በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት እና ዳታ ማእከል አስተዳደር ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች እና ትንታኔያቸው
ሀ. የዳታ ማዕከልና ፋሲሊቲ ማኔጅመንትRead More
- በክፍለ ከተማው ዳታ ሴንተር መደበኛ በሳምንት 2 ግዜ በአጠቃላይ በበጀት አመቱ ለ48 ግዜያት ቋሚ ክትትል በማድረግ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውስጥ አቅም መፍትሄ በመስጠት አገልግሎት ላይ እንገኛለን
- የክፍለ ከተማውን ዳታ ማዕከሎች ማስተዳደር የዳታ ማዕከል ዕቃዎችና ፋሲሊቲዎችን ያሉበትን ሁኔታ መረጃና የጥገና ታሪክ መዝግቦ መያዝ እና በየጊዜው ማሻሻል
- የክፍለ ከተማውን የዳታ ማዕከል መሳሪያዎችን ሁኔታ መከታተል፣ ሞኒተር ማድረግ፣ ኦዲት ማድረግና ጤንነታቸውን መከታተልና መፈተሽ
- የዳታ ማዕከል ዕቃዎች ወይም መሳሪያዎችን ማለትም የዳታ ማዕከል መቆጣጠሪያ፣ አላርም፣ ሙቀት መቆጣጠሪያ፣ እሳት መቆጣጠሪያ ወይም ማጠፊያ፣ የአደጋ ጊዜ ድምጽ ማሰሚያ፣ ካሜራዎች፣ የአቅም፣ የኃይል፣ የኔትወርክ ሁኔታን እና የመሳሰሉትን በትክክል ሰለመስራታቸው የ24/7 ክትትል ማድረግ
- የኔትወርክና ዳታ ማዕከል መሳሪያዎች ላይ ችግር ሲፈጠር ማስተካከያ ወይም የጥገና ስራ እያከናወን እንገኛለን
- ሁሉንም የዳታ ማዕከል መሳሪያዎችን ሁኔታ መከታተል፣ ሞኒተር ማድረግ፣ ኦዲት ማድረግና ጤንነታቸውን መከታተል መፈተሽ
- በዳታ ማዕከሉ ያሉ ብልሽቶችን ወይም ጊዜ ጠበቀው መተካት ያለባቸውን ዕቃዎች ሁኔታ መከታተል
- በዳታ ማዕከል አጠቃቀም ላይ ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ፣ መደገፍና ፈጣን ምላሽ መስጠት
- ዳታ ማዕከል ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች ወይም ፋሲሊቲዎችን የጽዳት ሁኔታ መከታተል
- የተገኙ ችግሮችን መረዳት፣ መፍትሄ የሚሰጥበት መንገድና የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን መለየት
- የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት አስፈላጊ መሳሪያዎችን ወይም ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት
- ብልሽቶች ሲገጥሙ የመጀመሪያ ደረጃ የጥገና ስራዎችን ማከናወን
- የዳታ ማዕከል ችግሮችን መፍታትና የዕለት ተዕለት ኦፕሬሽናል ስራዎችን ማከናወን
- የዳታ ማዕከል መሳሪያዎችን ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በትክክል ማስቀመጥ
- ዳታ ማዕከል ለሚጠቀሙ ባለሙያዎች በዳታ ማዕከል አጠቃቀም ዙሪያ ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግና መደገፍ እንዲሁም ፈጣን ምላሽ መስጠት
- በዳታ ማዕከል የሚገኙ ቁሳቁሶችን አስቀድሞ ከብልሽት የመከላከል፣ ጥገና ማድረግ፣ ማጽዳትና በየወቅቱ የሚቀየሩ ዕቃዎችን መከታተልና መለወጥ
- ዳታ ማዕከሉን ማስተዳደር
- ብልሽቶች ሲገጥሙ የመጀመሪያ ደረጃ የጥገና ስራዎችን ማከናወን
- የዳታ ማዕከል ዕቃዎችን እና ፋሲሊቲዎችን ያሉበትን ሁኔታ መረጃ መዝግቦ መያዝ እና በየጊዜው ማሻሻል
- ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን በሰፖርት፣ ሜንቴናንስ እና ዋራንቲ ውል ወይም በSLA መሰረት በአቅራቢዎች እንዲፈታ ማድረግ፣ መከታተል። ውላቸው ያበቃ ከሆነ ሌሎች የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረብ ለሚመለከተው ሪፖርት ማድረግ፣ ተከታትሎ መፍታት
ለ. ሲስተም አስተዳዳር
- የሰርቨር ሲስተሞችን አጠቃላይ ሁኔታ ሞኒተር ማድረግ፣ ኦዲት ማድረግ እና የሲስተምና ሰርቨር ጤንነቶችን መከታተል
- የተለዩ ወይም ሪፖርት የተደረጉ ችግሮችን መረዳትና መፍትሄ የሚሰጥበትን መንገድ መለየት እንዲሁም የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ወይም ሶፍተዌሮችን ማዘጋጀት
- የሲስተም ጥገና፣ ትራብልሹቲንግና የኮንፊገሬሽን ማስተካከያ ስራዎችን መስራት፣ የእለት ተዕለት ኦፕሬሽናል ስራዎችን ማከናወን
- የሰርቨሮችን እና የኮምፒዩተሮቸን አቅም ማሳደግ
- ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን በሳፖርት፣ ሜንቴናንስ እና ዋራንቲ ውል ወይም በSLA መሰረት በአቅራቢዎች እንዲፈታ ማድረግ፣ መከታተል። ውላቸው ያበቃ ከሆነ ሌሎች የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረብ ለሚመለከተው ሪፖርት ማድረግ፣ ተከታትሎ መፍታት
- የተወሰዱ የማስተካከያ እረምጃዎች ወይም ስራዎች በትክክል ስለመሰራታቸው ፍተሻ ማድረግ፣ መረጃ መያዝ (Testing, approval, Document)
- ተጠቃሚዎችንና ፓስወርዶችን ማኔጅ ማድረግ፣ ቨርቹዋል ኮምፒዩቲንግ ፕላትፎርሞችን፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችን ማኔጅ ማድረግ
- የሰርቨርና ሰርቨር ሲስተሞች ያሉበትን ሁኔታ መረጃና ታሪክ መዝግቦ መያዝ እና በየጊዜው ማሻሻል
- አጠቃላይ ሲስተም ሞኒተሪንግ ስራዎችን መስራት እና መከታተል
- አጠቃላይ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሲስተሞች፣ መሰረተ ልማቶችና መሳሪያዎች ጤንነትን መከታተል
- በሲስተሞችና መሰረተ ልማቶች ላይ ሪፖርት የሚደረጉ ችግሮችና የሚቀርቡ ጥያቄዎችን መቀበል
- ጥያቄዎችንና ችግሮችን ማጥናትና መረዳት
- ሰርቨሮችን ባክአፕና ሪከቨር የማድረግ ስራዎችን መስራት
- የስቶሬጅ ሲስተም ማኔጅ ማድረግ ማሳደግና እንዲሻሻሉ ማድረግ
- የሰርቨሮችን እና የኮምፒዩተሮቸን ወይም ወርክስቴሽኖችን አቅም እንዲያድጉ ማድረግ
- ለሁሉም ብልሽቶች የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ የጥገና ስራዎችን ማከናወን
- ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን በሳፖርት፣ ሜንቴናንስ እና ዋራንቲ ውል ወይም በSLA መሰረት በአቅራቢዎች እንዲፈታ ማድረግ፣ መከታተል። ውላቸው ያበቃ ከሆነ ሌሎች የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረብ ለሚመለከተው ሪፖርት ማድረግና ተከታትሎ መፍታት
ሐ. አክቲቭ ዳይሬክተሪ አገልግሎት
- ኤፍቲፒ ሰርቨሩን በመጠቀም መረጃዎችን፣ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን መለዋወጥ እና መጠቀም
- የአገልግሎት ጥያቄ መቀበል
- የአገልግሎት ዝርዝር ጥያቄውን መረዳትና ፍቃድ ስለመኖሩ ማረጋገጥ (Analyze Request & Authorization)
- አክቲቭ ዳይሬክተሪ አገልግሎት ማስተዳደር እና ማኔጅ ማድረግ
- የአክቲቭ ዳይሬክተሪ ኮንፊገሬሽን ስራዎችን መስራትና አገልግሎቱን መስጠት
- አገልግሎቱ ወይም ጥያቄው በትክክል ስለመሰጠቱ ፍተሻ (Testing) ማድረግ
- የደንበኞችን ምላሽ መቀበልና መረጃ መያዝ (record transaction)
- የአክቲቭ ዳይሬክተሪ ጥያቄው በትክክል ስለመሰጠቱ ፍተሻ (Testing) ማድረግ
- በክፍለ ከተማው ውስጥ ያሉትን ኮምፒውተሮች ወደ አንድ ሰርቨር በማሰባበሰብና ለማኔጅመንት ምቹ በሆነ መልኩ ኮምፒውተሮችን በማስተሳሰር የሚያስፈልገውን ክትትል ማድረግ
መ. ቪዲዮ ኮንፈረንስ
- የአገልግሎት ጥያቄ መቀበል
- የአገልግሎት ዝርዝር ጥያቄውን መረዳት
- የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት መስጫ ሳይቶችን ማዘጋጀት እና አስፈላጊ የኮንፊገሬሽን ስራዎችን መስራት፣ ቅድመ አገልግሎት ሙከራ ማድረግ
- የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊ የኦፕሬሽን ስራዎችን መስራት
- የአገልግሎት መቆራረጥ እንዳይኖር መከታተልና እርምጃ መውሰድ
- የቪዲዮ ኮንፈረንስ መሳሪያዎች ደህንነታቸው በተጠበቀ ቦታ መልሶ ማስቀመጥና አገልግሎቱን ማጠናቀቅ
- የደንበኞች ምላሽ (feedback) መቀበልና መረጃ መያዝ (record transaction)
- የቪዲዮ ኮንፈረንስ መስጫ ማዕከላት በግራውንድ እና በአስራ አንደኛ ፎቅ የሚገኝ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ የተሳካ የቪድዮ ኮንፍራንስ አግለግሎት እንዲሰጥ ማድረግ
ረ. ኔትወርክ ማኔጅመንት
- ኔትወርክ ሲስተም አጠቃላይ ሁኔታ ሞኒተር ማድረግ፣ ኦዲት ማድረግ እና የኔትወርክ ጤንነትን መከታተል
- የተለዩ ወይም ሪፖርት የተደረጉ ችግሮችን መረዳትና መፍትሄ የሚሰጥበትን መንገድ ወይም ዘዴ መለየት እንዲሁም የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
- የማስተካከያ እርምጃ መውሰድና የእለት ተዕለት ኦፕሬሽናል ስራዎችን ማከናወን
- በኔትወርክና ኔትወርክ መሳሪያዎች ላይ የተለያዩ የኮንፊገሬሽን ወይም ማሻሻያዎችን፣ ትራብልሹቲንግ እና የማስተካከያ ስራዎችን መስራት
- የኔትወርክ ኮንፊገሬሽን ፋይል ጥበቃ ወይም ባክአፕ፣ ሲበላሽም የመመለስ ወይም ሪከቨር የማድረግ ስራዎችን መስራት
- የኔትወርክ አቅም የሚገድቡ ችግሮችን በመለየት የማሻሻል ስራ መስራት
- ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን በዋራንቲ ውል ወይም በSLA መሰረት በአቅራቢዎች እንዲፈቱ ማድረግ፣ መከታተል። ውላቸው ያበቃ ከሆነ ሌሎች የመፍትሄ አማራጮችን ማቅረብ ለሚመለከተው ሪፖርት ማድረግ፣ ተከታትሎ መፍታት
- የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች ወይም ስራዎች በትክክል ስለመስራታቸው ፍተሻ ማድረግ፣ መረጃ መያዝ፣ የመፈተሽ ስራ መስራት (Testing, approval, Document)
- የኔትወርክና የኔትወርክ ሲስተሞች ያሉበትን ሁኔታ፣ የጥገና ታሪክና ኮንፊገሬሽን መረጃ መዝግቦ መያዝ እንዲሁም በየጊዜው ማሻሻል
- የኔትወርክ ፍላጎት መለየትና ዲዛይን ማድረግ እንዲሁም የኔትወርክ ዝርጋታ ስራ ማከናወን
ሸ. ኢንተርኔት አገልግሎት ማኔጅመንት
- በክፈፍለ ከተማው ስር ባሉ ተቋማት የሚቀርቡ የኢንተርኔት አገልግሎት ጥያቄዎችን መቀበልና ከቴሌኮም አቅራቢዎች ጋር ግንኙነት በማድረግ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ
- ማንኛውንም ከቴሌኮም አቅራቢዎች የሚቀርቡ የኢንተርኔት እና የዳታ ወይም የቪፒኤንና ተያያዥ አገልግሎቶች በውሉ መሰረት በትክክልና በተሟላ ሁኔታ ስለመስራታቸው መከታተል እና ሪፖርት ማድረግ
- የተወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች ወይም ስራዎች በትክክል ስለመስራታቸው ፍተሻ ማድረግ፣ መረጃ መያዝ፣ የመፈተሽ ስራ መስራት (Testing, approval, Document)
- የኢንተርኔት አገልግሎቶች ያሉበትን ሁኔታ፣ ታሪክና ኮንፊገሬሽን መረጃ (Including IP) መዝግቦ መያዝ እንዲሁም በየጊዜው ማሻሻል
- የሁሉንም ተገልጋዮች እና የክፍለ ከተማው ስር ላሉ ተቋማት፣ ግለሰቦችና ከቴሌኮም ተቋማት የሚቀርቡ የኢንተርኔት፣ የዳታ (VPN) ፣ የዋይፋይ፣ የIP አገልግሎቶችን መረጃ፣ የሰርቪስ ቁጥር (Account Number) ፣ የአገልግሎት ክፍያ፣ ተያያዥ ዕቃዎች (Epon, Gpon, Wi-Fi, Router, ADSL/DSL etc.) ሁኔታና መረጃ መዝግቦ መያዝ በየጊዜው ማሻሻል
- የተለዩ ወይም ሪፖርት የተደረጉ የኢንተርኔት እና የዳታ ወይም የቪፒኤንና ተያያዥ ችግሮችን የተሟላ መረጃ መያዝ፣ ችግሮቹን መረዳትና መፍትሄ የሚሰጥበትን መንገድ ወይም ዘዴ እና መፍትሄ የሚሰጡ አካላትን መለየት ማዘጋጀትና ሪፖርት ማድረግ
- ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን በSLA መሰረት በአገልግሎት አቅራቢዎች ወይም በበላይ አካል እንዲፈቱ ማድረግና ለሚመለከተው ሪፖርት ማድረግ እንዲሁም TT-ቁጥሮችን በጥንቃቄ መያዝና ተከታትሎ መፍታት
- በክፍለ ከተማ በገመድ አልባ ወይም ዋይፋይ እና በገመድ አገልግሎት እንዲሁም በ12ቱ የወረዳ አስተዳደሮች ደግሞ በገመድ የኢንተርኔት አገለግሎት እየተሰጠ ይገኛል
ቀ. የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሲስተም ደህንነት መጠበቅ እና መከታተል
- ለሳይበር ደህንነት ፖሊሲና ፕሮሲጀሮችን በመከተል አዋጪ ምላሾችን መስጠት
- የሳይበር ደህንነት ክስተቶች እንዳይስፋፉ የመከላከያና መቆጣጠሪያ እርምጃዎችን መውሰድ
- በአደጋ ስጋት ዳሰሳ መሰረት በማንኛውም የመቆጣጠሪያ ስርዓት ላይ አስፈላጊውን የደህንነት ቁጥጥር ስርዓት መተግበርና ተጋላጭነት በተገቢ ሁኔታ መቆጣጠር
- ስራ ላይ ባሉ እና በአዳዲስ የሳይበር ደህንነት መሳሪዎች ላይ አስፈላጊውን የደህንነት እርምጃ (security measures) መውሰድ
- የሳይበር ጥቃት የደረሰባቸው የመረጃ ስርዓቶችና ሃብቶችን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ወደነበሩበት መመለስ
- የተቋሙን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ለልማት እና ሲስተም ደህንነት ጥሰቶችን እና ተጋላጭነት መለየት እና መመርመር
- ሚስጥራዊነት ያለው መረጃዎችን ለመጠበቅ የፋየርዎል እና ዳታ ኢንክሪፕሽን ፕሮግራሞችን እና የአንቲቫይረስ ሶፍተዌሮችን መጠቀም እና maintain ማድረግ
- በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ለልማት እና ዳታ ቤዝ ሲስተም ውስጥ ያሉ ጥቃቶችን፣ ሙከራዎችን እና የደህንነት ጥሰቶችን መመዝገብ እና ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ
- ለተጠቃሚዎች ስለ ኔትዎርክ መሰረተ ልማት፣ ዳታቤዝ ደህንነት እና አጠቃቀም ዙሪያ ለተጠቃሚዎች የግንዛቤ እና የምክር አገልግሎት መስጠት
- የአደጋውን ክብደት በመገምገም እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ሚቀጥለው የስራ ክፍል ማስተላለፍ (Escalate) ማድረግ
- የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ለልማት እና ሲስተም ደህንነት መመሪያዎችን እና አሰራሮችን ወይም ፕሮሲጀሮችን ተግባራዊ ማድረግ
- የኮምፒውተር እና የመሰረተ ልማት መሳሪያዎችን ደህንነታቸውን ጠብቆ ኮንፊገር ማድረግና መቆጣጠር
- የሳይበር ጥቃት የደረሰባቸውን የመረጃ ስርዓቶች፣ ሃብቶችን እና ተቋማትን መለየት እና ማስተላለፍ፣ ሪፖርት ማድረግ
- የሳይበር ጥቃት የደረሰባቸው የመረጃ ስርዓቶችና ሃብቶችን ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ወደነበሩበት እንዲመለሱ ከሚመለከተው አካል ጋር አብሮ መስራት
- በመረጃ አጠባበቅ፣ በይለፍ ቃል አወሳሰብና ለሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን መስጠት
- የተለያዩ ፋሲሊቲዎች ፍቃድ በተሰጠው አካል ብቻ አገለግሎት ላይ እንዲውሉ ለማድረግ የሚያስችል የቁጥጥር ስራ መስራት
- በሳይበር ደህንነት ስትራቴጂ መሰረት መረጃ እና ሪከርዶች እንዳይለወጡ መጠበቅ
- በሳይበር ደህንነት ፖሊሲዎች መሰረት መረጃዎችና የመረጃ ስርዓቶችንና አሴቶችን መጠበቅ
- የመረጃ ስርዓቶች በሰርጎ-ገቦች እንዳይጠቁ በንቃት መጠበቅ
- የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነቶችን መቆጣጠር ወይም መጠበቅ
- የአዳዲስ የሳይበር ስጋቶችን መቀነስ
- የሳይበር ደህንነት መጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች ደህንነት ሳይቆራረጡ እንዲሰሩ ማድረግ
- በሳይበር ደህንነት ፖሊሲ እና ፕሮሲጀሮች ገዥ ሰነዶች ላይ ስልጠና መስጠት
- የሳይበር ደህንነት የጥንቃቄ እርምጃዎችን አስመልክቶ ምክር መስጠት
- በመረጃ አጠባበቅ፣ በይለፍ ቃል አወሳሰብና ለሳይበር ጥቃት የሚያጋልጡ ሁኔታዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫዎችን መስጠት