቶች ልዩ ድጋፍ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚወጡ የብቃት መመዘኛዎች መሠረት መምህራንና ሌሎች የትምህርት ባለሙያዎችን ያሰለጥናል፣ እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፤ ሙያ ድጋፍ ይሰጣል፤
- ትምህርት ቤቶችን ማቋቋምና ማስፋፋት ለሚፈልጉ አካላት የመረጃ አገልግሎትና ድጋፍ ይሰጣል፤
- በከተማው ውስጥ የሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚተዳደሩ ትምህርት ቤቶች የመማርና ማስተማር ሂደት በበላይነት ይመራል፤ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- የስርዓተ ጾታ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- በሁሉም አስፈፃሚ አካላት፣ በመንግስት የልማት ድርጅቶችና ሌሎች የአስተዳደሩ አካላት የስርዓተ ፆታንና ህጻናት ጉዳይ በዕቅዳቸው ላይ ማካተታቸውን ይከታተላል፤ በስርዓተ ፆታ እኩልነት ዙሪያ ግንዛቤና ንቅናቄ እንዲፈጠር ይደረጋል፤
- ሴቶች በከተማው አስተዳደር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት ይሰራል፤
- በከተማ አስተዳደሩ የሚተገበሩ ህጎች የሴቶች፣ የአረጋዊያን፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብትና ደህንነት የሚያስከብሩ መሆናቸውን ይከታተላል፤
- የሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብቶች ስለመጣሳቸው መረጃ ሲደርሰው ከሚመለከተው አካል ጋር ጉዳዩን በማጣራት ውጤቱን ለሚመለከተው የፍትህ አካል ያስተላልፋል፤ ይከታተላል፤
- የሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ህጻናት፣ አረጋውያን እና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አቅም የሚያጎለብቱ ትምህርታዊ፣ ሙያዊና የተጨማሪ ክህሎት ሥልጠናዎችን ያዘጋጃል፤ ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ሴቶች፣አረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች በማህበራት እንዲደራጁ፣ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- ለሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ህጻናት ፣ጎዳና ተደዳደሪዎች እና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መብት፣ ደህንነትና ጥቅም የሚሰሩ ማህበራት እንዲደራጁና እንዲጠናከሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤
- ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሚመለከት ከልማት ስትራቴጂ አኳያ ተቃኝቶ በወጣ ፕሮጀክት ላይ በከተማው ውስጥ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ይመሰርታል፤ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፤
- የሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በሁሉም የተባበረ ጥረት መፍትሄ እንዲያገኝ ያስተባብራል፤ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
- ለሴቶች፣ ህጻናትና አካል ጉዳተኛ ልዩ ትኩረት በመስጠት በሁሉም የልማት ሥራዎች ውስጥ ፍላጎቶቻቸው እንዲካተት ለማድረግ ከተለያየ ጥቃት መከላከል፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞቻቸው ለማስከበር ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
- ሴቶች፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ያላቸውን አቅምና ችሎታ ለህብረተሰቡ ጠቃሚ የሆኑ አገልግሎቶች ለማበርከት የሚያስችላቸው የበጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲያጎለብቱ ያበረታታል፤
- ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች ህጻናትና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ሁኔታ የሚሻሻልበትን ሁኔታ ያጠናል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በየደረጃው ያሉ የሕፃናት አደረጃጀቶችን አቅም በማጎልበት የሕፃናት ተሳትፎ እንዲያድግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል፤
- የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓትን በማጠናከር የነዋሪዎች ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት እና ዋስትና የሚሻሻሉባቸውና የሚጠበቁባቸው አሰራር ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ ጥምረት ምክር ቤቶች እንዲቋቋሙ በማድረግ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በማህበረሰብ አቀፍ የተሀድሶ አገልገሎት እንዲታቀፉ ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤
- በማህበረሰብ አቀፍ ሊታቀፉና ሊደገፉ ያልቻሉ፣ በወንጀል ነክ ድርጊት ውስጥ የተሳተፉ፣ የሱስ ተጋላጭ ህጻናት፣ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞች እና ሰርቶ ለማደር አቅም የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በአስተዳደሩና መንግስታዊ ባልሆኑ ማዕከላት ውስጥ ክብካቤና ድጋፍ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
- የከፋ የምግብ ችግር ያለባቸው ህጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የአዕምሮ ህመምተኞች እና መሰል የህብረተሰብ ክፍሎች ይለያል፣ ይመዘግባል፣ ለምገባ ኤጀንሲ መረጃውን ያስተላልፋል፤
- የምገባ ኤጀንሲ ተጠቃሚዎችን ሁኔታ ክትትል በማድረግ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲቋቋሙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ የተቋቋሙት ከምገባ ፕሮግራሙ እንዲወጡ ዝርዝራቸውን ለኤጀንሲ ያስተላልፋል፤
- በመንግስት በጀት የሚተዳደሩ የቀዳማይ ልጅነት እና የክብካቤ መስጫ ማዕከላትን ያስተዳድራል፤ ያስፋፋል፣ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በከተማው አስተዳደር ተቋማት ውስጥ የህጻናት ማቆያ እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
- የተለያዩ መንግስታዊ አገልግሎቶችን በነፃ ለማግኘት ለሚጠይቅ ሰው ጥያቄውን አጣርቶ የድህነት ማረጋገጫ ማስረጃ ይሰጣል፤
- የማህበራዊ ልማት ፈንድ የሚያስገኝ ፕሮጀክት ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- መስራት የማይችሉና ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተስብ ክፍሎች በሴፍቲኔት ቀጥታ ድጋፍ ማዕቀፍ ውስጥ ተጠቃሚ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ያስተባብራል፤
- በዘላቂ ማረፊያ የሚፈፀሙ የባይተዋር ቀብሮችን መረጃ ይይዛል፤ ያጠናቅራል፤ የቀብር ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤በበጎ አድራጎት ማህበር ወይም ድርጅት ውስጥ ቆይተው በሞት የተለዩ እና ሌሎች የባይተዋር ቀብር ያስፈፅማል፤
- በከተማው ውስጥ ያሉ መሠረታዊ እድር እና በየደረጃው የሚገኙት የእድር ምክር ቤቶችን ይመዘግባል፤ ፈቃድ ይሰጣል፤ ባህላዊና ታሪካዊ እሴታቸው ጠብቀው እንዲሄዱ ድጋፍ ያደርጋል፤ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ያበረታታል፤
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር፣የአዲስ አበባ ትያትርና ባህል አዳራሽ፣ የራስ ቲያትር፣ የሀገር ፍቅር ቲያትርና የህፃናትና ወጣቶች ትያትር ቤቶችን እና የህዝብ ቤተ መፃህፍትን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ያጠናል፤ በሕግ መሠረት ይጠብቃል፤ ያስጠብቃል፤ የሀገሪቱን ብሔር ብሔረሰቦች ታሪክና ባህል ተመዝግቦ እንዲያዝ ያደርጋል፤ የባህል ሙዝየሞችን ያደራጃል፤ ያስተዳድራል፤ ቋንቋዎችና ሥነ ፅሑፎች እንዲዳብሩ ያደርጋል፤
- በባህል ተፅዕኖ ሳቢያ ማህበራዊ ዕድገትን የሚያጓትቱ አመለካከቶችን፣ እምነቶችንና ልማዳዊ አሠራሮችን የመለወጥ ተግባሮችን ያከናውናል፤
- የባህል ዘርፍ ልማዳዊ አስተዋጽኦ እንዲስፋፋ ያድርጋል፤ ባህል፣ ኪነጥበብ፣ ሥነ ጥበብ እና የፈጠራ ችሎታ በከተማው ውስጥ እንዲዳብርና እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ግብረ-ገባዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን የሚያራምዱና የሚያስፋፉ እንቅስቃሴዎችን ይከታተላል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ያደርጋል፤
- በከተማው አስተዳደር ሥር የሚገኙ ቤተ መጽሐፍትን፤ ቤተመዛግብትና አብያተ-መዘክርን ያስተዳድራል፣ ይመራል፤ እንዲቋቋሙና እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ በባህል ዘርፍ የህዝብን ተሳትፎ መሠረት ለማስያዝ ሌሎች የባህል ተቋማት እንዲስፋፉ ያድርጋል፤
- የከተማውን የቱሪዝም መስህቦችና መልካም ገጽታ ለሀገር ውስጥና ለውጪ እህት ከተሞች የቱሪዝም ገበያ በስፋት ያስተዋውቃል፤
- የከተማው የቱሪስት መስህቦችና መዳረሻዎችን ተለይተው እንዲታወቁና ለቱሪዝም አመቺ ሆነው እንዲለሙና እንዲደራጁ፤ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እንዲስፋፉ፣ የከተማው ነዋሪም ከቱሪዝም ጥቅሞች ተካፍይ እንዲሆን ያድርጋል፤
- ለቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሙያ ፍቃድ ይሰጣል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደረጃዎችን ይወስናል፤ ተፈፃሚነቱን ይቆጣጠራል፤
- በቱሪዝም የሰመረ አገልግሎት እንዲኖርና የቱሪስቶችም ደህንነት እንዲረጋገጥ ከሚመለከታቸው ጋር ይሠራል፤
- የቱሪዝም ሴክተር የማስፈፀም አቅም ይገነባል፤
- የባህልና ቱሪዝም መረጃዎችን ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ ያሠራጫል፤
- በከተማው ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የኪነ ጥበብና የቱሪዝም ተቋማትን፣ ማህበራትን፣ ክበባትን፣ ሞያተኞችን በሕግ መሠረት ይመዘግባል፤ ፊቃድ ይሰጣል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ድጋፍ ያደርጋል፡፡
- ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል:-
- ዘመናዊ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ሥርዓት በመዘርጋት ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ይሰጣል፤ ኢንቪስትመንትን ለማበረታታት ለባለሃብቶች የተሰጡ የታክስና የቀረጥ ነጻ መብቶች በህግ አግባብ እንዲፈፀሙ ያደርጋል፤ ለታሰበው ዓላማ መዋላቸውን ይከታተላል፤
- ታክስ ከፋዮች በፈቃደኝነት ታክስ የመክፈል ባሕልን እንዲያዳብሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የታክስ መመሪያዎችን አፈፃፀም ለማሻሻል እና ገቢ በአግባቡ እንዲሰበሰብ ለማድረግ የጥናትና የምርምር ሥራዎችን ያካሂዳል፤
- ለግብር እና ለልዩ ልዩ ገቢዎች አወሳሰን የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ይተነትናል፤ በመስኩ ስለሚፈጸሙ ወንጀሎች የተሟላ የስታትስቲክስ መረጃ ያጠናቅራል፤ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
- በከተማ የሚሰበሰቡ ገቢዎችን ወስኖ፤ ውሳኔዎችን ለግብር ከፋዮች በጽሁፍ ያሳውቃል፤ ብቃት ባለው መልኩ ለማከናወን የሚያስችሉ የአሰራር ዘዴዎችን በመቀየስ ገቢ ይሰበስባል፤
- በተዋረድ ባሉ የቢሮው አደረጃጀት የሚሰበሰቡ ገቢዎች ለፋይናንስ ቢሮ በወቅቱ ፈሰስ ያደረጋል፤
- ግብር ከፋዮች ደረሰኝ እንዲያሳትሙ ይፈቅዳል፤ ይቆጣጠራል፤ አግባብ ባለው ህግ መሰረት የታክስ ህጎችን ያስከብራል፤
- የቀን ገቢ ግምት ጥናት አግባብ ባለው ህግ መሰረት ያከናውናል፤
- አግባብነት ካላቸው አካላትና የከተማ ነዋሪዎች እና ግብር ከፋዮች ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል ስልቶች በመቀየስ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የቢሮው ሠራተኞች ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ መሰረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፡፡
- የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የከተማ አስተዳደሩን የስፖርት ትምህርትና ሥልጠና ማዕከላትን፣ የስፖርት ማዘወተሪያዎች፣ የስፖርት ልህቀት ማዕከላት እና የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላትን ያስተዳድራል፤ እንዲስፋፉና አቅማቸው እንዲገነባ ያደርጋል፤
- በከተማ አስተዳደሩ ህጎች ሲተገበሩ የወጣቶችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም የሚጠብቁ መሆናቸውን ይከታተላል፤ ሁሉም አስፈፃሚ አካላት የወጣቶችን ጉዳይ በዕቅዳቸው ማካተታቸውን ይከታተላል፤ መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
- ለወጣቶች መብት፣ ጥቅም እና ደህንነት የሚሰሩ ማህበራት እንዲደራጁና እንዲጠናከሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤ የወጣት መብት መጣሱን መረጃ ሲደርሰው ጉዳዩን ከሚመለከተው አካል ጋር በማጥናትና በማጥራት የህግ ከለላ ማግኘት እንዲችሉና ተገቢው መፍትሔ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- የወጣቶችን አቅም የሚያጎለብቱ ትምህርታዊ፣ ሙያዊና የተጨማሪ ክህሎት ስልጠናዎችን ያዘጋጃል፤ ያመቻቻል፤ ይሰጣል፤ ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት በተለያዩ በኪነ-ጥበብ በቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ያበረታታል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤
- አግባብ ካላቸው አካላት ጋር በመተባባር ወጣቶች በማህበር እንዲደራጁ፣ የመስሪያ ቦታ እንዲመቻችላቸው፣ የማምረቻ መሳሪያ አቅርቦት፣ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- ወጣቶች በከተማው አስተዳደር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጥምረት ይሰራል፤
- ወጣቱን በመልካም ስነ ምግባር ለማነጽና የሀገር ፍቅር ስሜቱን ለማጎልበት የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል፣ተግባራዊ ያደርጋል
- ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ ያበረታታል፤
- ወጣቶችን በሚመለከት ከልማት ስትራቴጂ አኳያ ተቃኝቶ በወጣ ፕሮጀክት ላይ በከተማው ውስጥ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ይመሰርታል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያቀርባል፤
- የአካል ጉዳትና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት በሁሉም የልማት ስራዎች እንዲሳተፉ፣ ከተለያዩ ጥቃቶች መከላከል፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጥቅሞቻቸው ለማስከበር ከሌሎች አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፤
- የወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን ያቋቁማል፤ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
- ነዋሪው በስፖርት ለሁሉምና በባህላዊ ስፖርት ተሣታፊና ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- ለስፖርት ተግባራት የሚውሉ የስፖርት ትጥቆችና መሣሪያዎች አቅርቦት የሚሟላበትን ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያመቻቻል፤
- አግባብ ባለው ህግ የስፖርት ህክምና አገልግሎት መደራጀቱን፣ በስፖርት አበረታች መድሃኒቶችና ዕፆች መጠቀምን ለመከላከል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፤
- የስፖርት ልማት ፈንድ የሚቋቋምበትን እና ባለሀብቱ በስፖርት ኢንቨስት የሚያደርግበትን ስልት ይቀይሳል ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል
- የስፖርት ማህበራት ያደራጃል፤ የማዘውተሪያ ስፍራ አጠቃቀም የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ የስፖርት ማህበራትንና ክለቦችን እንዲሁም ጅምናዚየሞችን ይመዘግባል፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤
- በሳይንሳዊ ጥናት ላይ የተመሰረቱ የስፖርት ማሰልጠኛ ዘዴዎችን በማዘጋጀት ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች የስፖርት ዳኞችና የመሳሰሉት እንዲሰለጥኑ ያደርጋል፤
- የከተማውን ነዋሪ የስፖርት ተሳትፎ ለማጎልበት ያቅዳል፤ የስፖርት ውድድሮችንና የመዝናኛ ትርዒቶችን ያዘጋጃል፤ ይመራል፤ ከሚመለከተው ጋር በመተባበር የትምህርት ቤቶች የስፖርት ውድድር እንዲስፋፋና እንዲጠናከር ያደርጋል፤
- የአካል ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በስፖርት ያላቸው ተሳትፎ እንዲጎለብት አሰራር ይዘረጋል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በውጭ ኦዲተር የተመረመረ የሂሳብ ሪፖርት ከማህበሩ እንዲቀርብለት በማድረግ የስፖርት ማህበራት ገቢ ለአላማቸው ብቻ መዋሉን ያረጋግጣል፤
- የአስተዳደሩን ስፖርትና መዝናኛ ምክር ቤት በየደረጃው በማቋቋም አግባብ ባለው ህግ አደረጃጀቱን ያጠናክራል፤ ይመራል፤ ይቆጣጠራል፡፡
- የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ከታችኛው የእድሜ እርከን የሚጀምርበት ስልት ይቀይሳል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በከተማ ደረጃ የብዙሃን የአካል እንቅስቃሴ እና የስፖርት መዝናኛ አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ያደርጋል፤ ያስተባብራል፤ ይመራል፤
- የፕላንና ልማት ኮሚሽን
ኮሚሽኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የከተማውን የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ የተቋማትን አፈፃፀም ይከታተላል፤ ግብረ መልስ ይሰጣል፤ ይገመግማል፤ ይመዝናል፤ ደረጃ ያወጣል፤ ሪፖርት ለሚመለከተው ያቀርባል፤
- የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የአካባቢ ልማት ፕላን ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤
- የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፕላን ያዘጋጃል፤ ያፀድቃል፤ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፤
- የፕላን ዝግጅትና አተገባበር የጥናትና ምርምር ሥራዎች ያከናውናል፣ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ያቀነባብራል፤ ያሰራጫል፤
- የሕዝብ ተግባቦትና ስርፀት ስራዎችን ያከናውናል፤ ተደራሽ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመረጃ ስነድና ስርጭት ቋት ያደራጃል፣ ጥቅም ላይ ያውላል፤
- የከተማው አስተዳደር ከተማ ፕላን ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላት ድጋፍና ምክር ይሰጣል፤
- በሚያመነጫቸው ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ ከተማ ፕላን፣ የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያን፣ የሴቶችንና የወጣቶች ጉዳዮች እንዲካተቱ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤
- ከተማ ፕላን በሚጥስ ማናቸውም አካል ላይ በሕግ መሠረት እርምጃ ይወስዳል፤ ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- ከተማ ፕላን ለማዘጋጀት የሚያስችል መሠረታዊ የከተማ ካርታ ከሀገሪቱ ጂኦዳቲክ ካርታ ጋር በተገናዘበ መልኩ ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ያደራጃል፤ ያሰራጫል፤
- የፀደቀ ፕላን በሕግ መሠረት እንደየአግባቡ ያሻሽላል፤ ያጣጥማል፤
- የፕላን፣ የዲዛይንና የግንባታ ፈቃድ ደረጃዎችን አፈፃፀም የሚመለከቱ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ፕላን ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላት እንዲያቀርቡና የመስክ ምልከታ እና ጥናት በማድረግ ሪፓርት ያቀርባል፤
- የከተማውን ዝርዝር የሥነ ህዝብ ጥናትና ትንበያ ያካሄዳል፣ ውጤቱንም ለከተማው አስተዳደር አካላትና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፤ የስነህዝብ ፖሊሲ በከተማው ውስጥ ይፈፅማል፤ ያስፈፅማል፤
- የከተማውን አመታዊ አጠቃላይ የምርት እድገት ለማስገኘት የሚያስፈልገውን የካፒታልና የምርታማነት እድገት መነሻዎችን ይገምታል፤ ውጤቱንም ለሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላትና ለባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፤
- የከተማውን የምርት እድገት ግቦች የፖሊሲና የህግ ሪፎርም እርምጃዎች ጋር የተጣጣሙ የቁጠባ፣ የኢንቨስትመንትና የወጪና የገቢ ንግድ ከተማ አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ግቦችን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤
- ከአጠቃላይ ከተማ አቀፍ ምርት የኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት ዘርፎችና የከተማ ግብርና የተናጠል ድርሻን ይለያል፤ ውጤቱንም ለሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላትና ለባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፤
- የከተማውን በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች መካከል የሚኖረውን የግብዓት አቅርቦት ፍላጎት ይተነትናል፤ ውጤቱንም ለሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላትና ለባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፤
- ለሬዚለንት ስትራቴጂ ትግበራ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ የክልል እና የውጭ ሀገር የግል ዘርፍ አካላት ጋር አጋርነትን ይመሰርታል፤
- ለሁሉም ዘርፎች የሬዚሊየንስ ስትራቴጂ ለማስፈፀም አዋጭ ፕሮጀክቶችን ያሰናዳል፣ ለተፈፃሚነታቸውም ተዛማች የሆነ የገንዘብ ምንጭ መገኘቱንና ለታለመለት ዓላማ መሰራጨቱን ያረጋግጣል፤
- በሬዚሊየንስ አግባብ ፍላጎት መርና ችግር ፈቺ የሆነ ጥናት የተፅእኖ ዳሰሳ ከዩኒቨርሲቲ፣ ከምርምር ማዕከላትና ከሌሎች ትምህርታዊ አካላት ጋር በመተባበር ያከናውናል፤
- ከሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላት ጋር ተከታታይ ምክክር በማድረግ የሚተገበሩ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን እንዲሁም ሊወሰዱ የሚገባቸውን የፖሊሲና የህግ ሪፎርም እርምጃዎችን የሚዘረዝር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ የዘርፍ ፕላን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፤
- ተዋረዳዊ አደረጃጀት ያላቸው የከተማው አስተዳደር አጠቃላይ ፕላን ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ በየበኩላቸው የሚፈፅሟቸውን ተግባራት የሚያሳይ የተቀናጀ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ልማት ፕላን አፈፃፀም መርሀ ግብር ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፡፡
- የኢንቨስትመንት ኮሚሸን
ኮሚሽኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የኢንቨስትመንት አመችነትን ያጠናል፤ ያስተዋውቃል፤ ያስተባብራል፤ ያስፋፋል፤ ምክርና የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
- የእርስ በእርስ ቁጥጥርን ለማረጋገጥ አገራዊ ፋይዳ ያላቸው የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ይገመግማል፤ ለሚመለከተው አካል በማቅርብ እንዲጸድቅ ያደርጋል፤
- የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ሲቀርቡለት በህግ መሰረት መርምሮ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ማግኘት የሚገባቸውን በማረጋገጥ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ የንግድ ወይም ኢንዱስትሪ ፈቃድ ማግኘት እንዲችሉ አግባብ ወዳለው አካል ያስተላልፋል፤
- ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎች፣ የፋይናንስና የብድር አገልግሎቶች፣ የጥሬ ዕቃና የማምረቻ መሳሪያዎች የማግኘት ዕድልና የተለያዩ የመሰረተ ልማት አውታሮች የሚሟሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና ለማበረታታት እንዲሁም የከተማውን መልካም ገጽታ ለመገንባት የሚረዱ የማስተዋወቅ ስራዎችን ይሰራል፤ ጽሑፎችን ያዘጋጃል፤ ያሠራጫል፤ ዓውደ ርዕዮችን፣ ዓውደ ጥናቶችንና ሴሚኖሮችን ያዘገጃል፤
- ኢንቨስትመንትን ለማስፋት በባለሀብቶች፣ በመንግስታዊ መሥሪያ ቤቶችና በሌሎች ኢንቨስትመንትን በተመለከተ አግባብነት ባላቸው አካላት መካከል ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል፤ ያስተባብራል፤
- የኢንቨስትመንት ፈቃድ የሰጣቸውን ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ይከታተላል፤ የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የያዛቸው ሁኔታዎች መከበራቸውንና ማበረታቻዎች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤ ከህግ አግባብ ውጪ ሆነው ሲገኙ የኢንቨስትመንት ፈቃዱን ይሰርዛል፤ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የድህረ-ኢንቨስትመንት የድጋፍና ክትትል ሥራን ለዚህ ዓላማ ከተቋቋሙ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤
- የኢንቨስትመንት ፈቃድ ላወጡ ባለሀብቶች የአንድ መስኮት አገልገሎት የሚያገኙበትን አሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤
- እንደ ኢንቨስትመንቱ ዓይነት ለፕሮጀከቱ የሚያስፈልገውን የመሬት ፍላጎት ገምግሞ የመሬት ዝግጅት እንዲደረግ ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤ አግባብ ካለው አካል ጋር በመቀናጀት ለከተማው አስተዳደር አቅርቦ ያስወስናል፤ ተፈፃሚ እንዲሆኑ ይከታተላል፤ ስለፕሮጀክቱ አፈጻጸም ከባለሃብቱ ጋር ይዋዋላል፤ ከህግ አግባብ ውጪ ሆነው ሲገኙ ይሰርዛል፡፡
- የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
ኮሚሽኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የመረጃና ቴክኖሎጂ ማዕከል በማቋቋም ከአደጋ በፊትም ሆነ በአደጋ ጊዜ እና በኃላ የተማከለ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል፣ በከተማ ደረጃ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤
- የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች መንስኤና የተጋላጭነት ደረጃና ትንናት መረጃ ያሰባስባል፤ የቅድመ አደጋ ጠቋሚ ጥናቶችን በማካሄድ አስፈላጊውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃዎችን ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤
- በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ ሊከሰት የሚችል አደጋን የመከላከል እና የአደጋ ጉዳት ቅነሳና የማጣጣም ስራን ይሰራል፤ ሌሎች ተቋማትም እንዲሰሩ ያደርጋል፤
- በከተማዋ የሚገኙ ተቋማት የአደጋ ስጋት ቅነሳ እቅድን በልማት እቅዶቻቸው ውስጥ እንዲያካትቱ ያደርጋል፤ ተግባራዊ እንዲሆኑ ይከታተላል፤
- የተቋሙ ባለሙያዎች፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና ህብረተሰቡ ስለ አደጋ ስራ አመራር ስልጠና የሚያገኙበት የስልጠና ማእከል ያደራጃል፤
- በተከታታይ ወይም በዕቅድ ላይ ተመስርቶ የናሙና ልምምዶች ያከናውናል፤ እንዲከናወኑም ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ በአደጋ ምላሽ እቅድ ላይም የማስተካከያ እርምጃዎችንም ይወስዳል፤
- የአደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን፣ የአደጋ ጊዜ ማምለጫ ደረጃዎች፣ የእሳትና የጭስ፣ የነበልባል እና ሌሎች አደጋ ጠቋሚ መሳሪያዎች በአገልግሎት መስጫ ልዩ ልዩ ተቋማት መተከላቸውንና በአግባቡ መስራታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ለህዝቡ ለማድረስ ሁሉን አቀፍ የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ ለህብረተሰቡ የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን፤ በአደጋ ወቅት መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች እና የደረሰውን አደጋ በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን የማሰራጨት ተግባር ያከናውናል፤
- በአደጋ የተጎዱና የተፈናቀሉ አካላት የአጠቃላይ የጉዳት መጠን፣ ክስረትና ፍላጎት መረጃ በማሰባሰብ ይተነትናል፤ ያደራጃል፤ ለሚመለከተው አካል የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፤ ሲወሰንም ተከታትሎ ይፈጽማል፤ ያስፈጽማል፤
- በከተማው የአደጋ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች ወቅታዊና ተደራሽ የሆነ የአደጋ ምላሽና መልሶ ማቋቋም የአደጋ ምላሽ አሰጣጥ ስራ አመራር ስርዓት ይዘረጋል፤
- በተከሰቱ አደጋዎች ምክንያት የተፈጠሩ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች መጠን የአፋጣኝ መረጃ ትንተና መሰረት በማድረግ በከተማ ደረጃ የአደጋ ጊዜ አስቸኳይ አዋጅ የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ለሚመለከተው አካል የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፤
- በአደጋ ክስተት ወቅት የሚመለከታቸውን መስሪያ ቤቶችና ነዋሪዎችን በማስተባበር ፈጣን ምላሽ ማለትም የነፍስ አድን እርዳታ ያደርጋል፤ ለድንገተኛ አደጋዎች የቅድመ ሆስፒታል ህክምና እና አምቡላንስ አገልግሎት ይሰጣል፤
- መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑና የግል ድርጅቶችን እንዲሁም ሌሎች በከተማው ውስጥ በአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦትና መልሶ ማቋቋም ተግባራት ላይ ሚና ያላቸው ተቋማት ያስተባብራል፤
- የአደጋ ስጋት ስራ አመራር መሰረተ ልማቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያዘጋጃል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በአደጋ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጊዜያዊ ድጋፍና መልሶ የማቋቋም ተግባር ያከናውናል፤
- ለአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦት ምላሽ ስራ ብቻ የሚውል የአደጋ ጊዜ ፈንድ፣ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ቁሳቁስ በመጠባበቂያነት ይይዛል፤ ያደራጃል፤ ያስተዳድራል፤ ያሰራጫል፤
- አደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎች እና በአደጋ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽና እርዳታ አቅርቦት አገልግሎቶች ላይ የሚሳተፉ በጎ ፍቃደኞችን በመመልመል፣ በማደራጀትና ሙያዊ ስልጠናዎች በመስጠት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ተግባራት ላይ ተባባሪ እንዲሆኑ ይሰራል፣
- በአደጋ ስራ አመራር ሥርዓት ውስጥ ተሳታፊ በሚሆኑ ባለድርሻ አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ለማስፈንና ውጤታማነታቸውን ለማረጋገጥ የጋራ መድረኮች ይመሰርታል፣ ያስተባብራል፤
- አግባብ ባለው ህግ አደጋ በይፋ መገለጹን ተከትሎ አግባብ ባለው አካል ሲወሰን ከተለያዩ አካላት ለምላሽ ስራ የሚውል ያደርጋል፤
- የኮሚሽኑን ፓራ ሚሊተሪ ሰራተኞችን ካቢኔ በሚያወጣው ደንብ መሠረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤
- የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፡-
- የኮንስትራክሽን ስራዎች ዘመናዊና ዓለም አቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በዲዛይን፣ በኮንትራት ይዘትና አስተዳደር እንዲሁም በግንባታ ጥራትና ቁጥጥር ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ሥርዓት እንዲሰፍን ያደርጋል፤
- አገር በቀል የኮንስትራክሽን ድርጅቶችን ብቃትና ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስትራቴጂ ያመነጫል፣ በሚመለከተው አካል ሲጸድቅ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ ይደግፋል፣ ይቆጣጠራል፤
- በኮንስትራክሽን ሥራዎች የሚሳተፉ አካላት የሥራ ውል ዝግጅትና አፈጻጸም ወጥነት ኖሮት እንዲፈጸም ለማድርግ የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፤ አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፤
- በኮንስትራክሽን ሥራዎች የሚኖሩ የሙያ ደረጃዎች እንዲዘጋጁ እና እንዲሻሻሉ ሃሳብ ያቀርባል፤ ሲጸድቅ አፈጻጸማቸውን ይደግፋል፤ ይቆጣጠራል፤
- የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ሥራዎችን ደረጃ ያወጣል፤ ሲጸድቅ ፕሮጀክቶችን ይመዘግባል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤
- የግንባታ ህጎች፣ ኮዶችና ደረጃዎች እንዲዘጋጁ እና እንዲሻሻሉ ያደርጋል፣ ሲጸድቅ ተግባራዊነቱን ይደግፋል፣ ይቆጣጠራል፤
- የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ግብዓቶች ደረጃ በወጣው ስታንዳርድ መሰረት ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በከተማ አስተዳደሩ በጀት የሚሰሩ ግንባታዎች ዲዛይን በአግባቡ መሰራታቸውን ይፈትሻል፤ ያረጋግጣል፤ በዲዛይናቸው እና በውላቸው መሰረት ስለመገንባታቸው ምርመራ ያደርጋል፤ ማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
- በማንኛውም ዘርፍ የሚደረጉ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶችን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፣ የድርጅቶቹን አፈጻጸም መረጃ ይይዛል፤ ወቅታዊ የእርምት ሥራ እንዲያከናውን ያደርጋል እርምጃ ይወስዳል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር የኮንስትራክሽን ገበያ አመላካቾችን እና የግንባታ ሞዴል ዋጋዎችን ያዘጋጃል፤ የግምት ቀመሮችን ያወጣል፤ ያጸድቃል፤ ይቆጣጣራል፤
- የኮንስትራክሽን ሥራዎችን እና ግንባታዎችን ደህንነት በመከታተል ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጉዳቶችን ይለያል፤ ጉዳቶችን ለማስተካከል የሚያስችሉ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ለሚመለከተው አካላት ያስተላልፋል፤
- በኮንስትራክሽን ሥራዎች እና ግንባታዎች ላይ የሚፈጠሩ የአደጋ አጋጣሚዎች እና ጉዳቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይፈትሻል፤ ሪፖርት ያቀርባል፤ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የኮንስትራክሽን ሥራዎች በአካባቢ ደህንነት፣ በሰራተኞችና በህብረተሰቡ ጤንነት እና ደህንነት ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለመከላከል የሚያስችሉ አሰራሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እንዲዘረጋ ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውን ይቆጣጠራል፤
- በግንባታና ዲዛይን እና የግንባታ ግብአት ማምረት ላይ የሚሳተፉ የስራ ተቋራጮችን፣ አማካሪዎችን፣ ባለሙያዎችን፣ ግብዓት አምራችና አቅራቢዎችን፣ የግንባታ መሳሪያ አከራዮችን ይመዘግባል፤ የሙያና የብቃት ማረገገጫ ፈቃድ ይሰጣል፤ ይሰርዛል፤ ዕድሳት ያደርጋል፤ ህጋዊ ፈቃድ ይዘው መስራታቸውን ያረጋግጣል፤
- የግንባታውን ኢንዱስትሪ ለማዘመን የሚያስችሉ በዲዛይን፣ በኮንስትራክሽን ግብዓትና ግንባታ ወጪ ቆጣቢ የሆኑ አዳዲስ አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ያጠናል፤ ሲፈቀድም ይተገብራል፤
- በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ የስራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎችና ባለሙያዎች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶችን አቅም ይገነባል፤
- የግንባታ ግብአት ናሙናዎችን በመውሰድ በላቦራቶሪ ጥራታቸውን ያረጋግጣል፤ ችግር በታየባቸው ላይ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ ከሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች አስፈላጊውን ክፍያ በማስከፈል የግንባታ ግብዓት የጥራት ምርመራ ያካሂዳል፤ ውጤቱን ያሳውቃል፤
- የኮንስትራክሽን ዘርፍ የመረጃ መረብና ማዕከል እንዲኖር ያደርጋል፤ መረጃዎችን ይመዘግባል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ ይተነትናል፤ ያሰራጫል፤
- የመሠረተ-ልማት ግንባታ ስራዎችን በቅንጅት ለመስራት፣ ዲዛይን ለማዘጋጀት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል፦
ሀ) የግንባታ ዕቅድና የዲዛይን ማቅረቢያ መመሪያ ያዘጋጃል፤ ያሰራጫል፤ ስለአጠቃቀሙም ስልጠና ይሰጣል፤
ለ) የግንባታ ስራዎች ቅንጅት ለማጎልበት የሚያስችል ጥናት ያካሄዳል፤ ግንባታ የሚያካሄዱ አካላት ተቀናጅተው እንዲሰሩ ያደርጋል፤
- በከተማው መዋቅራዊ ፕላን መሠረት የፕላን ስምምነት መረጃ በጽሁፍ ይሰጣል፤ የማይሰጥበት ሕጋዊ ምክንያት በሚኖርበት ጊዜ በህግ መሠረት ውሳኔውን ለባለጉዳዩ በጽሁፍ ያሳውቃል፤
- የመንግስትም ሆነ የግል የህንጻ ወይም የመሠረተ-ልማት አዲስ ግንባታ፣ የግንባታ ማሻሻያ ወይም እድሳት ፈቃድ፣ ለህዝብ ግልጋሎት ለሚውል የተጠናቀቀ ግንባታ መጠቀሚያ ፈቃድ እንዲሁም ግንባታ የማፍረስ ፈቃድ በሕግ መሠረት ይሰጣል፤
- የግንባታ ዲዛይን በከተማው መዋቅራዊ ፕላን፣ በሕግና በሕንጻ ደረጃ መሠረት በመመርመር ያጸድቃል፤
- የመኖሪያ ግንባታን ከመኖሪያ ውጪ ወደ ሆነ ሌላ አገልግሎት መቀየር የሚፈልግ ሰው በጽሁፍ ሲጠይቅ እና የግንባታው ዲዛይን ለተለወጠው አገልግሎት መዋል የሚችል ሆኖ ሲገኝ፣ ንግድ ፈቃድ ከመሰጠቱ በፊት የመጠቀሚያ ፈቃድ ይሰጣል፤
- የውጭ ማስታወቂያ የሚተከልባቸውንና የሚለጠፍባቸውን ቦታዎች፣ ግንባታዎችና ሌሎች ቋሚ ነገሮች ደረጃ አውጥቶ ይወስናል፤
- የውጭ ማስታወቂያ ጥያቄ ሲቀርብለት፣ በህግና በማስታወቂያ ደረጃ መሠረት ፈቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ የተፈቀደው ጊዜ ሲያበቃ መነሳቱን ያረጋግጣል፤
- ፈቃድ የሚሰጥባቸው ማናቸውም ተግባራት በተሰጠው ፈቃድ መሠረት በስራ ላይ ስለመዋላቸው ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ በፈቃዱ መሰረት ባልተከናወነ ሥራ ላይ በህግ መሠረት የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ፈቃዱ እንዲሰረዝ ያደርጋል፤
- የሰጣቸው ፈቃዶችን፣ የግንባታ ዲዛይኖችንና በከተማው ውስጥ የሚገኙ ግንባታዎችን በሚመለከት የተሟላ መረጃ ይይዛል፤ ያደራጃል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ እንዳስፈላጊነቱ ለሚመለከታቸው አካላት ያሰራጫል፤
- የመሠረተ-ልማት ቅንጅትን፣ የግንባታ፣ የእድሳት፣ የመጠቀሚያ ወይም ማፍረስ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥርን የሚመለከቱ የፌደራል መንግስት ህጎች፣ ፖሊሲዎች፣ ደረጃዎች እና ስልቶች በከተማው ውስጥ ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
- ግንባታዎች በዲዛይናቸውም ሆነ በአገነባባቸው ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎችም ተጠቃሚዎች ተደራሽ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል ተገቢው እርምት እንዲደረግ ያደርጋል፡፡
- የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የአካባቢ ጥበቃ ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ አካባቢ እንዳይበከል የመከላከያ ስልት ይቀይሳል፣ አግባብ ያላቸውን አካላት ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር ያስተባብራል፤
- የአካባቢ ጥበቃ፣ የተፈጥሮ ሀብትና የዘለቄታ አጠቃቀም እንዲኖርና እንዳይባክን ተገቢ ግንዛቤ ይፈጥራል፤ ስለ አካባቢ ጥበቃ በተለያዩ መድረኮች፣ አደረጃጀቶች እና በመገናኛ ብዙሃን ትምህርት ይሰጣል፤
- ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ልማትን ተግባራዊ እንዲሆን ያስተባብራል፤
- ከኢንዱስትሪ ከሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚመነጩ ዝቃጭ፣ ተረፈ ምርት፣ ቆሻሻ በሕግ መሠረት መወገዱን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ በህግ አግባብ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- ከተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚመነጩ የአየር፣ የድምጽ እና የፍሳሽ ብክለትን በህግ መሰረት ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የአካባቢ ጥበቃ ሕጎችን መሠረት በማድረግ የማምረቻና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ሌሎች አካባቢ ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ አካላት የብክለት መከላከል የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
- የከተማው የካባና ሌሎች ተቆፋሪ ማዕድናት ሥፍራዎች ያላቸውን የማዕድን ክምችት መጠን ይለያል፤ ለልማት ያዘጋጃል፤ ከአደጋ ነጻ መሆኑን ያረጋግጣል፤
- የካባ ማምረት ሥራ ለሚያካሂዱ ፈቃድ ይሰጣል፤ ቁጥጥር ያደርጋል፤
- የተለያዩ ማዕድናት ቁፋሮ የተካሄደባቸውን ቦታዎች መልሰው የሚለሙበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊነቱን ያረጋግጣል፤
- የተለያዩ ዕፅዋት የሚተከሉበትን ቦታና የሚሰጡትን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊና አካባቢያዊ ጠቀሜታ በማጥናት ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፤ በከተማው መሪ ፕላን ለመናፈሻ፣ ለደን፣ ለወንዝ ዳርቻና ለሌላ አረንጓዴ ቦታ ልማት በተከለሉ ቦታዎች ላይ የሚተከሉትን ዕፅዋት አይነት በሚመለከት ያማክራል፤ ያስተዋውቃል፤
- ያልተሞከሩና የማይታወቁ ከአካባቢ ጋር ተስማሚና ጠቃሚ የሆኑ የዕፅዋት ዝርያዎች በከተማው ማልማት ለሚፈልጉ ሰዎች ፈቃድ ይሰጣል፤
- በመንግስትም ሆነ በግል የይዞታ ክልል የለሙ ዛፎችን ለመቁረጥ ሲፈለግ ፈቃድ ይሰጣል፣ ከባለስልጣኑ ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ እንዳይቆረጡ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤
- በአስተዳደሩ ይዞታ ስር የሚገኙ ጥብቅ የደን ቦታዎች፣ የወንዝ ዳርቻዎች፣ የጋራ መገልገያ አረንጓዴ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በተፋሰስና በአረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አገልግሎት ዘርፎች መሠማራት ለሚፈልጉ የግል ባለሀብቶች፣ የሃይማኖት ድርጅቶች፣ ነዋሪዎች ወይም ሌሎች አካላት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፡፡
- ዓላማውን ከግብ ሊያደርሱ የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፤
- የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን
ኮሚሽኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የግብርና ምርት በጥራት የሚመረትበት፣ ለገበያ የሚቀርብበትን እና የግብርና ልማት የሚጎለብትበት ስልት ይቀይሳል፤ ያስፈጽማል፤
- ነዋሪዎች በከተማ ግብርና እንዲሳተፉ ያበረታታል፤ በተለያዩ የግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ አካላት ምርትና ምርታማነታቸዉ እንዲጨምር ዘመናዊ የግብርና ግብዓት እንዲቀርብላቸው ሙያዊ ድጋፍና ምክር እንያገኙ ያደርጋል፤
- የእንስሳት በሽታዎች ስርጭትን ያጠናል፤ በበሽታ ስርጭት የተነሳ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች ለመንግስትና ለአርቢዎች ያሳውቃል፤ ለእንስሳት አርቢዎች የእንስሳት ህክምናና የክትባት አገልግልት ይሰጣል፤ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ የዕብድ ውሻ በሽታ መከላከያ ክትባት ይሰጣል፤ ባለቤት የሌላቸውን እንስሳት ያስወግዳል፤
- ለእንስሳት አርቢዎች የማዳቀል አገልግሎት ይሰጣል፤ የተሻሻለ የግብርና ቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ ለአርሶ አደር እንዲዳረስ ያደርጋል፤ ውጤታማነታቸውንም ይከታተላል፤ ለገበሬዎች ትምህርትና ሥልጠና እንዲሁም የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፤
- የእንስሳት ማራቢያና ማባዣ ማዕከላትን ያቋቁማል፤ ያስፋፋል፤ ያስተዳድራል፤
- የእንስሳትና የእጽዋት የኳራንቲን አገልግሎት ይሰጣል፤ በከተማው ውስጥ አገልግሎት ላይ ሊውሉ የሚችሉ የእንስሳት መድሃኒቶች ጥራት ደረጃቸውን የጠበቁና የአገልግሎት ዘመናቸው ያላለቀ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈ መድሃኒቶችን ያስወግዳል፤
- በመዋቅራዊ ፕላኑ ለእንስሳት፣ ለሰብል፣ ለአትክልትና ፍራፍሬ ገበያዎችና ለከተማ ግብርና የተከለሉ ቦታዎችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት እንዲዘጋጁና በዘመናዊ መንገድ እንዲሰሩ ያደርጋል፤
- በግል የሚቋቋሙትን የእንስሳት ጤና ክሊኒኮች፣ ላብራቶሪዎች፣ የቆዳና ሌጦ መጋዘኖች፣ ጸረ-ተባይ ማከማቻ መጋዘኖችና መሸጫ መደብሮች ደረጃና ጥራት ጠብቀው መስራታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በህግ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት፣ በማህበራት እና በግል ቄራ ድርጅቶች የእርድ እንስሳትና የሥጋ ምርመራ አገልግሎት ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ ሕገወጥ የእንስሳት እርድና በሕገወጥ መንገድ የታረዱ ስጋ ዝውወርን ይቆጣጠራል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የተነሽዎች ማቋቋሚያ ፈንድ እና የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕቀፍ ያዘጋጃል፤ ሲፈቀድ ይመራል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የተነሽዎችን የሼር ባለቤትነት ጥያቄ ይቀበላል፤ ተገቢውን ይፈጽማል፤
- ለልማት ይዞታቸውን የለቀቁ የልማት ተነሽዎች ከሚመለከታቸው የአስተዳደሩ አካላት ጋር በመቀናጀት የመኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ያደርጋል፤ የመኖሪያ ቤቱ እስኪዘጋጅ ድረስ የቤት ኪራይ እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- በልማት ምክንያት ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተነሱ የልማት ተነሽዎችን ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ እድል ፈጠራ ፕሮግራሞች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤ በተሰጣቸው የክህሎት ሥልጠና መሠረት በአካባቢው በሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ቅድሚያ ተጠቃሚ መሆናቸውን ይከታተላል፤
- የልማት ተነሽዎች የኑሮ ሁኔታ በዘላቂነት ለማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ ኘሮጀክቶችን ይቀርፃል፤ ለፕሮጀክቱ የሚያገለግሉ የማምረቻ እና የመሸጫ ማእከላትን እንዲያገኙ ያደርጋል፤
- በከተማዉ አስተዳደር ክልል ዉስጥ የሚኖሩና ኑሮኣቸዉ በግብርና ስራ ላይ የተመሠረተ አርሶ አደሮች የያዙት መሬት መጠን ልኬት እንዲወሰድና የመጠቀሚያ ፈቃድ እንዲሰጣቸዉ ከሚመለከተው አካል ጋር ይሰራል፤
- ምንም ገቢ የሌላቸዉና መስራት የማይችሉ አርሶ አደሮች ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት የማህበራዊና የቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- ለልማት ይዞታቸውን የለቀቁ ልማት ተነሽዎች የተሰጣቸውን ካሳ አቀናጅተው ወደ ተሻለ ልማትና የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚሰማሩበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ ይደግፋል፤ ይከታተላል፤
- ለልማት ይዞታቸውን የለቀቁ የልማት ተነሽዎችን መረጃ አደራጅቶ ይይዛል፤
- የተሻለ ልምድና ሀብት ያላቸዉ ለልማት ይዞታቸውን የለቀቁ የልማት ተነሽዎችና ቤተሰቦችን በመለየት አዋጭ በሆኑ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ በግል ይዞታቸው ወይም ተደራጅተዉ የሚሰማሩበትን ስልት ይቀይሳል፤ ተግበራዊ ያደርጋል፤ ይደግፋል፣ ይከታተላል፤
- በልማት ይዞታቸውን የሚለቁ ባለይዞታዎች ከመልቀቃቸው በፊት አግባብ ባለው ህግ መሰረት የይዞታ ማስለቀቅ ሂደት መተግበሩን ይከታተላል፤
- በልማት ስራዎች እና መልሶ ማልማት ተነሽ ለሆኑት ተገቢውን የካሳ ግምት መተመኑን፤ የካሳ ክፍያ መፈጸሙን፤ ምትክ ቦታ መዘጋጀቱን፤ መሸንሸኑን፤ የምትክ ቤት ማግኘታቸውንና መቀበያ ሰርተፊኬት መሰጠቱን ይከታተላል፡፡
- የመንገዶች ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የመንገድ ኔትዎርክን፣ የመንገድ ስራን፣ የመንገዶችን አጠባበቅና አጠቃቀም ህግ ያዘጋጃል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የመንገድና ድልድይ ዲዛይን ደረጃ ያወጣል፤ ያሻሽላል፤ የጥገና ስታንዳርድ ያወጣል፤ የመንገድ ደረጃ አመዳደብ መመሪያ ያወጣል፤ አተገባበራቸውንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የመንገድና ድልድይ ዲዛይን ከመጽደቁ በፊት በትራንስፖርት ቢሮ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደርጋል፤
- የመንገድ እና የድልድይ ዲዛይን፣ ግንባታ፣ ጥገና ስራዎችን በራስ አቅም ያከናውናል፤ እንዲከናወን ያደርጋል፤
- ለመንገድ ሥራ የአዋጭነት ጥናት፣ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ፣ የመንገድ ዲዛይን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ጥናቶች ያካሂዳል፤ እንዲካሄድ ያደርጋል፤
- ለመንገድ ሥራው የሚያስፈልገውን ቦታ አግባብ ባለው ህግ መሰረት እንዲለቀቅ ያደርጋል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሠረት የመንገድ ዲዛይን የሚሰሩ፣ የግንባታ ቁጥጥርና ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን የሚሰጡ አማካሪዎችን፣ በመንገድ ግንባታዎች ላይ የሚሰማሩ ሥራ ተቋራጮች የሚመረጡበትን ዘዴ ይወስናል፤
- ግንባታቸው የተጠናቀቀ መንገዶችና ሥራዎች በውሉ መሠረት በተፈለገው ጥራትና ደረጃ መከናወናቸውን በማረጋገጥ ይረከባል፤
- የመንገድ ፕላን መሰረት አዲስ ለሚገነቡ ለእግረኛ መተላለፊያ መንገድ የሚያስፈልገውን የመሬት ስፋትና አሰራር፤ የመንገድ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎችን ክብደት፣ ዓይነት ወሰን፤ ለተለያዩ የመንገድ ተጠቃሚዎች የሚውሉ መንገዶችን ለይቶ ይወሰናል፤ የመንገድ ምልክቶችን ይተክላል፤
- ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በመንገዶች ዳር እና መካከል የሚተከሉ የዛፍ ዓይነቶችና መጠን ይወሰናል፤ መተግበሩንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በዋና መንገዶች እና በመለስተኛ ዋና መንገዶች ግራ እና ቀኝ ዳርቻዎች፣ አካፋዮችና አደባባይ ላይ የአረንጓዴ ልማት ስፍራዎች ዲዛይን የመንገድ ግንባታ ፕላን አካል አድርጎ ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ መትከያ ስፍራዎችን ዝግጁ ያደርጋል፤ አስፈላጊውን መረጃ በወቅቱ ለተፋሰስና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ መረጃ ይሰጣል፤
- የአካባቢውን የውሃ ፍሰት መጠን ያገናዘበ የመንገዶችን ፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ይገነባል፤ ያስገነባል፤ ይጠግናል፤ ያሻሽላል፤
- መንገዶችን የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎቹን ጨምሮ ከደለል፣ ከሌላ ጉዳትና አለአግባብ ከመጠቀም ይጠብቃል፤ በመንገዶች ላይ የሚከሰቱ መሰናክሎችን ያስወግዳል፤ ወይም እንዲወገዱ ያደርጋል፤ በተገቢው መንገድ ያስተዳድራል፤
- በመንገድ ላይ ለሚከናወኑ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ቁፋሮዎች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ፈቃድ ይሰጣል፤
- ከሚለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በመንገዶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወይም ማናቸውንም መሰናክሎች የሚያስቀምጡ ወይም ነዳጅና ቅባት ነክ ፈሳሾችን የሚያፈሱ ሰዎችን አግባብ ባለው ህግ መሠረት እንዲጠየቁ ያደርጋል፤
- በህብረተሰቡ፣ በቡድን፣ በግል ወይም በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት ለሚሰሩ መንገዶች ስታንዳርድ ያወጣል፤ ፈቃድ ይሠጣል፤ ይቆጣጠራል፤ እንዳስፈላጊነቱም በሚወጣው መመሪያ መሠረት ተገቢውን የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፤
- ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በኮብልሰቶን መሰራት የሚገባቸውን መንገዶች ይለያል፤ በዕቅድ ውስጥ ያካትታል፤ የኮብል ስቶን የሚጠርቡ ማህበራትን የአቅም ክፍተት በመለየት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
- የመንገድ ላብራቶሪ ምርመራና ፍተሻ ስራዎችን ያከናውናል፤ ውጤቶችንም በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
- የመንገዶችንና ድልድዮችን ይመዘግባል፣ መረጃ ይይዛል፤ መንገዶች አግባብ ባለው አካል እንዲሰየሙ ሃሳብ ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ይተገብራል፤
- የመንገድ አካፋዮችና ዳርቻዎች፣ የመከለያ አጥሮች ደረጃ እና ዲዛይን ያዘጋጃል፤
- ለጎርፍ የተጋለጡ የከተማ ክፍሎችን በተመለከተ ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት ጥናት ያደርጋል፤ የመከላከያ ሥራ መስራት የሚያስችል ዲዛይን ያዘጋጃል ወይም እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በህግ አግባብ ከስራ ተቋራጮች እና ከአማካሪዎች ጋር ውል በመዋዋል ግንባታው እንዲከናወን ያደርጋል፤
- በአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረት ሰራተኞች ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤ ያሰናብታል፡፡
- የውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፡-
- የውሃ አቅርቦት እና ፍሳሽ ማስወገድ ፍላጎት ያጠናል፤ የውሃ አቅርቦት እና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ማስተር ፕላን፣ የአጭር፤ የመካከለለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድን ያዘጋጃል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የውሃ አቅርቦት እና ፍሳሽ ማስወገድ ፍላጎትን የሚያሟሉ ፕሮጀክቶችን ይነድፋል፤ ፕሮጀክቶች በወጣላቸው ስታንዳርድ፣ ዕቅድና የውል ስምምነት መሠረት ተጠናቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፤
- የውሃ መገኛ፣ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያዎች፣ የማሰባሰቢያና መስመር ዝርጋታ ጥናቶችን ያካሂዳል፤
- የውሃ አቅርቦት እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መሰረተ ልማት ዲዛይን ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በተዘጋጁ ዲዛይኖች መሰረት አግባብ ባለው ህግ ያስገነባል፤ ያስተዳድራል፤
- የአገልግሎት ክልል በሚመለከት አግባብ ካለው ክልላዊ መንግስት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፤ የውሀ መሰብሰቢያ ስፍራዎችን ይለያል፤ ስምምነት ላይ ሲደረስ ስራ ላይ ያውላል፤
- አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ለውሃ አቅርቦት እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ልማት ለሚለቀቅ ንብረት ተገቢውን ካሳ ይከፍላል፤ ይይዛል፤ ያስተዳድራል፤
- የውሀ ምንጭ ሀብት ግድብ፣ የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃ ምንጭ፣ የግድብ ተፋሰስ ይንከባከባል፤ ያስተዳድራል፤
- ባለስልጣኑ አጣርቶ የሚያቀርበውን ውሀ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አጠቃቀሙን ሊወስን ወይም ሊገድብ ይችላል፤
- የውሀ ማጣራት፤ ማከፋፈል፤ መሸጥ፣ የፍሳሽ መስመር መዘርጋት፣ መስመር የማስቀጠያና የመገልገያ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
- የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎችን፤ የቅብብሎሽ ጣቢያዎችን ይገነባል፤ ያስገነባል፤ ያስተዳድራል
- ለውሃው አቅርቦት እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ልማት ስራ ማስፈጸሚያ የሚውል ገንዘብ ከተለያዩ የገንዘብ ምንጮች ያፈላልጋል፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ለውሀ ስርጭት እገዛ የሚያደርጉ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎችን ያከናውናል፤
- በግል የውሃና ፍሳሽ መስመር ዝርጋታ ስራዎች ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሙያዎችና ተቋማት እንደአስፈላጊነቱ የአጭር ጊዜ ስልጠናና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ይቆጣጠራል፤
- የፍሳሽ ቆሻሻን በተሸከርካሪ በመሰብሰብ፣ በማጓጓዝ እና በማስወገድ ተግባር ላይ መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች አግባብ ባለው ህግ የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤
- የባዩጋዝና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረቻ ቦታዎችን ያዘጋጃል፤ ያመርታል፤ ያስተዳድራል፤
- የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮ ማከናወን ለሚፈልጉ አካላት የቁፋሮ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ይቆጣጠራል፤
- የውሀ መስመሮችን እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመሮችን በየወቅቱ ያድሳል፤ በሚበላሹበትም ወቅት አስፈላጊውን ጥገና ያከናወናል፤ የውሀ ስርጭትን ያከናውናል፤
- ውሃን ከምርት ጀምሮ ተጠቃሚው ጋር እስኪደርስ ድረስ ባሉ ሂደቶች የወጣውን የጥራት ስታንዳርድ መጠበቁን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤ ፍሳሾች በተዘረጋ የፍሳሽ መስመርና በተሽከርካሪ ያስወግዳል፤
- ፍሳሽን ያጣራል፤ የተጣራ የፍሳሽ ውሀንና ዝቃጩን መልሶ በመጠቀም በልዩ ልዩ አገልግሎት ላይ እንዲውል ያደርጋል፤
- የውሀ ቆጣሪ የማስመጣት ብቸኛና ልዩ ስልጣን ይኖረዋል፤ የቆጣሪና የላብራቶሪ ምርመራ ያካሂዳል፤ በምርመራው ውጤት መነሻነት ተገቢውን አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- ውሃና ፍሳሽን በተመለከተ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ይሰጣል፤ ህብረተሰቡን በተለያየ የውሃና ፍሳሽ ስራዎች እንዲሳተፉ ያስተባብራል፤
- በአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረት ሰራተኞች ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤ ያሰናብታል፡፡
- የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋግጫ ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- በአጠቃላይ ትምህርት እና በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሠጥ ትምህርትና ስልጠና ከሀገሪቱና ከከተማ አስተዳደሩ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ፍላጎትና አግባብነት ካላቸው ሥርዓተ ትምህርት፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር መገናዘባቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳል፤
- አጠቃላይ የትምህርትና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በህግ የተቀመጠውን የትምህርትና ስልጠና ስታንዳርድ፣ የትምህርትና ስልጠና አገልግሎት አሰጣጥ መስፈርት ማሟላታቸውን፤ አግባብነቱና ጥራቱ ደረጃውን ጠብቆ ስለመፈፀሙ ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤
- አጠቃላይ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ያድሳል፣ ያግዳል፣ ይሰርዛል፤ ለሰልጣኞች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና ይሰጣል፤ ብቁ ሆኖ ለተገኘ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
- አጠቃላይ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማትን እና የሙያ ብቃትን መረጃ ያደራጃል፤ ያሰራጫል፤
- የአጠቃላይ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማት ብቃት እና ምዘና መከታተያና መገምገሚያ ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ፍቃድ ያላቸው የትምህርት እና ስልጠና ተቋማት ጥራታቸው ከስታንዳርድ በታች በሆኑ ተቋማት ላይ የሙያ ብቃት ማረጋገጫውን እስከመሰረዝና እስከ ማሸግ የሚደርስ እርምጃ ይወስዳል፤
- በሕገ ወጥ መንገድ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ያገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ላይ የሙያ ፈቃዳቸውን ይሰርዛል፣ ተቋሙንም ያሽጋል፤ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ እንዲጠየቁ ስልጣን ላለው አካል ያሳውቃል፤
- የሙያ ብቃት ፍቃድ እያላቸው አግባብ ያለው ህግ በሚጥሱ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የሙያ ብቃት ፍቃድ ሳያገኙ ወይም በሌሎች ተቋማት የሙያ ብቃት ፈቃድ የሚሰሩ የትምህርት እና ስልጠና ተቋማትን ያሽጋል፤ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ እንዲጠየቁ ሥልጣን ላለው አካል ያሳውቃል፤
- ለትምህርት እና ስልጠና ተቋማት ዕውቅና ይሰጣል እውቅና አግኝተው የሚሠሩ ትምህርት ቤቶች በሀገር ደረጃም ሆነ በከተማ ደረጃ በሚወጡ ህጎች የተቀመጡ የትምህርት አግባብነትና ጥራት ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
- በትምህርት ተቋማት የህብረተሰቡን ተሳትፎ ሊያረጋግጡ የሚችሉ አደረጃጀቶች፣ የወላጅ፣ የተማሪ፣ የመምህራን ፎረም፣ የተማሪ ክበባት ስለመኖራቸው ያረጋግጣል፤ እንዲሁም የትምህርት አገልግሎት ክፍያዎች የወላጆችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ እንዲሆን ከተቋማቱ ጋር ይመክራል፤
- ከሥራ ዓለምና ከተቋማት የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ብቁ ሆነው ለተገኙ ተመዛኞች የምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
- በምዘና ጣቢያነት አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ኢንዱስትሪዎችን ይለያል፤ ለምዘነና ምቹ ሆነው እንዲደራጁ ያደርጋል፤ የምዘና ስራ ይከታተላል፤ በበላይነት ይመራል፤
- ከባለስልጣኑ ውጭ በከተማው አስተዳደር ከሚገኙ ተቋማት ወይም ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የምዘና አገልግሎት መስጠት የሚችሉ አካላትን በመምረጥ ዕውቅና ይሰጣል፤
- የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከላት፣ የኢንዱስትሪ መዛኞች እና ሱፐርቫይዘሮች አሰራር ለመከታተል የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- ከባለስልጣኑ ባለሙያዎች በመረጃ አያያዝና አደረጃጀት ዙሪያ የሚቀርቡትን የጥናት ኘሮጀክቶች፣ ኘሮፖዛሎችንና ሪፖርቶችን በመገምገም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ብቃት ያላቸው ሰራተኞች በሚፈለጉበት ወቅት የሙያ ብቃት ምዘና በመስጠት ብቃታቸውን ያረጋግጣል፡፡
- የምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የምግቦችን ደህንነትና ጥራት፣ የመድኃኒቶችን ደህንነት፣ ፈዋሽነት፣ ጥራትና አግባባዊ አጠቃቀም የህክምና ባለሙያዎችን ብቃትና አሰራር፣ የኃይጅን፣ የአካባቢ ጤናን እና የጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግበት ተቋማት የቁጥጥር ደረጃዎች ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
- ለጤና ተቋማት፣ የመድኃኒት አከፋፋዮችና ማከማቻዎች፣ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ያግዳል፤ ይሰርዛል፤
- ለጤና ነክ ተቋማት የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤ የንጽህናና የጤና ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የህጻናት ማቆያዎችን የሙያ ደረጃ ፈቃድ ይሰጣል፣ የንጽህና፣ የጤንነትና ተስማሚነት ደረጃዎችን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የምግብ፣ የመድኃኒት የአካባቢ ጤና አጠባበቅ፣ የጤና ባለሙያዎች እና የጤናና ጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማትን በሚመለከት የመረጃ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤
- በምግብ ወይም በመድኃኒት መመረዝ ወይም መበከል ምክንያት ለሚደርስ ሞት፣ የጤንነት መታወክ መንስኤ የሆነውን ንጥረ ነገር ልዩ ልዩ ናሙናዎች በመውሰድ ምንነታቸው እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤ እርምጃ ይወስዳል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የባህል መድሀኒት አዋቂዎች በባህል ህክምና ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ ፈቃድ ይሰጣል፤ የባህል መድሀኒቱ ምን አይነት ይዘት እንዳለው በላብራቶሪ እንዲመረመር ያደርጋል፤ ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤
- በደረጃው የተፈቀደለት የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ያግዳል ይሰርዛል፤ የባህል ሕክምና ከዘመናዊ ሕክምና ጎን ተጠናክሮ የሚሄድበትን ሥልት ይቀይሳል፤
- በባለስልጣኑ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማት ላይ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያበቃ ምግቦች፣ መድኃኒቶችና ጥሬ ዕቃዎችቻቸው በአግባቡ መወገዳቸውን ያረጋግጣል፤
- ሕገወጥ ምግቦችን፣ መድኃኒቶችና፣ የጤና አገልግሎቶችን ይቆጣጠራል አስፈላጊ እርምጃዎችንም ይወስዳል፤
- አስተዳደሩ በሚቆጣጠራቸው የጤና ተቋማት አበረታች መድሀኒቶች፣ የናርኮቲክ መድኃኒት፣ ሳይኮትሮፒክ ንጥረ ነገሮች እና ፕሪከርሰር ኬሚካሎች ለህሙማን ማዘዝን፣ ማደልን፣ አጠቃቀምን፣ መመዝገብንና ሪፖርት ማድረግን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ አስፈላጊ ሲሆን ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
- በከተማው አስተዳደር ሥር ያሉ ጤና ነክ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ተቋማት ተገቢውን የሐይጅንና አካባቢ ጤና አገልግሎት መስፈርት ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፤
- የስነምግባር ግድፈት በሚያሳዩ የጤና ባለሙያዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤
- ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን የጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ ያደራጃል፤ለሚሰጠው አገልግሎት በህጉ ክፍያ ያስከፍላል፡፡
- የመንግስት ሕንጻና ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል:-
- በመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ላይ ለከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤
- ስልጣኑ በህግ ለሌላ አካል ወይም ለሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ካልተሰጠ በቀር የከተማውን አስተዳደር ህንፃዎችንና ቋሚ ንብረቶችን ይመዘግባል፤ በበላይነት ያስተዳድራል፤ ያድሳል፤ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች በመለየት እንዲጠገን ያደርጋል፤
- የህንጻና ንብረት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዘመናዊ ስርዓትን ይዘረጋል፤ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል፤ ምድረ ግቢን ውብና ማራኪ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- የመንግስት ህንፃዎች አጠቃቀም፣ ለተጠቃሚው ያላቸው ተደራሽነት እና ከወጪ አንፃር ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
- የተቋማትን ፍላጎት፣ የስራ ባህሪይ እና የተገልጋይ ሁኔታን በማጥናት የተቋማትንና የስራ ክፍሎችን የስራ ቦታ ይደለድላል፤
- የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት ለአገልገሎት አሰጣጥ የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች የኪራይ ደረጃ አጥንቶ ይወስናል፤ ለመንግስት አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች እንዲገነቡ ያደርጋል፤
- በከተማው ውስጥ ባለቤት የሌላቸው ህንጻና ንብረቶችን አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተረክቦ ያስተዳድራል፤
- የመንግስት ህንፃዎች ወጥ የሆነ ስታንዳርድ እና ዲዛይን እንዲኖራቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል፤ ያስገነባል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- የህንጻ አስተዳደር ሥራዎች የተቀላጠፉና ውጤታማ እንዲሆኑ የውስጥ አደረጃጀት እና የቢሮ ቁሳቁስ ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤
- በመንግስት የንብረት አያያዝ ስርዓት መሰረት የመንግስት ንብረቶች በአግባቡ ስለመያዛቸው እና ጥቅም ላይ ስለመዋላቸው የንብረት ኦዲት ያደርጋል፤
- በባለስልጣኑ የህንጻና የንብረት ኦዲት ውጤት መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ ያልወሰዱ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለይቶ ተጠሪ ለሆነለት ቢሮና ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
- አግባብ ባለው ህግ ቋሚ ንብረቶች ዋጋ እንዲወጣላቸው እና በየዓመቱ የዕልቀት ዋጋ እንዲሰላላቸው በማድረግ መንግስት የቋሚ ንብረቶች የያዙትን ዋጋ እንዲያውቅ ያደርጋል፤
- ባለስልጣኑ በሚያስተዳድራቸው ንብረቶች ላይ የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶችን ይከላከላል፤ ተፈጽሞም ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የመንግስት ህንፃዎች የሚገነቡበት ቦታ ያስፈቅዳል፤ ይመዘግባል፤ ተገቢውን የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይጠብቃል፤
- የመንግስት ህንፃዎች የሰራተኞች ካፍቴሪያ፣ የጽዳትና ውበት፣ የጥበቃ፣ የመጀመሪያ ህክምና፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎች ማቆሚያ፣ የመኪና እጥበት እና የህፃናት ማቆያ አገልግሎቶች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
- የአሽከርካሪና ተሸካርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተሸከርካሪዎችን ይመዘግባል፤ የስም ዝውውር አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ እዳና እገዳ አገልገሎት ይሰጣል፤
- የተሸከርካሪ አመታዊ ምርመራ በራሱ ወይም በህግ አግባብ ውክልና በሰጠው አካል ያከናውናል፤ ምርመራውን ያላለፉ ወይም በወቅቱ ያልተመረመሩ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ ያደርጋል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የአሽከርካሪነት ብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ ምትክ ይሰጣል፤ ህጋዊነቱን ያረጋግጣል፤
- የተሸከርካሪ ስታዳርዳይዜሽን፣ ምዝገባና ስረዛ፤ የተሸከርካሪ ዋጋ ግምት ይሰጣል፤
- የባለሞተር ተሸከርካሪዎችን የማሽከርከር ስልጠና የሚሰጡ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች የስራ ፍቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፤ አግባብነት የሌለው ተግባር ሲፈጽሙ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወስዳል፤
- በተሸከርካሪ ምርመራ አገልግሎት፣ በአሽከርካሪ ማሰልጠኛ፤ በጋራዥ፣ በጎሚስታ እና መሰል አገልግሎቶች ላይ ለሚሰማሩ ተቋማትና ግለሰቦች የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጣል፤ አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤
- የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ መረጃዎችን በተመራጭ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ያደራጃል፣ ያሰራጫል፣ እንደ አስፈላጊነቱም ስራ ላይ እንዲ ውሉ ያደርጋል፤
- ከአሽከርካሪና ከተሸከርካሪ ጋር ተያይዞ ያሉ አገልግሎቶችን ሊያሻሽሉ የሚችሉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ያከናውናል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሊት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የትራፊክ አመራርና አስተዳደር ሥራ በበላይነት ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤ ለአገልግሎቱ ሥልጠት የሚያግዝ ስልት ይቀይሳል፤ ይተገብራል፤
- ትራፊክን ማሳለጥ የሚያስችሉ ተግባራትን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን፣ ትርንስፖርት ባለስልጣን እና ከሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤
- የመንገድ ትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያስችል የትራፊክ ሥርዓት ይዘረጋል፤ ስታንዳርዶችን ያዘጋጃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የትራፊክ ፍሰትና ደህንነትን ለማሻሻልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ይዘረጋል፤ የመረጃ ሥርዓቱን በመጠቀም የትራፊክ ደህንነቱንና ፍሰቱን ይከታተላል፤ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ያቀናጃል፤ እንደአስፈላጊነቱ በግብዓትነት ይጠቀማል፤
- በትራንስፖርት አገልግሎት እና በትራፊክ ሥርዓት ዙሪያ ግንዛቤ ይፈጥራል፤
- የትራፊክ ምልክቶችና ማመላከቻዎች፣ የመንገድ ላይ ቅቦች፣ የትራፊክ መብራቶች እና ሌሎች የትራፊክ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ይተገብራል፤ ያስተዳድራል፤
- ከመንገድ ትራፊክ እንቅስቃሴ አንፃር ሊገነቡ የሚገባቸውን መንገዶች ይለያል፤ የመንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ዲዛይን ሲሰራ ወይም ሲያሰራ ትራፊኩን ከማሳለጥ አኳያ አግባብነቱን ይገመግማል፤ ያረጋግጣል፤
- ለህዝብና ለጭነት ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ መናኽሪያዎች፣ ፌርማታዎች፣ ፓርኪንግ እና ዴፖዎች በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሠረት በሚመለከተው አካል መገንባታቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ከትራንሰፖርት ባለስልጣን ጋር በመተባበር የከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ የጭነት ተሸከርካሪዎች መንቀሳቀሻ ፈቃድ ቁጥጥር ሥርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ መሆኑንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- መንገድ ለመዝጋትና ሌሎች ተዛማች ተግባራትን ወይም ከታለመለት ዓላማ ውጪ ለመጠቀም ለሚቀርብ ጥያቄ ፈቃድ ይሰጣል፤ ያድሳል፤ የመንገድ ላይ ኩነቶችን ያስተዳድራል፤ ህግን በሚተላለፉ ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የትራፊክ ደንቦች መከበራቸውን ቁጥጥር ያደርጋል፤ አግባብ ባለው ህግ ደንብ ተላላፊዎችን ላይ እርምጃ ይወስዳል፤ የማስፈፀሚያ ስልቶችን ይዘረጋል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግጣል፤
- በከተማው ውስጥ የተሸከርካሪ የፍጥነት ወሰን ይወስናል፤ ለተለያዩ የመንገድ ተጠቃሚዎች የሚውሉ መንገዶች ለይቶ ይወስናል፤
- የተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልገሎት ክፍያ ያጠናል፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የአሽከርካሪዎችን የርቀት እይታ የሚጋርድ ወይም የደረቁ የመንገድ ዳርና የአደባባይ ዕጽዋት እንደአስፈሊጊነቱ በተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት ኤጀንሲ መወገዳቸውን ወይም መመልመላቸውን ያረጋግጣል፤
- የሕዝብ የብዙኃን ትራንስፖርት፣ አንቡላንስና የእሳት አደጋ አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችና የመሳሰሉት የመንገድ ቅድሚያና ያልተቋረጠ የትራፊክ አቅጣጫ የሚያገኙበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ ተግባራዊ መሆኑንም ይከታተላል፤
- የተሸከርካሪ ማቆሚያ ቦታ ፍላጎትና አቅርቦት ጥናት አጥንቶ አማራጭ የመፍትሔ ሃሳቦችን ያቀርባል፤ ከባለድርሻ አካላት ጋር ይተገብራል፤ የፓርኪንግ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤
- በትራፊክ ደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚጣል ቅጣት አግባብ ባለው ህግ ይሰበስባል፤
- የፓርኪንግ ቦታ ግንባታ ወይም አገልግሎት መስጠት ለሚፈልጉ የመንግስትና የግል ተቋማትና ግለሰቦች ፍቃድ ይሰጣል፤ ይቆጣጠራል፡፡
- የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- ብሎክን ማዕከል አድርጎ የተደራጀውን ሕብረተሰብ እና ብሎክ ካውንስል አደረጃጀትን ቀጣይነት ባለው መልኩ ያደራጃል፣ ያጠናክራል፣ ይደግፋል፣ ያስተባብራል፣ ክፍተቶች ሲኖሩ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
- በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚሰሩ ተግባራትን ይለያል፤ ተሳትፎ የሚጎለብትበትን ስልት ይቀይሳል፤ ስለህብረተሰብ ተሳትፎ አደረጃጀትና ጠቀሜታ ለህብረተሰቡ ያስተዋውቃል፤ ከተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት ይሰራል፤
- የተቀናጀ የህብረተሰብ ተሳትፎ ውጤታማ እንዲሆን መመሪያዎች እና የአሰራር ሥርዓቶች ያዘጋጃል፤ ሲጸድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤
- ህብረተሰቡ የብሎኩን የልማት ፍላጎት እንዲመለስ፣ የአግልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል፣ የሠላምና ፀጥታ፣ የስራ አጥነት እና የማህበራዊ ችግሮች ለማስወገድ ነዋሪው በባለቤትነት እና በፍላጎት እንዲደራጅ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፤
- አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን በመፈለግ አግባብ ባለው አካል ሲፈቀድ የአካባቢውን ህብረተሰብ የልማት ሥራ ያግዛል፤ ከህብረተሰቡ የሚሰበሰቡ የቁሳቁስ፤ የጉልበትና፤ የገንዘብ መዋጮዎች ሥራ ላይ መዋላቸውን ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
- በብሎክ ነዋሪዎች የተለዩ ፍላጎቶች የሚሟሉበትን እና የተለዩ ችግሮች የሚፈቱበትን ዕቅድ ከብሎክ ካውንስል ጋር በመሆን ያዘጋጃል፤ ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ያስፀድቃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
- ከሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላት ጋር በመቀናጀት በብሎክ የተደራጁ ማህበረሰብ አቀፍ ካውንስሎችን ችግሮቻቸው የሚፈቱበት እና ጥያቄዎቻቸው ምላሽ የሚያገኙበት ሁኔታ ያመቻቻል፤ ከአቅም በላይ የሆኑ ችግር ሲያጋጥሙ በየደረጃው ላሉት አስተባባሪ ካውንስሎች ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር ያቀርባል፤ ያስወስናል፣ ስራ ላይ መዋሉን ይከታተላል፤
- በብሎክ ውስጥ የተሰሩ ማንኛውም የልማት ስራዎች በአግባቡ ስራ ላይ እንዲውሉ እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ከብሎክ ካውንስል ጋር በመሆን ክትትል ያደርጋል፤ የማስተካከያ ሥራዎችን ያከናውናል፤
- በብሎክ በተምሳሌትነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ሁለገብ የህብረተሰብ ተሳትፎ ያደረጉ እና የልማት ስራዎችን ያከነወኑትን ካውንስሎችን በመለየት እውቅና ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ልምዳቸውን ቀምሮ እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በራስ መልካም ፈቃድ፣ ተነሳሽነት እና ያለማንም አስገዳጅነት ለሚሳተፉ ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል፤ ያስተባብራል፤ ይመራል፤
- በበጐ ፍቃድ አገልግሎት የሚሰማሩ ወጣቶች፣ የሞያ ማህበራት፣ መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን ያስተባብራል፣ የእውቅና እና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ ያበረታታል፤
- ህብረተሰቡ ያለውን እውቀትና ችሎታ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ላይ እንዲያውልና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችለውን የበጎ ፈቃድ ባህል እንዲያጎለብት ያበረታታል፤
- በከተማው የሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በእቅዶቻቸውና በፕሮግራሞቻቸው ውስጥ አካትተው እንዲሰሩ ያደርጋል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
- በከተማው ዘላቂ የበጐ ፍቃድ ፍኖተ ካርታ ያዘጋጃል፣ ካውንስል እንዲደራጅ ያደርጋል፣ ካውንስሉ የሚሳተፍበትን የአገልግሎት መስኮች ይለያል፣ ስልጠና ይሰጣል ተግባራዊነቱን ይከታተላል፡፡
- የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- አግባብ ባለው ሕግ መሠረት የመሬት ይዞታን በተመለከተ የመብት፣ ክልከላ እና ኃላፊነት መረጃን ምዝገባ፣ ስረዛ፣ እድሳት፣ ማስተካከያ ሌሎች የመሬት ይዞታ አገልግሎቶችን ባአግባቡ መሰጠታቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት ለተመዘገቡ የመሬት ይዞታ መብት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት መሰጠቱን ያረጋግጣል፣ ይቆጣጠራል፤
- በሥልታዊ ዘዴ ወይም በአልፎ አልፎ ዘዴ የመሬት ይዞታን የማረጋገጥ ሥራዎች መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ ይቆጣጠራል፤
- ሀገራዊ ደረጃን መሰረት ያደረገ የቁራሽ መሬት ልዩ መለያ ኮድ ይሰጣል፤ ተግባራዊነቱንም ያረጋግጣል፣
- የመሰረታዊና የህጋዊ ካዳስተር ካርታ ያዘጋጃል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፤
- የመሬት ይዞታ ምዝገባ መረጃን በዲጂታል እና በወረቀት ይይዛል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ እንዲሁም መረጃውን ይጠቀማል፤ ጥሬና የተቀናጀ ወይም የተተነተነ መሬትና መሬት ነክ መረጃዎችን ያሰራጫል፤
- ወቅታዊ የከተማ መሬት፣ የፊዝካል መሠረተ ልማትና የማህበራዊ ተቋማት የስፓሻልና ስፓሻል ያልሆኑ መረጃዎችንና ጥናቶችን ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ይሰበስባል፣ በጂ.አይ.ኤስና በካርቶግራፊ በማደራጀት ዳታ ባንክ ያዘጋጃል፣ ያስተዳድራል፤
- እንደአስፈላጊነቱ ከተማዋን ሙሉ በሙሉ የሚሸፍን እና ለተለያዩ ተቋማት የሚያገለግሉ የሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖልጂ ማለትም የአየር ፎቶ፣ የሳተላይት ምስሎችንና የራዳር ፎቶዎችን በመጠቀም የግንባታዎችን፣ የመሬት አጠቃቀምና ሌሎች የከተማ ለውጦችን በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ እንዲሰጡበት ያስተላልፋል፣ እንደአስፈላጊነቱ ጥሬ መረጃዎችን ለተለያዩ አካላት በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ይሰጣል፤
- ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ከተማ ህጋዊ ካዳስተር መረጃ ሥርዓት ላይ መደበኛ የሆነ የስጋት እና የደህንነት ቁጥጥር ያደርጋል፤
- የህጋዊ ካዳስተር ቴክኖሎጂ ስርዓትን እና የኔት ወርክ መሰረተ-ልማትን ያሻሽላል፤ ወቅታዊ ያደርጋል፤ ያስተዳድራል፤
- በህግ መሰረት የሕጋዊ ካዳስተር መረጃን ለህዝብ ክፍት ያደርጋል፤
- ተግባሩን በሚመለከት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ይመረምራል፣ ውሳኔም ይሰጣል፤
- የሚሰሩ ሥራዎች እና የሚሰጡ አገልግልቶች ግልጽነት ያለውና ፈጣን እንዲሆኑ የሚያስችል የአሰራር ማንዋልችን ያወጣል፤ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ያከናውናል፤
- ኤጀንሲው በራሱ በሰጠው የምዝገባ ማስረጃ ምክንያት በቅን ልቦና ጉዳት ለደረሰባቸው ሶስተኛ ወገኖች በፍርድ ቤት ተጠያቂ ሆኖ ሲገኝ ክፍያ ይፈጽማል፤ የሚከፍለው የዋስትና ፈንድ በከተማው አስተዳድር እንዲቋቋም ክትትል ያደርጋል፤
- የመሬት መቆጣጠሪያ ነጥቦችን ሀገራዊ ስታንዳርዶችን መሠረት በማድረግ ያስተክላል፣ እንዲናበቡ ያደርጋል፤ ዘመናዊ ያደርጋል፤ እንዲሁም ያስተዳድራል፤
- በሦስተኛ ደረጃ የሚተከል የመሬት የመቆጣጠሪያ ነጥቦችን የማብዛት ስራ ይሰራል፤
- መረጃ ለመሰብሰብ፣ ለማደራጀትና ለማሠራጨት እንዱሁም የአድራሻ ሥርዓት ለመዘርጋት፣ ለማስተዳደር እና የቤት ቁጥር ለመስጠት የሚያገለግል የህግ ማዕቀፎችንና ስታንዳርዶችን ያዘጋጃል፣ በሚመለከታቸዉ አካላት ያስጸድቃል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ይተገብራል፤ እንዲተገበር ሥልጠናና ድጋፍ ይሰጣል፤
- ለአድራሻ ሥርዓት የሚሆኑትን የመንገድ፣ የፓርሴልና የቤት ቁጥር በመስጠት እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመሰብሰብና በማደራጀት የአድራሻ ሥርዓትን ይዘረጋል፤ ዘመናዊ ያደርጋል፤ ያስተዳድራል፤
- የመሬት መረጃ አያያዝና አጠቃቀም እንዲሁም የአድራሻ ሥርዓትን በሚመለከት በፌደራልና በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ የሚወጡ አግባብነት ያላቸዉ ህጎች ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
- የመንግስት የግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- ዝርዝራቸው በኤጀንሲው መመሪያ የሚወሰኑ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ ዕቃዎች፣ አገልግሎቶችና ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ ያከናውናል፤
- በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ 1 ላይ የተገለፀው ቢኖርም በመንግስት ለሚከናወኑ የግንባታ ስራዎች ግዥ ግንባታውን እንዲያስፈፅም ስልጣን በተሰጠው አካል ተፈፃሚ ይሆናል፤
- ግምታቸው አግባብ ባለው ህግ መሰረት ከሚወሰን የገንዘብ መጠን በላይ የሆኑ በአስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ኃላፊነት ስር ያሉ ንብረቶች እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸውን ንብረቶች ይሸጣል፤
- ለመንግስት የልማት ድርጅቶችና ለግሉ ዘርፍ በወቅታዊ የገበያ መረጃ ላይ የተመሰረተ የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ የግዥ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤
- ለከተማ አስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች ግዥን በተመለከተ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤
- በከተማው አስተዳደር ለሚገኙ መንግስት መስሪያ ቤቶች፤ ለልማት ድርጅቶች እና ለግሉ ዘርፍ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተመጣጣኝ ዋጋ ያስከፍላል፤
- በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 የተመለከቱትን ሥልጣንና ተግባሮች በስራ ላይ ሲያውል፡-
ሀ. የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገዱ ተግባር አግባብ ባለው ህግ መሰረት መፈጸሙን ያረጋግጣል፤
ለ. ግዥ የተፈጸመላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸው ተመሳሳይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የአገር ውስጥ ግዥ ሂደት አጠናቆ የማዕቀፍ ስምምነት በመፈራረም ይህንኑ የመንግስት መሥሪያ ቤቶች እንዲያውቁት ያደርጋል፤
ሐ. የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸው ተመሳሳይ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ግዥ፤ ከተማዊ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ዕቃዎችና አገልግሎቶች የግዥ ሂደት በማጠናቀቅ ዕቃዎቹና አገልግሎቶቹ ለተጠቃሚ እንዲደርስ ያደርጋል፤
መ. ልዩ ሙያዊ እውቀት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አግባብነት ካላቸው መንግስታዊ ተቋማት መጠየቅና ማግኘት ይኖርበታል፡፡
- የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፡-
- የከተማዋን ሁለንተናዊ ጽዳት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ሥራዎችን ያከናውናል፤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ይሰራል፤
- የከተማው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብ፣ አጓጓዝና አወጋገድ የህዝብ ጤናን በማይጎዳና የአካባቢ ብክለትን በማይፈጥር መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር ይዘረጋል፤ ይተገብራል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤ ይቆጣጠራል፤
- በህብረተሰቡ ዘንድ የአመለካከትና የባህሪይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ የትምህርትና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በየደረጃው ያከናውናል፤ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችንም ይሰጣል፤ እንዲሰጥም ያስተባብራል፤
- የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስራዎችን ለመተግበር በከተማ ደረጃ የወጡና የፀደቁ ፖሊሲና ህጎች በየደረጃው እንዲፈፀሙ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና የግል የጽዳት ድርጅቶች በከተማው የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስራዎች የሚሳተፉበትን አማራጮች በማጥናት እንዲተገበር ያደርጋል፤
- ደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ የሚቀንስበትንና የሚለይበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ የደረቅ ቆሻሻ የመልሶ መጠቀምና ማስወገድ ስራዎች በአግባቡ መፈፀማቸውንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ለአገልግሎቱ የሚወጣው ወጪ በተገልጋዮች የሚሸፈንበትን የታሪፍና የክፍያ ስርዓት አጥንቶ ያቀርባል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የግል ባለሀብቶችና የግል ጽዳት ድርጅቶች የሚያቀርቡትን የፕሮጀክት ፕሮፖዛል ይገመግማል፤ የብቃት ማረጋገጫ፤ የምስክር ወረቅትና የስራ ፍቃድ ይሰጣል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤
- የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከላትንና ስፍራዎችን ያስተዳድራል፤ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን የማስወገጃ ቦታው በህዝብ ጤና እና በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ በማያስከትል መንገድ አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- የመልሶ መጠቀሚያ ማዕከላትና የማስወገጃ ቦታ የደረቅ ቆሻሻ በክብደት ሚዛን የሚመዘንበትንና ትክክለኛ መጠኑ የሚታወቅበትን ስርዓት ይዘረጋል፤ መረጃዎችን መዝግቦ ይይዛል፤ ያሰራጫል፤ እንዲሁም የከተማዋን የደረቅ ቆሻሻ አጠቃላይ ሁኔታ ከመረጃው ተነስቶ ማስተካከያ የሚደረግባቸውን መረጃዎች በማደራጀት ለወሳኝ አካል ያቀርባል፤
- የደረቅ ቆሻሻ ጊዜአዊ ማስቀመጫ ቦታዎችን በከተማው የተለያዩ አቅጣጫዎች በማጥናት እንዲገነቡና ጥቅም ሊይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
- የመልሶ መጠቀምና የቀልዝ (የብስባሽ ማዳበሪያ) ማዕከላትን በማስፋፋት ደረቅ ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የሚውልበትን፣ ጠቃሚ ውጤት የሚያስገኝበትን የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮች በማጥናት እንዲተገበሩ ያደርጋል፤ ውጤታቸውንም ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- መልሶ መጠቀሚያ ማዕከላትና ማስወገጃ ቦታ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ በማጥናት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ይተገብራል፤
- የአዲስ ሳኒተሪ ላንድፊል እና ከቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ቦታ መረጣ፣ የጥናትና የማልማት ስራዎችን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
- የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ ተሸከርካሪዎችን እንዲሁም ማሽነሪዎችን ያሰማራል፣ ያስተዳድራል፡፡
- ዓላማውን ከግብ ሊያደርሱ የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፤
- የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የህብረት ስራ ማህበራትንና የጋራ ህንፃ ባለቤቶች ማህበራትን ያደራጃል፤ ይመዘግባል፤ ያስፋፋል፤ የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጣል፣ ማህበሩ ሲፈርስ ከመዝገብ ይሰርዛል፤
- የህብረት ስራ ማህበራት በዩኒየንና በፌዴሬሽን ደረጃ እንዲደራጁ ያበረታታል፤ የህብረት ስራ ማህበራት ባንክ የሚቋቋምበትን መንገድ ያጠናል፤
- ለገንዘብና ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት የተደራጁትን አባላት ቁጠባ ባህል እንዲዳብር እና ቁጠባ ድርሻቸውን ከፍ በማድረግ ወደ ኢንቨስትመንት የሚሸጋገሩበትን አሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤
- ባህላዊና አገር በቀል የራስ አገዝ ማህበራት ወደ ዘመናዊ የህብረት ስራ ማህበራት የሚያድጉበትን ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤ የጥናቱንም ውጤት ያስተዋውቃል፤ ያሰራጫል፤ ለተግባራዊነቱም ይሰራል፤
- የህብረት ስራ ማህበራት ስራ አመራርና የሂሳብ አያያዝ ዘመናዊ አሰራርን እንዲከተል አስፈላጊውን የስልጠና ፕሮግራም ያዘጋጃል፤ ይሰጣል፤
- የህብረት ሥራ ማህበራትን ሂሳብ ይመረምራል፤ ሂሳብ አጣሪም ይመድባል፤ ሲፈርሱም ከመዝገብ ይሰርዛል፤ አግባብ ባለው ህግ የህብረት ሥራ ማህበራት የሚከተሉትን የሂሳብ አያያዝና ምርመራ ስርዓት ይከታተላል፤
- የህብረት ስራ ማህበራት የገበያ መሰረተ ልማት እንዲሟላላቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፤ ይከታተላል፤ የመስሪያ ቦታ፣ የመሸጫ ቦታ እና ሌሎች መሰል ተቋማት አስተዳደርና አጠቃቀምን በሚመለከት አግባብነት ባለው ህግ መሰረት ችግሮቻቸው የሚፈቱበትን አግባብ ያመቻቻል፤ የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤
- የህብረት ሥራ ማህበራት ምርቶች ገበያ እንዲገኙ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤ በአገር ውስጥ ሸማቹና አምራቹ በቀጥታ የሚገናኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- በከተማዋ የሚገኙ የህበረት ስራ ማህበራት ምርቶች ተጨማሪ እሴት ወይም ዋጋ እንዲኖራቸው፣ ወደ ኢንዱስትሪ ምርትነት እንዲለወጡ እና የእጅ ጥበብ ምርቶች እንዲድጉ የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል፤
- የህብረት ስራ ማህበራትን ለማስፋፋትና ለማጠናከር የሚረዳ የገበያ ጥናት በማድረግ አስፈላጊ መረጃዎችን ያጠናቅራል፤ ያሰራጫል፤ አግባብ ባለው ህግ ለህብረት ስራ ማህበራት የሚሰጡ ማበረታቻዎችን ያጠናል፤ ሲፈቀድም ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤
- ከተማዋን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ እና ለህብረት ሥራ ማህበራት እድገት የሚበጁ ልዩ ልዩ የፕሮጀክት ሃሳብን በማመንጨት፣ አዋጭነታቸውን በማጥናት እና በማዘጋጀት ማህበራት እንዲሰማሩባቸው ያበረታታል፤
- የህብረት ስራ ማህበራት ሞዴል የመተዳደሪያ ደንቦችን ያዘጋጃል፡፡
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- በከተማ አስተዳደሩ የወሳኝ ኩነት ምዝገባን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ይመዘግባል፤ መመዝገቡን ይቆጣጠራል፤ ይከታተላል፤
- የነዋሪነት መታወቂያና ሌሎች የነዋሪዎች አገልግሎቶችን ይሰጣል፤
- የክብር መዝገቦች ዝግጅትና ስርጭትን፣ የመረጃ አጠቃቀም ሥርዓት አግባብ ካለው የፌዴራል አካል ጋር በመተባበር ይሰራል፤ ድጋፍ ይሰጣል፤ የክብር መዝገቦች ለሁሉም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሰራጨታቸውን ያረጋግጣል፤
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስፈላጊነትን አስመልክቶ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ስልጠናዎች ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ያደርጋል፤
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የጥራትና የሽፋን ደረጃ ለመገምገምና ለመቆጣጠር የሚያስችል ጥናት ያካሂዳል፤ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና የብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ መሠረት የተሰበሰቡ መረጃዎችን አግባብ ላለው የፌደራል አካል በወቅቱ ያስተላልፋል፤
- የወሳኝ ኩነት ምዝገባና የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ያደርጋል፤
- መንግስታዊ ተቋማት፣ ማህበራት እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚደረገው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሥርዓት የተሟላ እንዲሆን ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ያስተባብራል፡፡
- የተፋሰስና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖረዋል፤
- በፕላኑ የተመላከቱ አረንጓዴ አካባቢዎችን ይለያል፤ የይዞታ ማስረጃ ሊወጣላቸው የሚችሉትን በሚመለከተው አካል በስሙ በማስመዝገብ የይዞታ ምስክር ወረቀት ያወጣል፤
- ተፋሰሶችን እና አረንጓዴ አካባቢዎችን ያስከብራል፤ ይጠብቃል፤ በተፋሰሶች እና በአረንጓዴ አካባቢዎች በፕላንና በዲዛይን ያልተደገፈ ልማት እንዳይካሄድ ይከላከላል፤ ተፈጽሞ ከተገኘ በሕግ መሰረት እንዲወገድ ያደርጋል፤
- በከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን መሰረት የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች እና ፓርኮችን ያለማል፤ ነባርና አዲስ የለሙትን ለህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ያስተላልፋል፤
- የተፋሰሶችን እና የአረንጓዴ አካባቢዎችን ቅደም ተከተል በማውጣት የልማት ወይም መልሶ የማልማት ዝርዝር ፕሮጀክት ያዘጋጃል፤ የተቀናጀ የአረንጓዴ ልማት ቦታ አቀማመጥ ዲዛይን በማዘጋጀት ለፕላንና ልማት ኮሚሽን ያቀርባል፤ ሲጸድቅም ይተገብራል ወይም እንዲተገበር ያደርጋል፤
- የአረንጓዴ ሽፋን ምጣኔ መሰረት የልማት ደረጃ ጠብቆ ወይም አስጠብቆ ያለማል፤ ወይም እንዲለማ ያደርጋል፤ ለወንዝና ለደን ስፍራነት መዋል የሚገባቸው ተጨማሪ ቦታዎች በማጥናት ያቀርባል፤ ሲወሰንም እንዲለሙ ያደርጋል፤ የለሙ ደኖችን ያስተዳድራል፤
- ነባርና አዳዲስ ዘላቂ ማረፊያ ቦታዎችን ያለማል፤የማስዋብ ስራ ያከናውናል፤ ያስተዳድራል፤
- በዘላቂ ማረፊያ የሚፈፀሙ መደበኟ ቀብሮችን መረጃ ይይዛል፤ ያጠናቅራል፤ የቀብር ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤ የአፅም ዝውውር ፈቃድ ይሰጣል፤
- የከተማው አስተዳደር የመንገዶች ባለስልጣን የመንገድ ግንባታ ዲዛይን አካል አድርጎ በሚያዘጋጃቸው የመትከያ ስፍራዎች ዲዛይን መሰረት በዋና እና በመለስተኛ መንገዶች ግራና ቀኝ ዳርቻዎች፣ አካፋዮች እና አደባባዮች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አግባብ ያላቸውን የጥላ ዛፎች እንዲተከሉ ያደርጋል፤ ይተክላል፤ ይንከባከባል፤ ይጠብቃል፤
- የአሽከርካሪዎችን የርቀት እይታ የሚጋርዱ ወይም የደረቁ የመንገድ ዳር፣ አካፋይ እና የአደባባይ ዕጽዋት እንደአስፈላጊነቱ ያስወግዳል ወይም ይመለምላል፤
- የከተማውን አየር ሚዛን የሚጠብቁ እንዲሁም ለከተማው ውበትና መናፈሻ ልማት የሚውሉ የእፅዋት ችግኝ ጣቢያዎችን ያስፋፋል፤ ያስተዳድራል፤ ችግኞችን ለተጠቃሚዎች አግባብ ባለው በህግ ያቀርባል፤
- በከተማው ውስጥ መልማት ያለባቸው በላቀ ሁኔታ ውጤታማ የሆኑና ያልታወቁ ወይም ያልተሞከሩ የውጭ እና ሀገር በቀል የዕፅዋት ዝርያዎችን በማጥናት እንዲለሙ ያደርጋል፤
- በአዲስ የሚለሙና ነባር የለሙ ተፋሰሶችንና አረንጓዴ አካባቢዎችን ይንከባከባል፤ ያስተዳድራል፤ እንዳግባብነቱ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ጋር በማቀናጀት እንዲፈፀም ያደርጋል፣
- በአካባቢ ልማት ፕላን መሰረት የሠፈር ቁርጥራጭ ክፍት ቦታዎች በሠፈሩ ነዋሪዎችና እንደየአግባቡ በሌሎች ባለድርሻዎች ቀጥተኛ ተሳትፎ የከተማው አረንጓዴ ልማት አካል ሆነው እንዲለሙ ያደርጋል፤ ይንከባከባል፤ ይጠብቃል፤ ያስጠብቃል፤
- በተፋሰስና በአረንጓዴ አካባቢዎች ልማትና አገልግሎት ዘርፎች መሠማራት ለሚፈልጉ የግል ባለሀብቶች፣ የሃይማኖት ድርጅቶች፣ ነዋሪዎች ወይም ሌሎች አካላት በየበኩላቸው የሚያቀርቡትን ጥያቄና የልማት ዕቅድ መርምሮ ፈቃድ ይሰጣል፤ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፡፡
- የዝናብ ውሃ በተፋሰስ መነሻ ጥቅም ላይ እንዲውል ወይም እንዲሰርግ ለማድረግ የሚያስችል ጥናት ያካሂዳል፤ ይተገብራል፤
- የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች እንዲገነቡ ያደርጋል፤ ያለማል፤ ያስተዳድራል፤ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የግል ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ያበረታታል፤
- የተፋሰስና አረንጓዴ ልማት ስራዎች ከአካባቢዉ ሥነ ምህዳር የሚስማሙ፣ የአገራችንን ሥነ ምህዳር የሚወክሉና ከአካባቢ ጥበቃ ዓላማዎች ጋር እንዲስማሙ አድርጎ ይፈጽማል፡፡
- የደንብ ማስከበር ኤጀንሲ
ኤጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- በከተማው አስተዳደር ከደንብ ማስከበር ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦችን፣ ስለሚደረጉ ቁጥጥሮች እና ስለሚወሰዱ ዕርምጃዎች በተለያዩ ዘዴዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ያስጨብጣል፤
- የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የደንብ መተላለፍ እና ተያያዥ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዳይፈፀሙ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ በመስራት ደንብ መተላለፍን እንዲቀንስ ያደርጋል፤
- ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ማንኛውንም ሕገወጥ ግንባታ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ መሬት መያዝን፣ መሬት መውረርን እና የመሬት ይዞታ ማስፋፋትን ተግባርን ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፣ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
- ሕገወጥ የመንገድ ላይ ንግድ፣ የእንስሳትና የስጋ ዝውውር፣ ዕርድ፣ ሽያጭ እና ተያያዥ የሆኑ የደንብ መተላለፍ ተግባራትን ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፣ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
- በክፍት እና ዝግ የመናፈሻ ቦታዎች፣ የመንገድ አካፋዬች፣ ዳርቻዎችና አደባባዮች የሚከናወኑ ሕገወጥ ተግባራትን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል እርምጃ ይወስዳል፤
- የትራፊክ እንቅስቃሴ እና ደህንነትን የሚያውኩ እና የሚጋርዱ በመንገድ ወይም በትራፊክ መብራት ላይ የሚከናወን ልመናን፣ በመንገድ ላይ የንግድ ዕቃዎችን ለረዥም ጊዜ ማስቀመጥ፣ ዛፍ ወይም አትክልት መትከል፣ ያለፈቃድ ድንኳን መጣል፣ ብየዳ ማድረግ፣ የተበላሸን ተሽከርካሪ ማቆም፣ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ መጠገን ወይም ማስጠገን፣ ማጠብ ወይም ማሳጠብን እንዲሁም ሌላ ማንኛውም የትራፊክ እንቅስቃሴን የሚያውክ ወይም ለአደጋ የሚያጋልጥ ተግባርን ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በቅንጅት ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ ይወስዳል፤
- መንገዶችን ማሻሻል፣ መቀየር፣ መቀየስ፣ በበር መዝጋት፣ በኬላ ማጠር መቁረጥን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ ይወስዳል፤
- በመንገድ መብራት ምሰሶ፣ በድልድይ፣ በመንገድ ምልክት እና በእግረኛ የመንገድ መከላከያ አጥር ላይ ባነር፣ ማስታወቂያ እንዲሁም በሕገወጥ መንገድ የውጭ ማስታወቂያ መለጠፍ ወይም መትከልን ወይም ማንጠልጠልን ይከላከላል፤ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤
- ሕገወጥ የፈሳሽ እና የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽን ከጎርፍ ማስወገጃ መስመር ጋር ማገናኘትና መልቀቅ፣ ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ማስወገድ፣ የማንሆሎችን ክዳን መክፈት፣ ፉካዎችን እና የጎርፍ ማስወገጃ መስመርን መድፈን ወይም ጉዳት ማድረስን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል እርምጃ ይወስዳል፤
- በትምህርት ተቋማት ዙሪያ ዕፅ መጠቀሚያ ቤት፣ ፊልም ወይም ቪዲዮ ቤት፣ ጭፈራ ቤት፣ መጠጥ ቤት፣ ቁማር ቤት መክፈትን፣ ጫት ማስቃምን ወይም ሺሻ ማስጨስን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ይከላከላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- በጋራ መኖሪያ ቤቶች ህብረተሰቡን የሚያውኩና ህገወጥ ተግባራትን ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት ይከላከላል፤ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት በገንዘብ የሚያስቀጡ የደንብ መተላለፍ ተግባራትን የቅጣት ገቢ ይሰበስባል፣ ህገወጥ ድርጊት የተፈጸመባቸዉን ንብረቶች ይወርሳል፣ በህጋዊ መንገድ ይሸጣል ወይም መወገድ ያለባቸውን ያስወግዳል፤
583 |
ከኤጀንሲው ተልዕኮ አንፃር በደንብ መጣስ ተግባሮች ላይ ቅድመ ጥናት ያደርጋል፣ በጥናቱ የተገኙ ውጤቶችን መሠረት በማድረግ ይፈፅማል፤
- አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የመከላከልና የቁጥጥር ኦፊሰሩን፣ ባለሙያዉን፣ አመራሩን ከማዕከል እስከ ንኡስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት በመመደብ ወይም በማዘዋወር ሊያሰራ ይችላል፤
- በዚህ አንቀጽ ከተደነገጉት በተጨማሪ ሌሎች የደንብ መተላለፍ ጥፋቶችን ይከላከላል፤ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የኤጀንሲውን የፓራ ሚሊተሪ ሰራተኞችን ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ መሰረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፡፡
- የምገባ ኤጀንሲ፤
ኢጀንሲው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፦
- የተማሪዎች ምገባ፣ የመማሪያ ቁሳቁስ እና የትምህርት መርጃ መሳሪያ ድጋፍ ማከናወን የሚያስችል ቀልጣፋና ውጤታማ አሰራር ይዘረጋል፤ ይተገብራል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤ አፈጻጸሙንም ይቆጣጠራል፤
- በቅድመ መደበኛ፣ በመጀመሪያ ደረጃ እና እንደአስፈሊጊነቱ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎች የምገባ ተግባር ያከናውናል፤ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- የተማሪዎች ምገባ፣ መማሪያ ቁሳቁስ፣ ትምህርት መርጃ መሳሪያ እና ደንብ ልብስ ድጋፍ ተጠቃሚ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶችና የተማሪዎች መረጃ ከትምህርት ቢሮ ይሰበስባል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፣ ያሰራጫል፤ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በመንግስት ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ፣ የትምህርት መርጃ መሣሪያ እና የተማሪ ደንብ ልብስ ድጋፍ ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በተማሪዎች ምገባ፣ መማሪያ ቁሳቁስ፣ በትምህርት መርጃ መሣሪያ እና በተማሪ ዩኒፎርም ደንብ ልብስ ድጋፍ በሚመለከት ከተማሪ ወላጆች፣ ከመንግስታዊ ድርጅቶች፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ጋር በትብብርና በቅንጅት ይሰራል፤
- የሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ግብዓት ያቀርባል፣ ያሰራጫል፤
- የከፋ የምግብ ችግር ያለባቸው ህጻናት፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የአዕምሮ ህመምተኞች እና መሰል የህብረተሰብ ክፍሎች ምገባ ማከናወን የሚያስችል ውጤታማ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፤ ይተገብራል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤ አፈጻጸሙንም ይቆጣጠራል፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ (8) የተጠቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎች በተመለከተ መረጃ ይሰበስባል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፣ ያሰራጫል፤ ጥቅም ሊይ እንዲውል ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ (8) የተጠቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ ከስርዓተ ጾታና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ መረጃ ይሰበስባል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፣ ያሰራጫል፤ ጥቅም ላይ እንዲውል ያደርጋል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ (8) ለተጠቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ፣ የገንዘብ እና ሌሎች ግብዓቶችን የሚደግፉ አካላትን ይለያል፤ ድጋፍ የሚያደርጉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤ ድጋፍ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን ያበረታታል፤ ዕውቅና ይሰጣል፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ (8) ለተጠቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎች የምገባ ተግባር ያከናውናል፤ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤
- የምገባ ኘሮግራሙ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም ጋር በማቀናጀት እንዲፈፀም ያደርጋል፣
- የምገባ ፕሮግራሞች በተጠቃሚዎች ጤንነት፣ ንጽህና ጥበቃና የስርዓተ ምግብ መሻሻል ላይ ያተኮረ መሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያረጋግጣል፤
- የምገባ ተጠቃሚዎች ያሉባቸው ማህበራዊ ችግሮች እንዲፈቱላቸውና ከድጋፉ እንዲወጡ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፤ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
- የምግብ ማዘጋጃ እና መመገቢያ ህንጻ ያስገነባል፤ ተገቢውን ግልጋሎት እየሰጠ መሆኑን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
- ከተልዕኮው አኳያ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፣ ጥናቱ በጥቅም ላይ እንዲውል ይከታተላል፤
- የምገባ ማዕከላትን በበላይነት ይመራል፤ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል፤
- የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት
የከተማው ካቢኔ በሚያወጣው ደንብ የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሆኖ እስኪቋቋም ድረስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት በተቋቋመበት ህግ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሰረት ስራውን ይቀጥላል፡፡
- የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት
የከተማው ካቢኔ በሚያወጣው ማሻሻያ ደንብ የትላልቅ ግንባታዎች ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሆኖ እስኪቋቋም ድረስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት በተቋቋመበት ህግ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሰረት ስራውን ይቀጥላል፡፡
- ስለኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ
በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩንቨርሲቲ በተቋቋመበት ሕግ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሰረት ስራውን ይቀጥላል፡፡
- አዲስ አበባ የስራ አመራር ኢንስቲትዩት
ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አፈጻጸም መነሻ ያደረገ የስልጠና ፍላጎት ጥናት በማድረግ ሰው ሀብት በብቃት ማፍራት የሚያስችል የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ስልጠናዎችን ይሰጣል፤
- የስልጠና መርሀ ግብር ይቀርፃል፤ ሞጁሎች ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የተቋማትን፣ የአመራርንና የባለሙያውን የማስፈፀም አቅም ለመገንባት የሚረዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ይሰራል፤ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ከመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ወይም የግል ድርጅቶች በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት ለአመራርና ባለሙያ የሥልጠና፣ የምክርና የማህበረሰብ አገልግሎት ይሰጣል፤
- ሥልጠና ጨርሰው በስራ የተሰማሩ አካላትን የስልጠና ዉጤታማነት ጥናት ያካሂዳል፤ ከጥናቱ በመነሳት የተሻሉ የአሰራር ስልቶችን ይቀይሳል፤
- የተለያዩ ሴሚናሮችን፣ ወርክ ሾፖችን፣ ኮንፈረንሶችንና አውደ ጥናቶችን ያዘጋጃል፤ ያካሂዳል፤ በሌሎች ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ላይ ይሳተፋል፤
- ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰርተፍኬት ይሰጣል፤
- የሥራ አመራር ሥልጠና፣ የምክር አገልግሎትና የጥናት ፕሮጀክቶችን በማዘጋጀት ገቢ የሚያገኝባቸዉን ሁኔታዎች ያመቻቻል፡፡
- የማህበራዊ ትረስት ፈንድ፤
በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በማህበራዊ ትረስት ፈንድ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 106/2011 በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሰረት ስራውን ይቀጥላል፡፡
- የኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት
ጽህፈት ቤቱ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የከተማ አስተዳደሩ ቃል አቀባይ በመሆን እና የአስተዳደሩ ዋነኛ የመረጃ ምንጭ በመሆን ይሰራል፤ በከተማ አስተዳደሩ ጉዳዮች ላይ የአስተዳደሩን አቋም ለህዝብ ይፋ ያደርጋል፤ በየደረጃው ያለው የመረጃና የመረጃ ልውውጥ መዋቅር ወይም የየከተማው አስተዳደር ኮሙኒኬሽን አካል ለየተመደበበት የአስተዳደሩ አደረጃጀት በቃል አቀባይነት ኃላፊነቱን የሚወጣበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- ለከተማው አስተዳደር የመረጃና የመረጃ ልውውጥ ወይም ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስራ አመራር ይሰጣል፣ በመስኩም በየደረጃው የተሳለጠ አፈፃፀም የሚኖርበትን ሥርዓት ይዘረጋል፣ በየደረጃው ለሚከናወነው የከተማው አስተዳደር መረጃ ሥርዓትና ልውውጥ ሥራ አቅጣጫ በመስጠት ያስተባብራል፤
- አስተዳደሩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሃገር ውስጥም ሆነ ለውጪ ሚዲያ አካላት መግለጫዎችን ይሰጣል፤ ከሚዲያዎች ጋር የተሳለጠ ተግባቦት እንዲኖር ያደርጋል፤ የከተማዉን ገፅታ ለመገንባት እና ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የትኛውንም ሚዲያ እና ድህረ ገጽ ይጠቀማል፤
- በከተማው የአስተዳደሩ ተቋማት ውስጥ ያሉ የህዝብ ግንኙነት ዳይሪክተሮች በከተማ አስተዳደሩ በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት በሜሪት እንዲመደቡ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤
- የድህረ ገፅና ማህበራዊ ሚዲያ ለማልማት፣ ሥራዎችን ያቅዳል፣ ያስተባብራል ይመራል፣ አሠራሮችን ይቀምራል፣ ይዘቶችን ይተነትናል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ግንኙነቶችን ያጠናክራል፣ ተደራሽነታውን ያሰፋል፤ በየመሥሪያ ቤቱ የሚከናወኑ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት፣ ስርጭትና ክትትል ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- ለከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች፤ አመራሮችና ኮሚኒኬተሮች በየደረጃው ካለ መንግሰታዊ መዋቅር ጋር ጠንካራ የግንኙነት ሥርዓት በመዘርጋት የአቅም ግንባታ ድጋፎችን ይሰጣል፤ በመስኩ መልካም አፈፃፀም የሚመዘገብበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤ አቅጣጫ ያስቀምጣል፤
- የብዙሐን መገናኛ የዕለት ተዕለት ዘገባ ቅኝት እና መረጃዎችን በመሰብሰብ ይተነትናል፣ ጥናታዊ ስራዎችን በማከናወን ለሚመለከታቸው አካላት ያሠራጫል፤
- በከተማው ላይ የሚነሱ የተሳሳቱ መረጃዎች በመነሳት ህብረተሰቡ ትክክለኛውን መረጃ እንዲያገኝ ያደርጋል፤ ጉዳዮ የሚመለከታቸው ተቋማትም ጉዳዩን በተመለከተ ትክክለኛውን መረጃ እንዲሰጡ ይከታተላል፤ ያስፈፅማል፤
- የተለያዩ ሃገራዊ እና ከተማዊ ሁነቶችን መሠረት በማድረግ ከሚሰበሰቡ የህዝብ አስተያየት ጥናቶች በመነሳት በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀት አመራሩ ህብረተሰቡን በአካል አግኝተው እንዲያነጋግሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ መድረክ ይፈጥራል፤ ተግባራዊና ውጤታማ መሆናቸውንም ይከታተላል፤
- በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን በመሰብሰብ ይተነትናል፤ ያስተነትናል፤ የኮሙኒኬሽን ስራ መነሻ ያደርጋል፤ ለሚመለከታቸው አካላት ያደርሳል፤
- ልዩ ልዩ የህትመትና የኦዲዮ እና አውዲዮ ቪዝዋል ዉጤቶችን ማዘጋጀት፤ የአስተዳደሩ መሥሪያ ቤቶች የፎቶ ግራፍ፣ የኦዲዮ ቀረፃና የዓርማ እና የህትመት ዲዛይን ፖለቲካዊ፤ ህጋዊና ማህበረሰባዊ የሞራል ጥያቄ የማያስነሱ መሆናቸውን እና ከተቀመጠለት ዓላማ የተገናዘበ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የማዘጋጀትና የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
- በኮሙዩኒኬሽን ሥራ ዙሪያ በሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ባላድርሻ አካላትና በዙሪያው የዳበረ እውቀትና የካበተ ልምድ ያላቸው ግለሰቦች መካከል በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የአጋርነት ሥርዓት ይዘረጋል፤
- በሥራው ልዩ ባህሪ ምክንያት የተለየ ሙያ ያለው የሰው ሀይል በልዩ ሁኔታ መቅጠር አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቅጥሩን ለከንቲባ በማቅረብ ያስወስናል፤ ሲፈቀድም ያስፈፅማል፤
- በከተማው አስተዳደር የመረጃ ስርጭትና የመረጃ ልውውጥ ዙሪያ ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፤ የህዝብ አስተያየት ቅኝትና ጥናት ያከናውናል፣ በኮሙዩኒኬሽን፣ ኢንፎርሜሽንና ሚዲያ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፤
- በከተማው አስተዳደር ውስጥ የሚዲያ መሰረተ ልማት የሚጠናከርበትን፣ የሚስፋፋበትን፣ በተገቢው ቴክኖሎጂና ብቃት ባለው የሰለጠነ ባለሙያ የሚደራጅበትን ሥርዓት ይቀይሳል፤
- ንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በራሱ ስም ይከሳል፡ ይከሰሳል፤
- ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል
በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል በተቋቋመበት ሕግ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሰረት ስራውን ይቀጥላል፡፡
- ስለከተማው አስተዳደር የልማት ድርጅቶች
- በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት የከተማው አስተዳደር የልማት ድርጅቶች በተቋቋሙበት ህግ መሰረት ስራቸውን ይቀጥላሉ፡-
ሀ) የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት፤
ለ) የቄራዎች ድርጅት፤
ሐ) የኤግዚቢሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት፤
መ) የሲኒማ ቤቶች አስተዳደር፤
- የሚከተሉት የልማት ድርጅቶች ካቢኔ በሚያወጣው ደንብ መሰረት ተጠሪነቱ ለትራንስፖርት ቢሮ የሆነ አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በሚል ስያሜ እስከሚቋቋም ድረስ በተቋቋሙበት ህግ መሰረት ስራቸውን ይቀጥላሉ፡-
ሀ) አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት፤
ለ) ሸገር የብዙሀን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት፤
- የግንባታ ኢንተርፕራይዝ ካቢኔ በሚያወጣው ደንብ መሰረት ተጠሪነቱ ለዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሆኖ አዲስ አበባ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት በሚል ስያሜ እስከሚቋቋም ድረስ በተቋቋመበት ህግ መሰረት ስራውን ይቀጥላል፤
- የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ካቢኔ በሚያወጣው ደንብ መሰረት በልማት ድርጅትነት ይቋቋማል፤ ተጠሪነቱም ለከተማ ስራ አስኪያጅ ይሆናል፤
- አዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ባለቤትነቱ ለከተማ አስተዳደሩ ሲተላለፍ የከተማው ካቢኔ በሚያወጣው ደንብ የልማት ድርጅት ሆኖ ይቋቋማል፤ ተጠሪነቱም ለትራንስፖርት ቢሮ ይሆናል፤
- በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ (1) የተጠቀሱት የልማት ድርጅቶች ስምና አደረጃጀት ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ ሊሻሻል ወይም ሊቀየር ይችላል፡፡
- ስለከተማው አስተዳደር ጤና ተቋማት፣ ኮሌጆችና ማዕከላት
በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚተዳደሩ የጤና ተቋማት፣ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ማዕከላት በየራሳቸው ህጎች መሰረት ስራቸውን ይቀጥላሉ፡፡
ክፍል አምስት
ስለ ክፍለ ከተማዎች
ምዕራፍ አንድ
የክፍለ ከተሞች አከላለል፣ ወሰንና ተጠሪነት
- የክፍለ ከተማ የአከላለል መሠረት
የክፍለ ከተማ አከላለል የቆዳ ስፋትን፣ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥን፣ የነዋሪ ብዛትን፣ የልዩ ልዩ አገልግሎት ተደራሽነትና የሀብት ስርጭትንና የአስተዳደር አመችነትን መሠረት ያደረገ ነው፡፡
- የክፍለ ከተማ ወሰን
የክፍለ ከተማ ወሰን በአዲስ አበባ ከተማ የአከላለል ካርታ ላይ ተለይቶ በተገለፀው መሠረት የተወሰነው ይሆናል፡፡
- የክፍለ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነት
የክፍለ ከተማ አስተዳደር ተጠሪነት ለነዋሪውና ለከተማው አስተዳደር ይሆናል፡፡
ምዕራፍ ሁለት
የክፍለ ከተማ የአስፈጻሚ አካላት ሥልጣን፣ ተግባር እና ተጠሪነት
- የክፍለ ከተማ አስፈጻሚ አካላት ሥልጣንና ተግባራት
ክፍለ ከተማው ከከተማው አግባብ ያለው አስፈጻሚ አካል ሥልጣንና ተግባር አኳያ በተዋረድ በተደራጀ ወይም በሚደራጅ አስፈጻሚ አካል የሥራ መስክ ተከፋፍሎ የሚከናወኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- በክፍለ ከተማው የሚገኙ ወረዳዎችን በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ የማስፈጸም አቅም ይገነባል፤
- የክፍለ ከተማውን አጠቃላይ ዕቅዶች፣ መርሐ-ግብሮችና ኘሮጀክቶች ያዘጋጃል፤ በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
- ፖሊሲ፣ ሕግ፣ ደረጃና የአስተዳደሩ የበላይ አካላት ውሣኔዎች በክፍለ ከተማው ተግባራዊ መሆናቸውንና የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ መጠበቁን ያረጋግጣል፤
- የተፈቀደለትን በጀት ይደለድላል፤ በሥራ ላይ ያውላል፤ አፈጻጸሙ በከተማው አስተዳደር የፋይናንስ አስተዳደር ሕግ መሠረት መሆኑን ይከታተላል፤
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት ግብር፤ ቀረጥና የአገልግሎት ክፍያ ይሰበስባል፤ የክፍለ ከተማው ገቢ የሚያድግበትን ሁኔታ ያጠናል፤ ሲፈቀድ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- የክፍለ ከተማው አስፈጻሚ አካላት ሥራን ይመራል፤ ያስተባብራል፤
- በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- የክፍለ ከተማውን የመንግሥት ሠራተኞች አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤ያሰናብታል፤
- በክፍለ ከተማው ውስጥ የሕዝብን ተሳትፎ ያሳድጋል፤ የብዙሃን ማህበራትን አቅም ይገነባል፤
- አነስተኛ ነጋዴዎችን፤ የዕደ ጥበብ ባለሙያዎችን፣ ስራ ፈላጊዎችን እና ሌሎች አካላት በማህበር እንዲደራጁ ድጋፍ ይሰጣል፣ አሠራራቸውንም ይቆጣጠራል፤
- የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ ይተገብራል፡ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ያስተባብራል፤ ተገቢውን ክትትል ያደርጋል፤
- የመንግስትና የግል የትምህርት ቤቶችን እና የቴክኒክና የሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማትን በበላይነት ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤
- በክፍለ ከተማው የመንግሥት ፖሊሲና ሕጐች እንዲሁም የአስተዳደሩ የሥራ እንቅስቃሴ እንዲተዋወቁ ያደርጋል፤
- ታሪካዊ ቅርሶችን ይጠብቃል፤ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ሥነ-ጥበብ እንዲበለጽጉ ያደርጋል፤
- የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎችን ያስተዳድራል፤ ስፖርት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስፋፋል፤ ወጣቶች ተገቢውን ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋል፤
- በልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች የሴቶችና የወጣቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ያረጋግጣል፤
- የአካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ የማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እና በደማቸው ውስጥ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ያለባቸው ሰዎች የእኩል እድል ተጠቃሚና ሙሉ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
- ጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ተግባራትን ያከናውናል፤ በክፍለ ከተማው የሚገኙ የአስተዳደሩን ጤና ጣቢያዎችንና ክሊኒኮችን ያስተዳድራል፣ የግል ክሊኒኮችን ይቆጣጠራል፤
- ኤች.አይ.ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚንቀሳቀሱ ተቋማትን ያስተባብራል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፤
- የመሠረተ ልማት አገልግሎቶች ለነዋሪው እንዲዳረሱ ያደርጋል፤ ያስተዳድራል፤ ተገቢውን ጥበቃና ቁጥጥር ያደርጋል፤ የመንገድ ግንባታና ጥገና ሥራዎች እንዲካሄድ ያደርጋል፤ የትራፊክ ደህንነትን ያስጠብቃል፤
- ሕገወጥ ግንባታዎችን ይከላከላል፤ ያስወግዳል፤ በክፍለ ከተማው ባለቤትነት ሥር ያሉ ቤቶችን ያስተዳድራል፤ ይቆጣጠራል፤
- ሕገ ወጥ ተግባራትን ይከላከላል፤ ይቆጣጠራል፤ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የከፍለ ከተማው ነዋሪዎች የስራ ዕድል መፍጠር እንዲችሉ ስልጠናዎች ይሰጣል፤ ተሞክሮዎችን በመለየትና በመቀመር ዕውቀትና ክህሎት እንዲቀስሙ ያደርጋል፤ ያበረታታል፤ የንግድ ስራ ክህሎት የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤ የስራ ዕድል እንዲፈጠር ያመቻቻል፤
- የጥቃቅንና አነስተኛ መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይሠጣል፤
- የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ በአግባቡ ማካሄድ የሚያስችላቸው የሙያዊ ድጋፍና ክትትል፣ የብድር፣ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ አገልግሎትና የገበያ ትስስር ያመቻቻል፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች አገልግሎት እንዲውሉ የተዘጋጁ ነባር የመስሪያ ቦታ የሆኑ ህንጻዎች፣ ሼዶች፣ ተለጣፊ ሱቆች እና ኮንቴነሮች እንዲሁም በመንግስት፣ በግልና በተለያዩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች የተገነቡ መደብሮችን ያስተዳድራል፤
- በአሰሪና ሠራተኛ መካከል የሥራ ቦታ ሰላም እንዲሰፍን የትምህርትና የሥልጠና አገልግሎት ይሰጣል፣ የሙያ ምክር አገልግሎት ስለሚስፋፋበት፣ ክፍት የሥራ መደቦች ይመዘግባል፤ ሥራና ሠራተኛ ያገናኛል፤
- የአካባቢ ጥበቃ ሕጎችን መሠረት በማድረግ የማምረቻና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ሌሎች አካባቢ ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ አካላትን ይቆጣጠራል፤ የአካባቢ ንጽህና እና ውበት እንዲጠበቅ ያደርጋል፤
- የይዞታ አስተዳደርን በተመለከተ፡-
ሀ) በከተማው መዋቅራዊ ኘላንና በአካባቢ ልማት ኘላን ሕጐች መሠረት የቦታ ይዞታ እና/ወይም የቤት ባለቤትነት ማስረጃ ካርታ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ በቋሚ ንብረት መዝገብ በመመዝገብ ለባለይዞታው ወይም ለቤት ባለንብረቱ ይሰጣል፤ ከሕግ ውጪ የተሰጠ የቦታ ይዞታ ወይም የቤት ባለቤትነት ማስረጃ አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ያግዳል፣ እንደአስፈላጊነቱ ይሰርዛል፤
ለ) የቦታ ይዞታ ወይም የቤት ባለቤትነት ስም ዝውውር አግባብ ባለው ሕግ መሠረት እንዲፈፀም ያደርጋል፤
ሐ) የቦታ ይዞታ ወይም የቤት ባለቤትነት መያዣ ዋስትና፣ እንዲሁም የፍርድ ቤት ወይም ሥልጣን ባለው አካል የተሰጠ ዕግድ ትዕዛዝ መመዝገብና ዋስትናው ወይም የዕግድ ትዕዛዙ ሳይነሳ ወይም ጊዜው ሳያበቃ የስም ዝውውር እንዳይፈፀም ያደርጋል፤
መ) በባንክ በዋስትና የተያዘ ይዞታን ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት በባንክ በመያዣ ስለተያዘ ንብረት xGÆBbxxአግባብ ባለው ህግ መሰረት ይመዘግባል፤
ሠ) በባለይዞታዎች መካከል የወሰን ክርክሮች ሲከሰቱ በኘላኑ መሠረት አስተዳደራዊ ውሣኔ ይሰጣል፤ ተፈጻሚ ያደርጋል፤
ረ) በቦታ ይዞታው እና/ወይም በቤት ባለቤትነት መረጃ ላይ የተደረጉ ለውጦች ሕጋዊ መሆናቸውንና በሕግ ሥልጣን በተሰጠው አካል ፀድቀው የተፈፀሙ መሆናቸውን በየወቅቱ ያረጋግጣል፤
ሰ) የቦታ ይዞታ እና/ወይም የቤት ባለቤትነት አስተዳደር ሥራዎች አግባብ ባለው ህግ መሠረት እንዲከናወኑ ያደርጋል፤
ሸ) የቦታ ይዞታ እና/ወይም የቤት ባለቤትነት ማህደሮችን እንዲደራጁ፤ እንዲጠበቁና የአዳዲስ ይዞታ ማኀደራት ሠነዶች ግልባጮችን በወቅቱ ለሚመለከተው አካል እንዲተላለፉ ያደርጋል፤
ቀ) የሕንፃ ግብርና የቦታ ኪራይ ማስከፈያ ሰነድ በማዘጋጀት ለየወረዳው ያስተላልፋል፣ ይከታተላል፤
በ) በካዳስተር መረጃ የተመዘገበ ቦታና ቤት እንዲለካ፤ የአዲሱ ልኬት መረጃ ወደ ኮምፒውተር እንዲገባ፤ የቦታ ቤዝ ማኘ እንዲደራጅ እና እንዲመዘገብ ያደርጋ፡፡
- በክፍለ ከተማው የሚገኙ ቦታዎችን የሚያስተዳድር ሆኖ፤
ሀ) የመሬት ልማትን በተመለከተ፡-
- የከተማውን መዋቅራዊ ኘላን መሠረት በማድረግ የአካባቢ ልማት ኘላን ያጠናል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤ የመሬት ልማት ሥራ ያከናውናል፤ እንደአስፈላጊነቱ የመሬት ልማት ሥራዎችን ከሚያከናውኑ መንግሥታዊ ወይም የግል ድርጅቶች ጋር አግባብ ባለው ህግ ይዋዋላል፤ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤
- የአካባቢ ልማት ኘላኖችን ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ የክፍለ ከተማው መሬት የሚለማበትን ዝርዝር የአፈጻጸም ስትራቴጂ ይነድፋል፤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- በከተማው አስተዳደር ለሚቀርቡ የቦታ ጥያቄዎች አግባብ ባለው ሕግ ቦታ ማስለቀቅና እንደየሥልጣኑ አግባብ በከተማው ማዕከል ወይም በክፍለ ከተማው በሚወሰነው መሠረት ምትክ ቦታ ይሰጣል፤ ካሣ እና ሌሎች ክፍያዎችን ይፈፅማል፣ ምትክ ቤት ይሰጣል፤
- የካሣ ክፍያ በተከፈለባቸውና በተለቀቁ ወይም በክፍት አካባቢዎች ላይ የቅየሳና የኘላን አፈጻጸም ሥራዎች ያከናውናል፤ ቦታዎቹን ለልማት ዝግጁ ያደርጋል፤ የአፈጻጸም ሪፖርትና ለመሬት ዝግጅት የሚያስፈልግ በጀትና ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፣ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤
- መረጃ በመሰብሰብ በልማት ምክንያት ለሚነሱ ቤቶች የካሣ ክፍያ ሠነድ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤ ሥልጣን ባለው አካል በሚወሰነው መሠረት ካሣ ክፍያ የተፈፀመባቸውን ንብረቶች እንዲነሱ ያደርጋል፤
- ምትክ ቦታ፣ በምትክ መኖሪያ ቤት እና/ወይም በጥሬ ገንዘብ ለሚከፈል ካሣ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ያጠናቅራል፤ ተንትኖም ያቀርባል፤ ሲወሰንም ተግባራዊ ያደርጋል፤
- ምትክ ቦታ ለሚገባቸው ተነሺዎች ምትክ ቦታ ማዘጋጀትና የይዞታ ማስረጃ/ካርታ በማዘጋጀት ያስረክባል፤
- ምትክ የመኖሪያ ቤት ለሚገባቸው ተነሺዎች ቤት በማዘጋጀት ያስረክባል፡፡
ለ. የሊዝ አፈጻጸምን በተመለከተ ፡-
- አግባብነት ባላቸው ህግ መሠረት ለማናቸውም ግንባታ የሚውል ቦታ ያስተላልፋል፤ የሊዝ ውል ይዋዋላል፤ ቦታውን ያስረክባል፤
- በተፈረመው የሊዝ ውልና በተፈቀደው የግንባታ ኘላን መሠረት ግንባታ መከናወኑን ያረጋግጣል፤ አግባብ ባለው ሕግና በውሉ በተወሰነው ጊዜና ሁኔታ ግንባታ ካልተጀመረ ወይም ካልተጠናቀቀ በቦታ ሊዝ ሕግ መሠረት ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- በተፈረመው የሊዝ ውል መሠረት ክፍያ በአግባቡና በወቅቱ መፈፀሙን ያረጋግጣል፤
- በሊዝ ለልማት የሚመደቡ ቦታዎችን በተመለከተ የአፈጻጸም ሪፖርት ያቀርባል፤
- የክፍለ ከተማ የሥልጣን አካላት
- እያንዳንዱ ክፍለ ከተማ የሚከተሉት የአስፈጻሚ የሥልጣን አካላት ይኖሩታል፡-
ሀ. የክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤
ለ. የክፍለ ከተማ ቋሚ ኮሚቴ፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ሥር የተዘረዘሩት አካላት በዚህ አዋጅ የተሰጡት ስልጣንና ተግባራት እንደተጠበቁ ሆኖ በቻርተሩ አንቀጽ 34 እስከ 36 የተመለከቱትን ስልጣንና ተግባራት ያከናውናሉ፡፡
ምዕራፍ ሦስት
ስለ ክፍለ ከተማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ ስለ ሌሎች አስፈጻሚ አካላት
- የክፍለ ከተማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት
- የሚከተሉት የክፍለ ከተማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ይሆናሉ፤
ሀ. የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣
ለ. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ከተራ ቁጥር 2 እስከ 18 ከተቋቋሙት አስፈፃሚ አካላት መካከል በክፍለ ከተማ ደረጃ የተደራጁ የአስፈጻሚ አካላት ኃላፊዎች፤
ሐ. ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንደአስፈላጊነቱ በአባልነት እንዲሳተፉ የሚመርጣቸው የክፍለ ከተማው ሌሎች ኃላፊዎች፡፡
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 1 (ለ) ሥር የተጠቀሰው አስፈጻሚ አካል ኃላፊ በቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ሊገኝ በማይችልበት ጊዜ በግልጽ ተለይቶ ውክልና የተሰጠው ኃላፊ በተተኪ አባልነት በቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይሳተፋል፡፡
- የክፍለ ከተማ አስፈጻሚ አካላት
- በዚህ አዋጅ አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ (2) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ለዋና ሥራ አስፈጻሚው ተጠሪ የሆኑና የክፍለ ከተማው ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሚሆኑ ጽህፈት ቤቶች ባልተማከለ መርህ መዋቅራዊ የሥራ ክፍፍል በሚወሰነው መሠረት የአስፈጻሚ አካላት ተዋረዳዊ አደረጃጀት አካል ሆነው ይደራጃሉ፡፡
- በዚህ አዋጅ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ለማስፈጸም በጸደቀ ወይም በሚጸድቅ መዋቅራዊ አደረጃጀት ተዋረዳዊ ኃላፊነት ይኖሩታል፡፡
ሀ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የሚደራጅ እያንዳንዱ ጽህፈት ቤት እንደአግባቡ ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪ ይሆናል፤
ለ. የእቅድና በጀት ዝግጅት፣ የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ፣ የሠራተኞች ውስጥ ዝውውርና የደረጃ ዕድገትን ጨምሮ ሌሎች ሙያዊና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በሥራው መስክ ለሚመለከተው ቢሮ ተጠሪ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማው ማዕከል ተከትሎ በሥሩ የሚደራጁትን ሌሎች ጽህፈት ቤቶች፣ ዳይሬክቶሬቶች ወይም የሥራ ክፍሎች በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤
ሐ. እያንዳንዱ ጽሕፈት ቤት ወይም በክፍለ ከተማው ደረጃ የሚቋቋም የአስፈጻሚ አካል ኃላፊ፣ የሥራ ክፍሎችና ሠራተኞች ይኖሩታል፤
መ. የክፍለ ከተማ ጽሕፈት ቤቶች ከሚያስተባብሯቸው አስፈጻሚ አካላት ድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶችን በጋራ ሊጠቀሙ ይችላሉ፤ ዝርዝሩ የከተማው ካቢኔው በሚጸድቀው መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በከንቲባው በሚያወጣ መመርያ ይወሰናል፤
ሠ. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) እስከ (2) እና በሕግ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአስፈፃሚ አካላት ኃላፊዎች የሥራ ሁኔታ ካቢኔው በሚያወጣው ደንብ ይወሰናል፡
ረ. በዚህ አዋጅ አንቀጽ 82 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት የተደራጁ የክፍለ ከተማ አስፈጻሚ ተቋማት የራሳቸውን በጀት ጥያቄ አዘጋጅተው ለዋና ስራ አስፈጻሚ ያቀርባሉ፤ ሲፈቀድላቸው በህግ አግባብ ስራ ላይ ያውላሉ፤ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋሉ፡፡
- የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ
የክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ተጠሪ የሆኑለትን የክፍለ ከተማ አስፈፃሚ አካላት ዕቅድና በጀት ከከተማው ሥራ አስኪያጅ ጋር በመመካከር በማዘጋጀት ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያቀርባል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን አዘጋጅቶ ለከተማው ሥራ አስኪያጅና ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያቀርባል፡፡
ክፍል ስድስት
ስለ ወረዳዎች
- የወረዳ ሥልጣንና ተግባር
ወረዳው ከክፍለ ከተማው አግባብ ያለው አስፈጻሚ አካል ሥልጣንና ተግባር አኳያ በተዋረድ በተደራጀ ወይም በሚደራጅ አስፈጻሚ አካል የሥራ መስክ ተከፋፍሎ የሚከናወኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
- የወረዳውን በጀትና ዕቅድ በማዘጋጀት ለክፍለ ከተማው አስተዳደር ያቀርባል፤ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮችን ግብር ይሰበስባል፤ አግባብ ባለው ህግ መሠረት የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ክፍያዎች ይሰበስባል፤
- የወሳኝ ኩነትና የነዋሪዎች ምዝገባ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ይሰጣል፤
- ነዋሪዎች በህብረት ስራ ማህበር እንዲደራጁ ያበረታታል፤ ያደራጃል፤
- ወረዳዎች የልማትና የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፤
- የህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተሳትፎ በማጠናከር በልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፤የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ያስተባብራል፤
- የወረዳውን የመንግሥት ሠራተኞች አግባብ ባለው ሕግ መሰረት ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤ያሰናብታል፤
- በወረዳ ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች ግልጽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
- የአካባቢው የልማት ሥራዎች የከተማውን ኘላን፤ የግንባታ ሕጐችንና ደረጃዎችን ጠብቀው መሠራታቸውን እንዲሁም ሕገ ወጥ ግንባታዎችን ይቆጣጠራል፤
- ሕገ ወጥ ድርጊቶች እንዳይካሄዱ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፤ ፀጥታ ሥራዎችን ይከታተላል፤ ነዋሪውን በኮሚኒቲ ፖሊሲንግ እንዲሳተፉ ያደርጋል፤
- ነዋሪው የአካባቢውን ጽዳት እንዲጠብቅና እንዲያስውብ ያስተባብራል፤ ይቆጣጠራል፤
- የነዋሪዎችን ተሳትፎ ለማጐልበት የተለያዩ ብዙሃን ማኀበራትና ማኀበራዊ ተቋማት እንዲደራጁ ድጋፍ ይሰጣል፤ ያስተባብራል፤
- የጥቃቅንና አነስተኛ መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይሠጣል፤በስራ ዕድል ፈጠራና በዕደጥበብ ሥራ ላይ የተሰማሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በማኀበር እንዲደራጁ ያበረታታል፤ ያደራጃል፤
- የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ በአግባቡ ማካሄድ የሚያስችላቸው የሙያዊ ድጋፍና ክትትል፣ የብድር፣ የካፒታል ሊዝ ፋይናንስ አገልግሎትና የገበያ ትስስር ያመቻቻል፣ የመስሪያና መሸጫ ቦታ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
- የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ፣ እድሳት እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ የንግድ እንቅስቃሴውን ይቆጣጠራል፤
- የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲያድግ፣ የህብረተሰቡ ማህበራዊ ችግሮች እንዲፈቱ ህብረተሰቡን በማስተባበር ይሰራል፤
- አፀደ ሕፃናትንና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ መሠረተ-ትምህርት እንዲስፋፋ ያደርጋል፤
- ክፍት ቦታዎችና የመሬት ይዞታ ሁኔታ የተሟላ መረጃ ይይዛል፤ በከተማው አስተዳደር ባለቤትነት ሥር ያሉ ቤቶች በቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በሚቀርበው ሠነድ መሠረት ያስተዳድራል፤
- በይዞታነት ለማንም አካል ያልተላለፉ የተዘጋጁና ያልተዘጋጁ ቦታዎችን ይጠብቃል፤ ህገወጥነት ተፈፅሞ ሲገኝም ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
- የከተማ ማደስ ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት የወረዳው አስፈጻሚ አካላት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ሁሉ ይፈጽማሉ፤
- ተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎችን፣ አነስተኛ ፓርኮችንና መዝናኛ ሥፍራዎችን ይጠብቃል፤ ይቆጣጠራል፤
- የወረዳውን የተደራጀ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃ ይይዛል፤ ለሚመለከተው አካል ሲጠየቅ ያቀርባል፡፡
- የወረዳ የሥልጣን አካላት
እያንዳንዱ ወረዳ የሚከተሉት የአስፈጻሚ የሥልጣን አካላት ይኖሩታል፡-
ሀ. የወረዳ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤
ለ. የወረዳ ቋሚ ኮሚቴ፡፡
- ስለወረዳ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
- የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከወረዳ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ይመረጣል፤ የሥራ ዘመኑም የምክር ቤቱ የስራ ዘመን ይሆናል፤ ሆኖም በራሱ ፈቃድ ሲለቅ ወይም በምክር ቤቱ ከኃላፊነት ሲታገድ የስራ ዘመኑ ሳያልቅ ከኃላፊነት ሊሰናበት ይችላል፤
- የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተጠሪነቱ ለወረዳው ምክር ቤትና ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ ወረዳውን ይመራል፤
- የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /፪/ አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዋና ሥራ አስፈጻሚው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ሀ. የቋሚ ኮሚቴ አባላትን ከምክር ቤት አባላት ወይም የምክር ቤት አባላት ካልሆኑት መካከል መርጦ ለወረዳው ምክር ቤት በማቅረብ ሹመታቸውን ያፀድቃል፤
ለ. የወረዳው ዓመታዊ ዕቅድና የበጀት ድልድል ሃሳብ በወረዳው ቋሚ ኮሚቴ ከተመከረበት በኋላ ለወረዳው ምክር ቤት ያቀርባል፣ የወረዳውን የገቢ ማሰባሰብ በበላይነት ይመራል፤
ሐ. የወረዳውን ቋሚ ኮሚቴ ይሰበስባል፤
መ. በወረዳው ሕግና ሥርዓትን ያስከብራል፤ የወረዳውን የፀጥታ ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፤ ከወረዳው አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ያሳውቃል፤
ሠ. የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት በወረዳው ቋሚ ኮሚቴ እንዲገመገም ያደርጋል፤ ውጤቱን ለወረዳው ምክር ቤት እና ለክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪፖርት ያደርጋል፤
ረ. በብሔራዊና በሕዝብ በዓላት ሥነ-ሥርዓቶች ላይ እንደአስፈላጊነቱ ወረዳውን ይወክላል፤
ሰ. ዓመታዊና ወቅታዊ ሪፖርት ለክፍለ ከተማው ሥራ አስፈጻሚና ለወረዳው ምክር ቤት ያቀርባል፤
ሸ. በወረዳው ምክር ቤትና በክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
- ስለወረዳ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ
1.የወረዳ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከወረዳ ምክር ቤት አባላት ወይም ከምክር ቤት አባላት ውጪ ሊመረጥ ይችላል፡፡
2.የወረዳ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ የስራ ዘመን የምክር ቤቱ የስራ ዘመን ይሆናል፤ ሆኖም በራሱ ፈቃድ ሲለቅ ወይም በምክር ቤቱ ከኃላፊነት ሲታገድ የስራ ዘመኑ ሳያልቅ ከኃላፊነት ሊሰናበት ይችላል፡፡
- ስለወረዳ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሥልጣንና ተግባር
- ከወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
- የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ በማይኖርበት ወቅት ተክቶት ይሰራል፡፡
- ስለወረዳ ቋሚ ኮሚቴ አባላት
- የወረዳ ቋሚ ኮሚቴ ተጠሪነት ለወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና በጋራ ለሚወስነው ውሣኔ ለወረዳው ምክር ቤት ሆኖ የወረዳ ቋሚ ኮሚቴ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፣
ሀ) የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤
ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ከተራ ቁጥር 2 እስከ 18 ከተቋቋሙ የአስፈፃሚ አካላት መካከል በወረዳ ደረጃ የተደራጁ አስፈጻሚ አካላት ኃላፊዎች፤
ሐ) ሥራ አስፈጻሚው እንደአስፈላጊነቱ በአባልነት እንዲሳተፉ የሚመርጣቸው የወረዳው ሌሎች ኃላፊዎች፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀፅ 1/ለ/ ሥር የተጠቀሰው አስፈጻሚ አካል ኃላፊ በቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ሊገኝ በማይችልበት ጊዜ በግልጽ ተለይቶ ውክልና የተሰጠው ኃላፊ በተተኪ አባልነት በቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ይሳተፋል፡፡
- ስለወረዳ ቋሚ ኮሚቴ ሥልጣንና ተግባር፤
- የወረዳ ቋሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
ሀ. በወረዳው ዕቅድና የበጀት ድልድል ሃሳብ ላይ ይመክራል፤
ለ. በወረዳው ውስጥ ፖሊሲዎች፣ አዋጆች፣ ደንቦችና የከተማው የበላይ አካላት ውሣኔዎች በሥራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤
ሐ. በወረዳው ምክር ቤትና በዋና ሥራ አስፈጻሚው የሚሰጡት ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፤
- የወረዳው ቋሚ ኮሚቴ የሥራ ዘመን የወረዳው ምክር ቤት የሥራ ዘመን ይሆናል፡፡
- ስለወረዳ አስፈጻሚ አካላት
- እያንዳንዱ ወረዳ በከተማው ካቢኔ በጸደቀ ወይም በሚፀድቀው መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት ሥልጣንና ተግባራቸው የሚወሰንላቸው አስፈጻሚ አካላት ይኖሩታል፤
- ወረዳዎች በዚህ አዋጅ የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ለማዋል የሚያስችላቸው ሌሎች የሥራ ክፍሎችና እንደአስፈላጊነቱም ነዋሪውን የሚያሳትፉ የበጐ ፈቃደኞች ኮሚቴዎች፣ እና የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡባቸውን ማዕከላት በከተማው ካቢኔ በጸደቀ ወይም በሚጸድቅ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የሥራ ድርሻ ዝርዝር መሠረት ለማደራጀት ይችላሉ፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት የሚደራጅ እያንዳንዱ ጽሕፈት ቤት በአጠቃላይ ለወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪ ይሆናል፡፡ የዕቅድና በጀት ዝግጅት የዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ፣ የሠራተኞች የውስጥ ዝውውርና የደረጃ ዕድገትን ጨምሮ ሌሎች ሙያዊና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ በሥራው መስክ ለሚመለከተው የክፍለ ከተማ ጽሕፈት ቤት ተጠሪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የከተማው ማዕከል ቢሮዎችና የሚያስተባብሯቸው ሌሎች አስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ተከትሎ በሥሩ የሚደራጁትን ሌሎች ጽሕፈት ቤቶች ወይም ሌሎች የሥራ ክፍሎች በበላይነት ይመራል፣ ያስተባብራል፤
- የወረዳ ጽሕፈት ቤቶች ከሚያስተባብሯቸው አስፈጻሚ አካላት ጋር እና ጽሕፈት ቤቶቹ በአንድ ላይ ደጋፊ የሥራ ሂደቶችን በጋራ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ዝርዝሩ የከተማው ካቢኔ በሚያፀድቀው መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በከንቲባው በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል፤
- በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1-4/ እና በሕግ በሌላ ሁኔታ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የወረዳ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችና ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የጽሕፈት ቤትና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት ኃላፊዎች የሥራ ሁኔታ በከተማው ካቢኔ በሚወጣ ደንብ ይወሰናል፡፡
- ስለወረዳ ሥራ አስኪያጅ
- የወረዳ ሥራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለክፍለ ከተማው ሥራ አስኪያጅና ለወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆኖ የወረዳው ማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች አስፈጻሚ በመሆን ይሠራል፤
- የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1////// አጠቃላይ አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ የወረዳው ሥራ አስኪያጅ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-
ሀ. በወረዳው የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ስሉጥ ውጤታማና ፍትሐዊ እንዲሆን ኃሳብ ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
ለ. የወረዳው ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ሠራተኞችን አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ያስተዳድራል፤
ሐ. ከወረዳው ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት ሰጪ አካላት ኃላፊዎች የተውጣጣና በከተማ ሥራ አስኪያጅ በሚወሰነው መሠረት የሚሠራ የሥራ አመራር ኮሚቴ ያቋቁማል፤ ይመራል፤
መ. በወረዳ የሚገኘውን የጽዳት፣ የውበት፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራ፣ የመሠረተ ልማት ጉዳዮችን ይከታተላል፣ ያስፈጽማል፤ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች ሕጐችና ውሣኔዎችን ተግባራዊ ያደርጋል፤
ሠ. ስለሥራው አፈጻጸም ለክፍለ ከተማው ሥራ አስኪያጅና ለወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወቅታዊና ዓመታዊ ሪፖርት ያቀርባል፤
ረ. ከክፍለ ከተማው ሥራ አስኪያጅና ከወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፤
- የወረዳው ሥራ አስኪያጅ በወረዳ ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ ያለድምጽ መሳተፍ ይችላል፡፡
- ስለ ቦርድ፣ አማካሪ ምክር ቤት፣ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ምክክር መድረክ
- በከንቲባው አቅራቢነት ለአስፈፃሚ አካላት እና ለሌሎች የከተማው ተቋማት የስራ አመራር ቦርድ፣ አማካሪ ምክር ቤት፣ ጠቅላላ ጉባኤ ወይም የምክክር መድረክ ካቢኔው በደንብ ሊያቋቁምላቸው ይችላል፤
- የከተማ አስተዳደሩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ እና የልማት ድርጅቶች ቦርድ በተመለከተ አግባብነት ያላቸው ህጎች ድንጋጌ የተጠበቀ ነው፡፡
- አስፈፃሚ አካል፣ የልማት ድርጅት ስለ ማደራጀትና ማቋቋም
ለከተማው ምክር ቤት ተጠሪ የሆኑት እና በከተማው ምክር ቤት በሚሾሙ ኃሊፊዎች የሚመሩ አስፈፃሚ አካላት ሳይጨምር ካቢኔው አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ደንብ በማውጣት ሌላ አስፈፃሚ አካል እንዲታጠፍ፣ ከሌላ አስፈፃሚ አካል ጋር እንዲዋሃድ፣ እንዲከፋፈል ወይም ሥልጣንና ተግባሩ እንዲለወጥ በማድረግ፣ ወይም አዲስ አስፈፃሚ አካል የማቋቋምና የማደራጀት፣ የከተማውን የልማት ድርጅት አግባብ ባለው ህግ መሠረት የማቋቋምና እንደገና የማደራጀት፣ የማፍረስ ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡
- የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀትና አሰራር ስለመወሰን
ካቢኔው አስፈላጊነቱን ሲያምንበት የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀትና አሰራር ለመወሰን ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡
ክፍል ሰባት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
- ደንብ የማውጣት ሥልጣን
ካቢኔው ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡
- ስለ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽህፈት ቤት
- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽህፈት ቤት ተጠሪነት ለአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ይሆናል፤
- በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ጽህፈት ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች አዋጅ የተደነገገው ስልጣንና ተግባር ይኖረዋል፡፡
- የመዳኘት ስልጣን የተሰጣቸው አካላትን ስለማቋቋምና ማደራጀት
ካቢኔው የከተማው አስተዳደር የመዳኘት ስልጣን የተሰጣቸው አካላትን እንደገና የማቋቋም፣ አደረጃጀትና አሰራራቸውን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡
- የመብቶችና ግዴታዎች መተላለፍ
- የመሸጋገሪያ ድንጋጌዎች
- በዚህ አዋጅ ያልተካተቱ አስፈጻሚ አካላት ከዚህ አዋጅ ጋር ባልተቃረነ መልኩ በተቋቋሙበት ህግ ስራቸውን ይቀጥላሉ፤
- የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀትንና አሰራር ለመወሰን ካቢኔው ያወጣቸው ልዩልዩ ደንቦች የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች እስካልተቃረኑ እና በዚህ አዋጅ መሰረት በሚወጡ ደንቦች እስከሚተኩ ድረስ ተፈፃሚነታቸው ይቀጥላል፤
- የዚህ አዋጅ አንቀጽ 104 ድንጋጌ ቢኖርም በዚህ አዋጅ መሰረት የአደረጃጀት ማሻሻያ እሰከሚደረግ ድረስ በከተማ፣ በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ ተደራጅተው በመስራት ላይ የሚገኙ አስፈፃሚ አካላት በተደራጁበት ህግና አግባብ ስራቸውን ይቀጥላሉ፤
- በዚህ አዋጅ የታጠፉ አስፈፃሚ አካላት በመከናወን ላይ ያሉ ስራዎችን እያከናወኑ ለርክክብ ዝግጁ ያደርጋሉ፤ በከንቲባው በሚወጣ መመሪያ በሚወሰነው መሰረት በዚህ አዋጅ ለተቋቋሙ አስፈፃሚ አካል ያስረክባሉ፡፡
- ስለተጠያቂነት
በዚህ አዋጅና በሌሎች ህጎች በተሰጠው ስልጣንና ተግባር ኃላፊነቱን ያልተወጣ ኃላፊ ወይም ሰራተኛ አግባብነት ባለው ህግና አሰራር ተጠያቂ ይሆናል፡፡
- የተሻሻለ ሕግ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ቢሮና የማሰልጠኛ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 49/2009 የማሰልጠኛ ተቋማት ተጠሪነት ለክህሎት፣ ካይዘን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ይሆናል፡፡
የተሻሩ ሕጎች
ከዚህ የሚከተሉት ሕጎች ተሸረዋል፡፡
- ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች
ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ የከተማው አስተዳደር አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ እና ልማዳዊ አሰራር በዚህ አዋጅ የተደነገጉትን ጉዳዮች በሚመለከት ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡
- አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከ—————-ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
አዲስ አበባ —————ቀን 2014 ዓ.ም.
አዳነች አቤቤ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ
አባሪዎች
አባሪ 1፦ ባሉበት የሚቀጥሉ፣ የሚታጠፉ፣ የስያሜ ለውጥ የሚያደርጉ እና በአዲስ የሚቋቋሙ ተቋማት ማጠቃለያ
ተ.ቁ | ባሉበት የሚቀጥሉ ተቋማት | በአዲስ የሚቋቋሙ ተቋማት | በውህደት የተፈጠሩ ተቋማት | የሚታጠፉ ተቋማት | የስያሜ ወይም የስልጣንና ተግባር ለውጥ ተደርጎ የሚቋቋሙ ተቋማት |
የከንቲባ ጽህፈት ቤት | የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን | የስርዓተ ጾታ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ | የመሰረተ ልማት ቅንጅት፣ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን | የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን | |
የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ | የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ | ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ | የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን | የምገባ ኤጀንሲ | |
የዐቃቤ ሕግ ቢሮ | የደንብ ማስከበር ኤጀንሲ | የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ | የትራንስፖርት ባለስልጣን | የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ | |
የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፤ | የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን /የልማት ድርጅት/ | የክህሎት፤ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ | የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ | የአዲስ አበባ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት /የልማት ድርጅት/ | |
የንግድ ቢሮ | የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት | የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ | የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ | አዲስ አበባ የሥራ አመራር ኢንስቲትዩት | |
የትምህርት ቢሮ | አዲስ አበባ ፖሊስ/ተጠሪነቱ ከፊደራል ሲዛወር/ | የጤና ቢሮ | የህዝብ ቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ጽህፈት ቤት | የትላልቅ ግንባታዎች ፕሮጀክት ጽ/ቤት | |
የባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ | የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ | የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽህፈት ቤት | የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን | ||
የገቢዎች ቢሮ | የትራንስፖርት ቢሮ | የመሬት ይዞታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት | የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት | ||
የፕላንና ልማት ኮሚሽን | የፋይናንስ ቢሮ | የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከ-ያና መቆጣጠርያ ጽ/ቤት | የተፋሰስና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ | ||
የኢንቨስትመንት ኮሚሽን | አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት /የልማት ድርጅት/ | የአዲስ ዙ ፓርክ | |||
የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን | የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ | መስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ | |||
የትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን | የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ | ||||
የምግብ ፣መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን | ኮንስትራክሽን ቢሮ | ||||
የመንግስት ሕንፃና ንብረት አስተዳደር ባለሥልጣን | የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን | ||||
የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን | የግንባታ ኢንተርፕራይዝ | ||||
የመንገዶች ባለስልጣን | የምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍቲኔት ኤጀንሲ | ||||
የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን | ስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ | ||||
የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ | ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ | ||||
የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ | የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ | ||||
የህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ | የስፖርት ኮሚሽን | ||||
የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ | የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ | ||||
የትራፊክ ማንጀመንት ኤጂንሲ | የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ | ||||
የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ | |||||
ጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል | |||||
ማህበራዊ ትረስት ፈንድ | |||||
ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት | |||||
26 | 6 | 11 | 22 | 9 |
አባሪ 2. በውህደት የተፈጠሩ ተቋማት
ተ.ቁ | ነባር ተቋማት | በውህደት የሚፈጠሩ ተቋማት |
1 | የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ | የስርዓተ ጾታ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ |
2 | የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ | |
3 | የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ | የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ |
የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ኤጀንሲ | ||
4 | የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ | የኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ |
5 | የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ | |
6 | የስፖርት ኮሚሽን | የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ |
7 | የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ | |
8 | አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት /የልማት ድርጅት/ | አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት /የልማት ድርጅት/ |
9 | ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት /የልማት ድርጅት/ | |
10 | የቴክኒክና ሙያ ት/ት እና ስልጠና ኤጀን | የክህሎት፣ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ |
11 | የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ | |
12 | ካይዘን | |
13 | ፋይናንስ ቢሮ | ፋይናንስ ቢሮ |
14 | የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባለስልጣን | |
15 | ጤና ቢሮ | የጤና ቢሮ |
16 | የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት | |
17 | የትራንስፖርት ቢሮ | ትራንስፖርት ቢሮ |
18 | ትራንስፖርት ባለስልጣን | |
19 | ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ | ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ |
20 | ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን | |
21 | የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ | መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ |
22 | የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት | |
23 | የመሬት ይዞታ አስተዳደር ጽ/ቤት |
አባሪ 3. የተጠሪነት ለውጥ የተደረገባቸው ተቋማት
ተ.ቁ | የተቋሙ ስም | ተጠሪ የነበረበት ተቋም | አዲስ ተጠሪ የሚሆንበት |
የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን | ለከንቲባ | ለከተማ ሥራ አስኪያጅ | |
የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ | ለሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ | ለከተማ ሥራ አስኪያጅ | |
የተፋሰስና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ | ለአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን | ለከተማ ሥራ አስኪያጅ | |
የጉለሌ እጽዋት ማዕከል | ለአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን | ለከንቲባ | |
እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን | ለሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ | ለከተማ ሥራ አስኪያጅ |
ተቀላቅለው ወይም እንደ አዲስ የሚቋቋሙ
ተ.ቁ | ነባር የተቋሙ ስም | አዲሱ መጠሪያ | ተጠሪ የነበረበት ተቋም | አዲስ ተጠሪ የሚሆንበት |
1. | የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳዳር ኮርፖሬሽን | ለከተማ ስራ አስኪያጅ | ||
2. | የግንባታ ኢንተርፕራይዝ | የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት | ለቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ | ለዲዛየንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ |
3. | የግንባታ ዲዛየን ኤጀንሲ | |||
4. | አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት /የልማት ድርጅት/ | አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት | ለከተማ ሥራ አስኪያጅ | ለትራንስፖርት ቢሮ |
5. | ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት /የልማት ድርጅት/ | ለከተማ ሥራ አስኪያጅ | ||
6. | አዲስ አበባ የቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት | ለትራንስፖርት ቢሮ |