የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ5ቱን የጳጉሜን ቀናት የንቅናቄ ስራ የቅድመ ዝግጅት አፈፃፀም ገመገመ
ነሀሴ 28/2016 የካ ኮሙኒኬሽንRead More
አስተዳደሩ “ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበሩትን የ5ቱን የጳጉሜን ቀናት የንቅናቄ ስራዎች የቅድመ ዝግጅት አፈፃፀም አስመልክቶ ከክፍለ ከተማ አመራርና ከወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ገምግሟል።
በመድረኩ የ5ቱ የጳጉሜን ቀናት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት በየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ፣የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና እና የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት መርተውታል።
አቶ ብርሃኑ ረታ እንደገለፁት የጳጎሜ ቀናትን በዕቅዱ መሰረት በድምቀት ለማክበር እየተሰራ የሚገኘው የቅድመ ዝግጅት ስራ አበረታች መሆኑን በመግለፅ ቅንጅታዊ ስራዎችን እያጠናከሩ መሄድ ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ተቆጥሮ የተሰጠን ተግባር በውጤት ማጀብ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቶ መገርሳ ገላና በበኩላቸው የጳጎሜን ቀናቶች ስያሜያቸውን በሚገልፅ መልኩ በደመቀ ህዝባዊ ተሳትፎ እና አንድነትን ባጠናከረና የህዝቦችን ወንድማማችነትና እህትማማችነትን እንዲሁም አብሮነትን ባጠናከረ መልኩ ለማክበር እየተደረገ የሚገኘው ርብርብ በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።
5ቱም የጳጉሜ ቀናት በሚገባቸው ክብር ልክ ካለምንም መንጠባጠብ ለማክበር እየተደረገ የሚገኘው ቅድመ ዝግጅት የአመራሩን የመፈፀም አቅም ያሳየ ነው ያሉት አቶ እንዳልካቸው አስራት በቅድመ ዝግጅቱ ልክ ስራው በውጤት እንዲጠናቀቅ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ5ቱን የጳጉሜን ቀናት የንቅናቄ ስራ የቅድመ ዝግጅት አፈፃፀም ገመገመ
ነሀሴ 28/2016 የካ ኮሙኒኬሽንRead More
አስተዳደሩ “ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበሩትን የ5ቱን የጳጉሜን ቀናት የንቅናቄ ስራዎች የቅድመ ዝግጅት አፈፃፀም አስመልክቶ ከክፍለ ከተማ አመራርና ከወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር ገምግሟል።
በመድረኩ የ5ቱ የጳጉሜን ቀናት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት በየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ በቀለ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ፣የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና እና የክፍለ ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት መርተውታል።
አቶ ብርሃኑ ረታ እንደገለፁት የጳጎሜ ቀናትን በዕቅዱ መሰረት በድምቀት ለማክበር እየተሰራ የሚገኘው የቅድመ ዝግጅት ስራ አበረታች መሆኑን በመግለፅ ቅንጅታዊ ስራዎችን እያጠናከሩ መሄድ ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ተቆጥሮ የተሰጠን ተግባር በውጤት ማጀብ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።
አቶ መገርሳ ገላና በበኩላቸው የጳጎሜን ቀናቶች ስያሜያቸውን በሚገልፅ መልኩ በደመቀ ህዝባዊ ተሳትፎ እና አንድነትን ባጠናከረና የህዝቦችን ወንድማማችነትና እህትማማችነትን እንዲሁም አብሮነትን ባጠናከረ መልኩ ለማክበር እየተደረገ የሚገኘው ርብርብ በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።
5ቱም የጳጉሜ ቀናት በሚገባቸው ክብር ልክ ካለምንም መንጠባጠብ ለማክበር እየተደረገ የሚገኘው ቅድመ ዝግጅት የአመራሩን የመፈፀም አቅም ያሳየ ነው ያሉት አቶ እንዳልካቸው አስራት በቅድመ ዝግጅቱ ልክ ስራው በውጤት እንዲጠናቀቅ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ እና የከተማ አመራሮች በዚህ ምሽት በየካ ሾላ መብራት መንገድ ዳርቻ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት ድምቀት የሚሰጡ ችግኝ በመትከል በድጋሚ አሻራቸውን አኑረዋል።Read More
ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ከቤልጄም እስከ መገናኛ እየተጠናቀቀ የሚገኘውን የመንገድ ኮሪደር ልማት በበላይነት ከማስተባበርና ከመደገፍ በተጨማሪ ለአረንጓዴ ልማት መስፋፋት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በዚሁ ፕሮጀክት ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በማከናወን አሻራቸውን አኑረዋል።
ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
“የተዘጋ በር መክፈቻ ቁልፍ እሳቤን መቀየርና ሁሌም ለለውጥ ዝግጁ መሆን ነው”!!
አቶ ብርሃኑ ረታ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ Read More
ነገሮችን የምናይበት መነፅር ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለነገ ማንነታችንና ህልማችን ስኬታማነት ቁልፍ ጉዳይ ነው።
በአካል መግዘፍ አልያም በእውቀት መዳበር ብቻ ለስኬታማነትና ለወደፊት እኛነት በቂ አይደሉም፣ይልቁንም በአዎንታዊ እሳቤ ልቀን ስንገኝ ጉዞው የቀና ይሆናል !!
አንተ እስካልተለወጥክ ድረስ የሚለወጥ ምንም ነገር የለም፣ አንተ ስትለወጥ ደግሞ የማይለወጥ የለም እንደሚባለው የእሳቤ ተፅዕኖ ግዙፍ ነው!!
ራስን ለመመልከትና ለመለወጥ ፈቃደኝነት ደግሞ ወሳኙ ጉዳይ ሲሆን ከሚያዩትና ከሚሰሙትም ባሻገር ያላዩትና ያልሰሙት ጉዳይ ለመመርመርና ለመቀበል ለአዳዲስ ሃሳቦች ራስን ክፍት የማድረግ ብቃት የሚሻ ጉዳይ ነው!!
ወደ ትልማችን ለመድረስ ራስን መመልከት ፣ እሳቤን መመርመር ደግሞ ለለውጥና ለመለወጥ የመጀመርያው እርምጃ እንደሆነ ብዙዎች ከተሞክሯቸው በመነሳት አረጋግጠዋል ።
ነገር ግን ደግሞ ራስን መመልከት እንደምንለው ቀላል ያልሆነና ለምናየው ብሎም ለምንሰማው ነገር በምንሰጠው ምላሽና ድርጊት በሚገለፅ ውህድ ውጤት በማሰናሰል የሚዳሰስ በመሆኑ ስለራሳችን ያለንን ምስል በየጊዜው በመገንዘብ ሁሌም እሳቤያችንን በመመርመር ለለውጥ ዝግጁ መሆን የግድ ይላል!!
ስለሆነም ከትናንት እሳቤ ጠቃሚውን ብቻ ይዘን መተው ያለብንን ትተን ዛሬንና ነገን ያልዋጁ እንዲሁም ከህልማችንና መንገዳችን የሚያስቱ ስሁት እና አሉታዊ እሳቤዎቻችንን አራግፈን ትተን፤ ለዛሬና ለነገ የሚጠቅሙ እሳቤዎችን እየተቀበልን ሁሌም ለለውጥ እንለወጥ የመክፈቻ ቁልፉንም ሁሌም ከእጃችን እናስገባ!!
ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለሰጡን እውቅና እጅግ አድርገን እናመሠግናለን!!Read More
“ለአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ ትግበራ ሌት ተቀን በትጋት ስለሰራችሁ ምስጋና ይገባችኋል”!!ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ለከተማዋን ሁለንተናዊ ለውጥና እድገት ባጎናፀፈው የመንገድ ኮሪደር ልማት ስራ ስኬታማነት የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ጉልህ አስተዋፅኦ ይበልጥ ለቀጣይ ስራ የሚያነሳሳ እውቅና መሰጠቱን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ብርሃኑ ረታ ገልፀዋል።
ለዚህም ታላቅ እውቅና ለመብቃት ከአስተዳደሩ ጋር ቀንና ሌሊት በመደገፍና በመከታተልና የስራ አቅጣጫ በመስጠት የከተማ አስተዳደሩን ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችን አመስግነዋል።
አክለውም ለኮሪደር ልማቱ ውጤታማነት ሌት ተቀን ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ለክፍለ ከተማና ለወረዳ አመራሮች፣ በየዘርፉ ላሉ ባለሙያዎችና ነዋሪዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ ምስጋና የእናንተ የትጋትና የልፋት ውጤት ነውና ልትኮሩ ይገባችኋልም በማለት አቶ ብርሃኑ ረታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ከአቶ ጃንጥራር አባይ ጋር ከቤልጄም ኤምባሲ መገናኛ ያለውን የመንገድ ኮሪደር ልማትን ተዘዋውረው ጎበኙRead More
ነሐሴ 26/2016፣ የካ ኮሙኒኬሽን
የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና ከቤልጄም ኤምባሲ መገናኛ ያለውና ደረጃውን ጠብቆ የተሰራውን የኮሪደር ልማት ስራ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም የኮሪደር ልማቱ በመንገድ ስፋት፣ በትላልቅና ሰፋፊ የመዝናኛ ፓርኮች፣ በተዋቡ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች፣ በሰፋፊ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ በህንፃ ማስዋብ ስራዎች የተከናወኑ ተግባራትን አቶ ሞገስ አድንቀው ፕሮጀክቱ የከተማዋን ደረጃ ከፍ ያደረገና ለነዋሪዎችም ምቹና ፅዱ ከተማ በመፍጠር በየደረጃው የሚገኝ አመራርና ህዝብ እጅና ጓንት ሆኖ ከሰራ የሚፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ፕሮጀክቱ ዋና ማሳያ ነው ብለዋል።
አቶ ሞገስ ባልቻ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በየካ ክፍለ ከተማ በ2ኛው ምዕራፍ የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚተገበርባቸውን ቦታዎች ተዘዋውረው ጎበኙRead More
ነሐሴ 26/2016፣ የካ ኮሙኒኬሽን
በመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የምስጋና እና የዕውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር ላይ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ደ/ር) በይፋ የተበሰረው 2ኛ ዙር የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ተከትሎ በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻን ጨምሮ የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታና የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና በጋራ በመሆን በክፍለ ከተማው በ2ኛው ዙር የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚተገበርባቸውን ከጣሊያን ኤምባሲ ጀርባ እስከ ቀበና ድልድይ ድረስ በአካል በመዘዋወር ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ (ደ/ር) የተሰጠንን ሃላፊነት በአግባቡ በመተግበር ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቅቆ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ለአገልግሎት ለማብቃት ቀንና ሌሊት ሰርተን ለማስረከብ እንተጋለን ብለዋል፡፡
የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚነካቸው ወረዳ ነዋሪዎችም በአስተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉና የከተማዋን ደረጃ በሚያሳድጉ የልማት ስራች ላይ በነቃ ተሳተፎና በተቀናጀ መንገድ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመስራ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከጎናችን እንድትሰለፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የየካ ክፍለ ከተማ ፕላን ልማት ጽ/ቤት ክፍለ ከተማውን በፕላን የሚመራ ለማድረግ እና የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በርካታ ስኬታማ ስራዎች መሰራታቸውን ገለፀ
ነሀሴ 28/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More
የየካ ክፍለ ከተማ ፕላን ልማት ጽ/ቤት የበጀት አመት አፈፃፀሙን ከባለድርሻ አካሎች ጋር በጋራ በመሆን በመገምገም የ2017 የትኩረት አቅጣጫ ያወያየ ሲሆን በበጀት አመቱ የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።
ተቋሙ በ2016 በጀት አመት ክ/ከተማውን በፕላን የሚመራ ለማድረግ በርካታ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ የሰራ ሲሆን በተጨማሪም የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በርካታ ስኬታማ ስራዎችን መስራት መቻሉን የየካ ክፍለ ከተማ ፕላን ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፈይሳ ረጋሳ በሪፖርቱ ላይ አቅርበዋል፡፡
በበጀት አመቱ የተቋሙን የበጎ አድራጎት እና ኢኒሺየቲቭ ስራዎች እንዲሁም የተቋማት የእቅድ እና ሪፖርት ስርአት የመከታተል እና የመደገፍ ስራዎችም ተከናውነዋል፡፡
የስፓሻል ፕላን ዝግጅት አሰራርን በክትትል፣በግምገማ እና ቁጥጥር ውጤታማነት ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እቅድ ዝግጅት፣ክትትል እና ግምገማ እንዲሁም ምዘና ስርአት በማሻሻል በበጀት አመቱ በሰፊው መሰራቱም በሪፖርቱ ላይ ቀርቧል፡፡
ከእቅድ ውጪም ደራሽ ስራዎች ደርቦ በመስራት ስኬት የተመዘገበ ሲሆን የኮሪደር ልማቱን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶችን ከአጋር አካላት ጋር በስኬት ማከናወንም ተችሏል፡፡
የሪፎርም ስራዎች፣የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል እና በቴክኖሎጂ በመደገፍ የማዘመን ስራ፣የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመፍታት የተቋማት የክትትል አግባብ አጠናክሮ መቀጠል የ2017 በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ በእቅዱ ላይ ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም በ2016 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ለነበራቸው የክፍለ ከተማ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የእውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም የተከናወነ ሲሆን የተሻ ለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የየካ ክ/ከተማ ፅዳት አስተዳደር ፅ/ቤት አንደኛ፣የየካ ክ/ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ሁለተኛ እንዲሁም የየካ ክ/ከተማ ሰላም እና ፀጥታ ፅ/ቤት እና ዲዛይን እና ግንባታ ፅ/ቤት ሶስተኛ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የመስመር ማዛወር ስራ ተጠናቀቀ
ግንቦት 2 /2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More
የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርደር ልማት የኤሌትሪክ መስመር ማዛወር እና መልሶ ግንባታ ስራ አጠናቆ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
በመስመር ማዛወር ስራው ወቅት የልማት ተናሺ ለነበሩ 2 ሺ 7 መቶ ደንበኞች በአዲስ መልክ በሰፈሩበት አካባቢ አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ ተከናውኗል፡፡
የኃይል መስመር ማዛወር ስራው አጠቃላይ 68 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን፤ በቀጣይ የኃይል መቆራረጡን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ታሳቢ በማድረግ 50 ኪሜ የመካከለኛ እና 18 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ማሻሻያ መደረጉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
የቲቢ በሽታን ለመከላከል ለሚሰራው የቲቢ ምርመራ ዘመቻ ስራ ለዘርፉ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More
የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የቲቢ በሽታን ለመከላከል ለሚሰራው የቲቢ ምርመራ ዘመቻ ስራ ላይ ለሚሳተፉ ለዘርፉ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ስልጠናውን የጤና ጣቢያ ሃላፊዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የቲቢ ክፍል ባለሙያዎች እንዲሁም በምርመራ ዘመቻው የሚሳተፉ ባለሙያዎች ወስደዋል፡፡
የክፍለ ከተማው ጤና ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሶፊያ አለሙ የቲቢ በሽታ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ፤በጊዜ ህከምና ካልተደረገ ገዳይ የበሽታ አይነት መሆኑን በመግለፅ የዘመቻ ምርመራ በማዘጋጀት ይበልጥ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ምርመራ ለማድረግ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ማራኪ ለማድረግ በአምስት አቅጣጫ የኮሪደር ልማት ስራው እየተፋጠነ ይገኛል።
በየካ ክፍለ ከተማም የኮሪደር ልማቱ ነዋሪውን በባለቤትነት በማሳተፍ እየተከናወነ ሲሆን በዛሬው እለትም በወረዳ 07 እና 08 የመንገድ ዳር የልኬት ስራውን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች ጋር በማጠናቀቅ ለትግበራው ዝግጁ የማድረግ ስራ ሰርቷል።
መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮን የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ የማሳደግ ንቅናቄ መርኃ-ግብር በወረዳዎችም ተጠናክሮ ቀጥሏል
መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More
የክ/ከተማና የወረዳው አመራሮች፣ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር የሚጠቀሙ አንቂዎችና የክብር እንግዶች በተገኙበት የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ፤ የክፍለ ከተማውናንና የወረዳውን የማህበራዊ ሚዲያ የፌስ ቡክ ገጽ ማሳደግያ ንቅናቄ መርሃ ግብር በይፋ በመክፈት ወደ ስራ ገብቷል።
ጽህፈት ቤቱ “ማህበራዊ ሚዲያን ለወል ትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው ዕለት በወረዳ 01 እና 02
የየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ በቀለ በወረዳ 01 እና 02 አስተዳደሮች በመገኘት መርኃ-ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን በከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት ንቁ ተሳትፎ የሚያደርግ ህብረተሰብ በመፍጠር አዲስ አበባ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ሆና እንድትታይ የተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦችን በመጠቀም ዘመናዊ ፣ግልጽ እና ፈጣን ምላሽ መስጠትን ባህሉ ያደረገ የኮሙኒኬሽን ስርዓት በመዘርጋትና በዘርፉ መሪ ሚና በመጫወት ብሎም በመንግስትና በህዝብ መካከል ጥራት ያለውና እና ለሁሉም ነዋሪ ተደራሽ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ህዝብና መንግስት የሚያቀራርቡ ሥራዎች ላይ አተኩረን እንሰራለን ብለዋል።
የወረዳው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታምራተት አላዩ በበኩላቸው በህዝብ ግንኙነት ተግባራችን አሉታዊ እሳቤዎችንና የሐሰት ዘገባዎችን ከሚያሠራጩ ሚዲያዎች በመጠበቅ መንግስትንና ህዝብን በሚያቀራርቡ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አመላክተዋል።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ የወረዳው አመራሮች፣ ማህበራዊ አንቂዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘመቻውን ተቀላቅለዋል።
በዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ የተመራ የፌዴራል የሱፐርቪዥን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ የመስክ ምልከታ አደረጉ ::
በሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ኢርጎጌ ተስፋዬ የተመራ በፊዴራል ደረጃ የተዋቀረው የሱፐር ቪዥን ቡድን የመስክ ምልከታ እያደረገ ይገኛል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በቴክኖሎጅ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን፣ ከተማ ግብርና ፣ ስፖርት ማዘውተሪያዎችን ፣ደይኬር እና የክ/ከተማ ተቋማት ስራዎችንም ምልከታ እያደረገ ይገኛል።
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!!!
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽህፈት ቤት በ6 ወር የስራ አፈፃፀም በከተማ ደረጃ ተመዝኖ ከ11ዱ ክፍለ ከተማ 2ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆነRead More
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በዛሬው ዕለት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀሙን ከከተማና ከክፍለ ከተማ ዘርፍ አመራሮች ጋር የገመገመ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማትና ክፍለ ከተሞች እውቅናና ሽልማት በቢሮ ኃላፊዎች እጅ አበርክቷል።
በዚህም የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ልማት ጽህፈት ቤት በክፍለ ከተማው ቴክኖሎጂን ተግባራዊ በማድረግና በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻሉ እውቅና ተሰጥቶታል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ማስረሻ ተገኝተው እውቅናውን የተቀበሉ ሲሆን ለውጤቱ መገኘት የክፍለ ከተማው አስተባባሪዎች፣ በየደራጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።
ጽህፈት ቤቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችን ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ያነሱት አቶ ቴዎድሮስ እውቅናው ይበልጥ ጽህፈት ቤቱን የአገልግሎት እርካታ እስኪረጋገጥ እንዲተጋና የተቋም ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያነሳሳው መሆኑን አክለዋል።
ባለጉዳይ ቀንን ምክንያት በማድረግ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ተጠናክሮ ቀጥሏል
ጥር 15 /2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽንRead More
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን መሠረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ዕሮቡና አርብን ሙሉ ቀን በመጠቀም ቀልጣፋና ፍትሃዊ እንዲሁም ግልፀኝነት የሰፈነበት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
በአገልግሎቱ በዋናነት ለነዋሪዎች ጥያቄ ፈጣን ምላሽ የሚያሰጥና ግልፀኝነትና ብልሹ አሰራር በማስቀረት እርካታን የሚያረጋግጥ በመሆኑ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት በመስራት ላይ ነው።
ተገልጋዮች እየተሰጠ ባለው አገልግሎት ደስተኛ መሆናቸው የካ ኮሙኒኬሽን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ፅህፈት ቤት ለወጣቶች ሲሰጥ የቆየውን የህይወት ክህሎት ስልጠና ተጠናቀቀRead More
ጥር 15/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
ፅህፈት ቤቱ ከ18-25 አመት የዕድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ ወጣቶች ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የህይወት ክህሎት ስልጠና አጠናቋል።
በስልጠና ማጠቃለያ መረሀ-ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የየካ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ታመነ አበበ በስልጠናው 799 ወጣቶች መሳተፋውን ገልፀው ወጣቶቹ በቀጣይ ስድስት ወራት በተለያዩ ድርጅቶች ውስጥ የስራ ላይ ልምምድ ስልጠና የሚሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ታመነ አክለው ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ መከታተል ራሳቸውን መለወጥ እንሚኖርባቸው አሳስበው ስልጠው የሚጀመርበትን ጊዜ በወረዳቸው አማካኝነት ጥሪ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል፡፡
የምስራቅ አጠቃላይ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ዩንስ ሑንዱማ በበኩላቸው ስልጠናው ለነገ የስራና ማህበራዊ ህይወታቸው ትልቅ እገዛ የሚያደርግና በርካቶች ውጤታማ እንደሆኑ ገልጸው ሰልጣኞች በቀጣይ በስራ ላይ የሚያጋጥሙዋቸውን ተግዳሮቶች በሰለጠኑት መሰረት ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
አስተዳደሩ በከተራ፣ ጥምቀት እና ቃና ዘገሊላ በዓላት አከባበር ወቅት የተሰሩ የጸጥታ ሥራዎችን ገመገመ
ጥር 13/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማው የከተራ፣ ጥምቀት እና ቃና ዘገሊላ በዓላት አከባበር ወቅት የተሰሩ የጸጥታ ሥራዎችን ከከተማ ደጋፊዎች፣ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ የስራ አመራሮች ፣ከፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በጋራ ገምግሟል።Read More
ውይይቱን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ እንንደገለፁት የአደባባይ በዓላቱ በሰላም በሚከበሩበት ሁኔታ ላይ ቀደም ብሎ አስተዳደሩ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሰፊ ውይይት በማካሄድና ጠንካራ ስምሪት በመስጠት ለአከባበሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አንስተው ህብረተሰቡ፣የሃይማኖት ተቋማት፣ የጸጥታ አካላትና የክፍለ ከተማው የሰላም ሠራዊት ከአስተዳደሩ ጋር በቅንጅት በመሥራታቸው በዓላቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብረው መጠናቀቃቸውን ገልፀዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላና በዓሉ ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲጠናቀቅ ቀንና ማታ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በተጠንቀቅ ለሰሩት የፀጥታ አካላት፣ለሰላም ሰራዊት አባላት እንዲሁም በየደረጃዉ ላሉ አመራሮች ምስጋናቸዉን አቅርበው ቀደም ብሎ የነበሩ ስጋቶችን በመለየት ወደ መፍትሄው ማምራታችን እና በቅንጅት መሰረታችን በአሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የጎላ ሚና ነበረው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ምክርቤት የማዘጋጃ ቤታዊ ቋሚ ኮሚቴ የተከበሩ አቶ ማሾ ኦላና በበኩላቸው ሁሉም በየደረጃው የተሰጠውን ተልእኮ ተከትሎ የራሱን ስራ በትጋት በመወጣቱ የተሳካ ስራ መስራት ተችሏል በሒደቱ ላይ አስተዋፅኦ ለነበራችሁ አካላት በሙሉ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
በግምገማው በበአላቱ ወቅት የነበረው የተቀናጀ ስራ አበረታችና የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ያስቻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ጥንካሬዎችን አጠናክሮ በማስቀጠልና ውስንነቶችን በማረም በሚቀጥሉት ጊዜያትም በሰላምና ፀጥታዉ ጉዳይ ላይ ጠንካራ ርብርብ እንደሚደረግ ተገልፃል።
የምስጋና መልዕክት!
የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓል በክፍለ ከተማችን በሁሉም የታቦታት ማደሪያዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ታቦታቱም በሰላም ወደ መንበረ ክብራቸው ተመልሰዋል።Read More
ታቦታቱ ወጥተው እስኪመለሱ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፣ የክፍለ ከተማችን ፓሊስ መምሪያ አመራሮችና አባላት፣ የአድማ ብተና ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች፣ የሰላም ሰራዊት አባላት በአጠቃላይ የፀጥታ አስከባሪ እና በየደረጃው የምትገኙ የከተማ ደጋፊ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ሰላም ወዳዱ ህብረተሰባችንን በራሴና በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በዓሉ ካለአንዳች የፀጥታ ችግር ሃይማኖታዊ ትውፊቱ ተጠብቆ በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር ቀደም ሲል ጀምሮ ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅራችን እና ባለድርሻ አካላት በመናበብ፣ በመደማመጥ፣ በመተሳሰብ፣ እና በመቀናጀት ስኬታማ ማድረግ በመቻሉም በቀጣይም ጥምቀት እና ቃና ዘገሊላ ላይ ሰርተን ውጤታማ የሆንባቸውን ተግባራት በአድዋ የጀግኖች አባቶቻችን የመታሰቢያ ዝክረ በዓልና በመጭው የመሪዎች ስብሰባ ላይ መድገምና የከተማችንን ፀጥታ ዘላቂነት እያረጋገጥን መሄድ ይጠበቅብናል።
በተለይ በበጎ ፈቃደኝነት ለከተማችን ሰላም መረጋገጥ ቀን ፀሃዩ ለሊት ቁሩን ተቋቁማችሁ ከፀጥታ አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ እየሰራችሁ የምትገኙ በሁሉም ወረዳ የምትገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት ለነበራችሁ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያመሰገንኩ በቀጣይም ተሳትፏችሁን አጠናክራችሁ በማስቀጠል የየአካባቢያችሁን ሰላም በዘላቂነት እንደምታጠናክሩ በመተማመን ሁሌም ለምትሰሩት ስራ በአስተዳደሩና በራሴ ስም አመሠግናለሁ።
በመጨረሻም በዓሉ በደመቀና በአማረ መልኩ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻሁን ለተወጣችሁ አካላት በሙሉ በድጋሚ ምስጋናዬ በየአላችሁበት ይድረሳችሁ።
አቶ ብርሃኑ ረታ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ
ለወረዳና ለክ/ከተማ ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጠ
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት በ3 የስልጠና አርስት ላይ ማለትም 1.webmail 2. acronis True lmage 3. A.A complaint management portal / የካ ክፍለ ከተማ የአይሲቲ ባለሙያዎች እና ለወረዳ የአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰቷል፡፡
ሕዳር 27/2016 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ጽ/ቤት
ዜና ሹመት
አቶ ብርሃኑ ረታ አበጋዝ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ
ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም የካ ኮሙኒኬሽን
የአቶ ብርሃኑ ረታ አጠቃላይ የስራ ልምድ፣ የትምህርት ዝግጅት እና ለሃገራቸው ያበረከቷቸውና እያበረከቱት ያለውን እንቅስቃሴ ለምክር ቤቱ አባላት በክፍለ ከተማው የመንግስት ተጠሪ ሃላፊ በአቶ መገርሳ ገላና ቀርቦ ሃሳብ ከተሰጠበት በኃላ በሙሉ ድምጽ ሹመቱ ፀድቋል።
አቶ ብርሃኑ ረታ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙRead More
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው የተሾሙት አቶ ብርሃኑ ረታ መንግስት በሰጣቸው ኃላፊነት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት የመልካም አስተዳደርና የአቤቱታ ዘርፍ አማካሪ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ለአዲሱ የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ረታ መልካም የስራ ዘመን ይመኛል።
ዜና ጉብኝት
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በመንግስት ካፒታል እየተገነቡ ያሉ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው ጉኝተዋል።Read More
የየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የቀድሞው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞገስ አባተ እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መገርሳ ገላና አዲስ ተሹመው ለመጡት ዋና ስራ አስፈፃሚ ለአቶ ብርሃኑ ረታ በክ/ከተማው እየተገነቡ ያሉ የመንግስት ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው አስጉብኝተዋል።
ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ በኮከበጸብሕ 2ኛ ደረጃ ትምህርትቤት፣ በደጃዝማች ወንዲራድ 1ኛደረጃና ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እና በወጣቶች ገነት ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት እየተገነቡ ያሉ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የወረዳ 01 እና ወረዳ 02 የአስተዳደር ህንፃ እድሳትን ያለበትን ደረጃ ተመልክተዋል።
ፕሮጀክቶቹ በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ በጉብኝቱ ተገልፆል።
የክፍለ ከተማው ተቋማት በቅንጅታዊ ትብብር አሰራር ላይ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
በየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት በተመራው የፊርማ ስነ ስርአት ተቋማት በቅንጅት እና በትብብር በጋራ በሚያሰራቸው ጉዳይ ላይ የትስስር ሪፖርት አቅርበው የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።Read More
በፊርማ ስነ ስርአቱን የመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ፀሀይ ኪባሞ ቅንጅታዊ አሰራር የመንግስት ስራዎችን በአግባቡ ለማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ ተቋማት የትኩረት ማዕከላቸውን ተግባር ላይ ብቻ በማድረግ የፊርማ ስነ ስርአት ማድረጋቸውን ገልፀው ተቋማት ከተቋማት ጋር በቅንጅት መስራታቸው ስራን ለማቀላጠፍ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
የቅንጅታዊ ትብብር አሰራሩም በሚፈለገው ልክ ተቋማቱ ተቀናጅተው እንዲሰሩ የሚያስችል በመሆኑ በየጊዜው አፈጻጸሙ እየተገመገመ ተቀራራቢ ውጤት እንዲመጣ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም አብራርተዋል።