የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተካደር በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ስር ካሉ 12 ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በስሩም 24 ጽ/ቤቶች ይገኛሉ፡፡ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በክ/ከተማው በሰሜን ክፍል የሚገኝ ሲሆን የወረዳው የህዝብ ብዛቱም ወንድ 7845 ሴት 9396 በድምር 17,241 ነዋሪ በላይ እንደሚሆን ይገመታል፡፡Read More
በወረዳ አስተዳደሩ ስር 24 ያህል ጽ/ቤቶች፣ 1 ጤና ጣቢያ እና 5 ት/ቤቶች ይገኛለ፡፡
በወረዳ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያሚ ችግሮችን በየደረጃው በመለየትና በመፍታት አገልግሎት አሠጣጡን በማሻሻል መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ዘላቂ ልማትንና የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን በዚህም አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
በወረዳችን የአገልግሎት አሰጣጥ ቸግሮችን የመፍታት ጉዳይ ቁልፍ የወረዳው የትኩረት አጀንዳ ተደርጎ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ይህም በመሆኑ በአንድ በኩል ቀደም ሲል የወረዳችን በርካታ የህ/ሰብ ጥያቄዎችን ተከታትሎ የመፍታትና በሌላ በኩል ደግሞ በየጊዜው ከህ/ሰቡ አዳጊ ፍላጎት አኳያ ያለማቋረጥ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና ፍትሃዊነት ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመመለሰ በበጀት ዓመቱ ከላይ እስከ ታች ችግሮችን ከነመንስኤያቸውና መፍትሄያቸውን ለይቶ በማስቀመጥ በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን ባሳለፍነው ዓመት ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የተሄደበትን አግባብ አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡